Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Wedi
Member+
Posts: 8649
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

ፋኖ በለስ ቀናው!! አብዛኛው ደቡብ ጎንደን ከብ አዴን አገዛዝ ነጻ ወጥቷል፡፡ በህዝብ የተመርጡ የህዝብ አስተዳደሮች እየተመሰርቱ ነው!!

Post by Wedi » 20 Jul 2023, 18:50

ፋኖ በለስ ቀናው!! አብዛኛው ደቡብ ጎንደን ከብ አዴን አገዛዝ ነጻ ወጥቷል፡፡ በህዝብ የተመርጡ የህዝብ አስተዳደሮች እየተመሰርቱ ነው!!

እብናት ከተማን ጨምሮ ፋኖ የተቆጣጠራቸው የደቡብ ጎንደር አከባቢዎች ላይ ከማህበረሰቡ ጋር በመሆን አዲስ መዋቅር እየዘረጋ መሆኑ ተገለፀ!
እብናት ከተማና በዙሪያዋ የሚገኙ አከባቢዎችን ጨምሮ ማክሰኝት፣ አዲስ ዘመን፣ በለሳ በፋኖ ቁጥጥር ስር ገብተዋል።

የአማራ ሕዝብ የቁርጥ ቀን ልጆች በአሁን ሰዓት በተቆጣጠሯቸው አከባቢዎች ላይ የህዝብ አገልግሎት መስጫ ተቋማት እንዳይዘረፉ እየተቆጣጠሩ ሲሆን በተጨማሪም የማህበረሰቡን ሰላም ለማስጠበቅ 24 ሰዓት እየሰሩ ነው ተብሏል።

ፋኖዎች በተቆጣጠሯቸው አከባቢዎች ላይ የነበሩ የወረዳና የከተማ አመራሮች አከባቢውን ለቀው ወጥተዋል የተባለ ሲሆን፡ የብልፅግናን አጀንዳ አናስፈፅምም፣ ከህዝብ ጎን ነን ያሉ የወረዳ ፀጥታ ኃይሎች ከነመሳሪያቸው እጃቸውን ለፋኖ ሰጥተዋል ሲሉ ምንጮች ገልፀዋል።

የመንግስት አመራሮች በለቀቁባቸው የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ፋኖዎቹ ከህዝብ ጋር በመሆን አዳዲስ አመራሮችን እየተኩ መሆናቸውም ተመላክቷል።

በህዝብ የተመርጡ አዲስ የህዝብ የአስተዳደር መዋቅር እየተዘረጋ መሆኑን ፋኖ ውባንተ አባተ የሚመራው የገብርየ ሻለቃ አባላት ለአማራ ድምፅ ሚዲያ ገልጿል።

:!: