ቤተ-ክርስቲያን'ኮ የክርስቶስ ቤት ነው። ማንም በማንም ላይ ሊዘጋው አይችልም። ይህ የሚያሳየው በር ዘጊዎቹ መሠረታዊው የክርስትና አስተምሮት ያልገባቸው፣ ውዳሴ ማርያምን ሳይሆን ውዳሴ ማለሊትን ሲደግሙ ከርመው የደቆኑና የቀሰሱ ተጋዳላይ ካድሬዎች መሆናቸውን ነው። ይህ ድራማ ለእኔ አስገራሚ አይደለም፤ ምክንያቱም ገና ከጠዋቱ መሰሪው ጠቅላይ ሚንስትር ሀገራዊወን ሲኖዶስ ለማፍረስ የኦሮሚያና የትግራይን ሲኖዶስ መመስረትና ማጣመር ዓላማ አድርገው እንደሚነሱ አውቅ ነበር። ከወራት በፊት አፈንጋጩ የኦሮምያ ሲኖዶስ በግሉ ትግራይ ድረስት ተጉዞ ከክልሉ ፕሬዚደንትና ከቤተክርስቲያናቱ አስተዳደር ጋር የመከረውም ይህንኑ ነው።
እውነት ለመናገር የኢትዮጵያ ኦሮቶዶክስ ኃይማኖት በሁለቱም ክልል ያለ ቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረትና ቅርሷን አስጠብቃ "ተነጠልኩ" "ተገነጠልኩ" የሚሉትን አውግዛ መለየት ነበር የሚገባት። የራሱን ጳጳስ መሾም ቀርቶ ሲፈልግ ለምን የራሱን ክርስቶስ አያነግስም! እነዚህ ሰዎች የሰው ጉዳትና ሀዘን ነጥቀው እያለቀሱ ዘላለም እሹሩሩ መባል የሚፈልጉ ጥቅመኞች ናቸው።