አሁን ሁሉም ነገር ብትን ብትንትን ብሏል ። ሁሉም ዝርዝር ነው። ሁሉም ዝልዝል ነው። ሁሉም ትንትን ነው። ሁሉም ትርትር ነው ። ለምን? ምን እየሆንን ነው? ይህ ሁሉ መታመስ የሰዎች ፐርሰፕሽን ነው ወይስ አዲስ አይነት አገር እየመጣ ነው? አዲስ አይነት ሕዝብ እየመጣ ነው ወይስ ያለው እየሞተ? ምንድን ነው እየሆነ ያለው?
ኢትዮጵያ የሚለው አንድ ቃል እየፈረካከሰው ነው? እየተበተነ ነው? አገር፣ ሕዝብ፣ መደብ፣ የሚሉት ቃላት? ምንድን ነው እየሞተ ያለው? ምንድን ነው እየተወለደ ያለው?
አለምንም ጥርጥር እየሞተ፣ እያረጀ፣ እየፈረ ያለ አንድ ነገር አለ! እየመጣ፣ እየተፈጠረ ያለ ሌላ አንድ ነገር አለ! ምንድን ናቸው እነዚህ ነገሮች?
የምርጥ ማህበረ ሰብ ሲስተም ሶስት ወይም አምስት መቆሚያ እግሮች አሉት ። በፊዚክስ እግጅ እስቴብል ጽኑ የሆነው የእግር ቁጥር ሶስት ነው። ሶስት ወገን፣ ሶስት እግር፣ ሶስት ምሰሶ ያለው ነገር ነው ጸንቶ የሚቆመው። ከዚያ አልፎ የእግሮቹ ቁጥር በበዛ ልክ የነገሩ አቋቋም ይዛባል ። ባለ ሶስት እግር በርጩማ የመጨረሻው ጽኑ የማይዛባ ወምበር ነው ።
ከዚህ የፊዚክስ ሕግ ከተነሳን ዛሬ ላይ የኢትዮጵያ አቋቋም የተዛባው መቆሚያ እግሮቿ ስለበዙ ነው። ለምሳሌ መሬት አንድ መቆሚያ ነው ። ያለ መሬት አገር አይኖርም ። መሬት የማንም ሃብት ንብረት አይደለም ። የኢትዮጵያ መሬት በክልሎች መሸንሸን መሬት አልባ አገር እንደ መፍጠር ነው ።
ለምሳሌ ሕዝብ አንድ የአገር መቆሚያ ነው ። ሕዝብ የአገር መቆሚያ እግር የሚሆኑት ሁሉም እኩያ ዜጋዎች ሲሆኑ እንጂ የተዛባ የጎሳ ቡድኖች ሲሆኑ አይደለም ። ስለዚህ ኢትዮጵያ በመበተን ላይ ያለችው ዜጋ አልባ የሰዎች ክምችት ቅርጽ አልባ፣ ቅጥ አልባ የሰዎች መንጋ ስለሆነች ነው።
ከመሬትና ሕዝብ ቀጥሎ ያለው የኢትዮጵያ መቆሚያ እግር ማንነት ነው። ማንነት የሌለው ሕዝብ ማህበረ ሰብ አይደለም፣ ብትን እንሰሳ ነው ። ማንነት ታሪክ ነው ። ማንነት ካልቸር ነው። ማንነት ሃይማኖት ነው። ማንነት ኢኮኖሚ ነው ። ማንነት የአንድ ሕዝብ ህልውና ሜሞሪ ነው ። ሜሞሪ የሌለው ነገር ምን እንደ ሆነ አያውቅም፣ ማን እንደ ሆነ አይታወቅም ። ይህ እጅግ እጅግ መሰረታዊ የአገርነት መቆሚያ ምሰሶ ኢትዮጵያዊ ማንነት ነው።
በእኔ እምነት ኢትዮጵያዊያን ነጻ በመሆናቸው ተበትነው እየጠፉ ያሉ በጎች ናቸው ። የኢትዮጵያ መድህን ፓርቲ፣ ዴሞክራሲ፣ ሃይማኖት ቅብጥርሴ አይደለም ። የመጀምሪያ የኢትዮጵያ መድህን ፍቅረ ሕይወት፣ ፍቅረ ፍጥረት ፍልስፍናን መቀበል ነው። ፍጥረት የሰው ህብት፣ የሰው ንብረት አይደለችም ። ፍጥረት፣ ሕይወት ተጠቅመንበት ተንከባክበን ለሌላ ትውልድ የሚተላለፍ እጅግ ክቡር እጅግ ቅዱስ ጸጋ ነው ። ይህን ፍልሳፍና እንደ እምነት መቀበል አለብም ።
ዴሞክራሲ፣ ካፒታሊዝን፣ እድገት፣ ብልጽግና የሚባሉት አሮጌ የሞቱ የበሰበሱ ሃሳቦች ጋር ላንዴም ለሁሌም መፋታት አለብን ። ዜጋዎች እኩያዎች ናቸው ። አንድ ሰው በሌላ ሰው ላይ ለመያዝ የሚታትረው ስልጣን ወይም ኃይል ተሽሯል፤ አሁን ተቀባይነት የለወም ። ሰዎች ፣ ሕዝቦች ባሉበት መንደር ሆነ ወንዝ እንደ እኩያሞች በኩልነት በመግባባት በመስማማት ራሳቸውን ይገዛሉ ። ሌላ ማንም ሰው ሆነ ፈጣሪ መጥቶ ሌሎችን ሊገዛ ሊያዝዝ በፍጹም አይችልም ። ዴሞክራሲ ሞቶዋል ። አሁን የሚመጣው እኩዮክራሲ ወይም ስርዓተ እኩያነት ነው። በዚህ መሰረት የሚቀጥለው ፖለቲካችን አረንጓዴ ስርዓተ መንግስት ካልሆነ እንደ ሕዝብም እንደ ካልቸርም ጠፊ ነን።
በመጨረሻም ኢትዮጵያ የሚለው ቃልና መለያ ከሁላችንም ካልቸር፣ እምነት፣ ጎሳ ፣ እውቀትና ሃብት የላቀች ዘላለማዊ መለያ ስም ስለሆነ በዚህ መለያ የማያምኑና ይህን መለያ የማይቀበሉ ኢትዮጵያ በምትባል አገር ውስጥ የመኖር የሞራል ብቃትም ሕጋዊ ብቃትም ሊኖራቸው አይችልም ።
ሆረስ ዐይነ ብርሃን
Re: ኢትዮጵያዊ ፤ ነጻ ስለሆነ የጠፋ ሕዝብ!
ይህ አስተያየት አንብባችሁ ስትጨርሱ እስቲ የሽግግር ኮሚሽን ስለሚባለው የድንቁርና ኮሚሽን አስቡ? ሶስት ወይም አራት ቁልፍ በሆኑ ፍጹም መሰረታዊ ወይም ፋውንዴሽናል አላማና ፋናዎች ላይ አገሪቱን እንደ ማወያየት 120 ሚሊዮን አጀንዳ በመሰብሰብ ኢትዮጵያን እያፈራረሰ ነው ።
ኢትዮጵያዊያን ነጻ ስለሆኑ መንገድ የተፋቸው ፣ ፋና ያጡ ፣ የተበተኑ በጎች ናቸው !
የአቢይ አህመንድን የጎሳ ዲሪቶ መደመር ቅራቅምቦን አስቡ !
የኢዜማን የዉሸት የዜጋ እኩያነትና ያን ውደ ጎን አድርጎ በጎሳ ዲሪቶ ዝባዝንኬ ከወረሙማ ጋር አገር ሲያፈርስ አስቡት !
ኢትዮጵያዊያን ነጻ ስለሆኑ መንገድ የተፋቸው ፣ ፋና ያጡ ፣ የተበተኑ በጎች ናቸው !
የአቢይ አህመንድን የጎሳ ዲሪቶ መደመር ቅራቅምቦን አስቡ !
የኢዜማን የዉሸት የዜጋ እኩያነትና ያን ውደ ጎን አድርጎ በጎሳ ዲሪቶ ዝባዝንኬ ከወረሙማ ጋር አገር ሲያፈርስ አስቡት !