Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

የሲኖዶሱ ዘግናኝ ገመና ሲገለጥ⁉️ - ጦማሪዉ ፈላስፋዉ ጭሰኛ

Post by sarcasm » 08 Jul 2023, 10:31

የሲኖዶሱ ዘግናኝ ገመና ሲገለጥ⁉️
•••••••••••••••••••••••••••••

"የኢትዮጵያ ኦ/ተ/ቤ/ ክርስትያን የእርስ በርስ ጦርነቱ እንዲቆም በወቅቱ መግለጫ ባለመስጠቷ በመላው የትግራይ ህዝብ ምእመን መካክል ለተፈጠረው ቅሬታና አለመግባባት ቅዱስ ሲኖዶስ ይቕርታ ጠይቀዋል" ይላል የትላንቱ የሲኖዶስ የምፀት መግለጫ AKA ፌዝ::
ለመሆኑ ችግሩ የተፈጠረው ጦርነቱ እንዲቆም መግልጫ ባለመስጠቷ ብቻ ነው ወይ? የሚለው ጥያቄ ማንሳት ተገቢ ነው?

1- እነሱ እንዳሉት እንደ ቤተ ክርስትያን!
የትግራይ ህዝብ በጎረቤት አገር በባዕድ ሰራዊት ጭምር ሲጨፈጨፍ ካህናትና ምእምኑ ሲታረድ ጥንታዊ ገዳማትና የእምነት ቦታዎች በዘመናዊ ድሮን-ሲፈርሱ....ቅርሶችና ነዋየ ቅዱሳን ሲዘረፉ..ምንም አላወገዙም!

2- ከዚያ ይልቅ-ጦርነቱ እየተካሄደ በነበረበት ወቅት ቤተክርስትያኒቷ ከጨፍጫፊዎቹ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት ጎን ነኝ ብላ ይፋዊ መግለጫ ሰጥተዋል በመግለጫም ብቻ አላቆሙን ከየ አለማቱ አህጉረ ስብከቱ ገንዘብ በማሰባሰብ ለጦርነት ድጋፍ አድርገዋል!

3-የአለም ማህበረሰብ ጦርነቱ እንዲቆም ጥረት በሚያደርግበት ወቅትም የቤተክርስትያኒቱ ጳጳሳት "ጦርነቱ መቀጠል አለበት አሜሪካ እና የኢትዮጵ መንግስት ከሽብርተኛ ሃይል ጋር እኩል ቁጭ ብላችሁ ተደራደሩ ማለቷ ድፍረት ነው.." ወዘተ በማለትና እስከ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ፅ/ቤት በመጏዝ ለጦርነቱ ያላቸው ታላቅ ድጋፍ አስመስክረዋል!


4-በጦርነቱ ወቅት! የአማራ ታጣቂ ሃይል- በኢትዮጵያና በኤርትራ ጦር ጀርባ ታዝሎ ምዕራብ ትግራይን ከተቆጣጠረ ቡሃላ- ቤተክርስትያኒቱ ከወራሪዎች ጋር በመስለፍ የምዕራብ ትግራይ ሃገረ ስብከት በህገ ወጥ መንገድ ወደ ሰሜን ጎንደር ሃገረ ስብከት በማዛወር አሳፋሪ ተግባር ፈፅመዋል!

5-ከዚያም ቅዱስ ፓትሪያሪኩ በጦርነቱ ወቅት! በትግራይ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ ያለው ጄኖሳይድ እቃወማለሁ" ሲሉ የሲኖዶሱ አባላት መግለጫው የግላቸው እንጂ የቤተ ክርስትያኒቱ አቋም አይደለም" በማለት በአደባባይ ያለምንም ሐፍረት ተናግረዋል!

6-የቤተክርስትያኒቱ አንዳንድ ጳጳሳት በፋኖ ታጣቂዎች መካከል በመገኘት "የዋልድባ ገዳም የአማራ ነው::እዚህ ቁጭ ብለህ ጠላ ከምትጠጣ ተነስ:ታጠቅ ..ዝመት እያሉ በማነሳሳት የፋኖ ታጣቂዎች ለብዙ ዘመናት በገዳሙ ውስጥ በኖሩት መናኒያን መነኩሳት ላይ አሰቃቂ ጥቃት እንዲፈፀሙ አነሳስተዋል!

7-የባዕድ ሰራዊት ትግራይ ውስጥ ገብቶ እስከ ሁለት ሺህ የሚገመት የአክሱም ምእመንና ነዋሪ ሲጨፈጭፍ! ቤተክርስትያኒቱ ምንም አልተቃወመችም ብቻ ሳይሆን: የሲኖዶሱ ፀሃፊ አቡነ ጴጥሮስ "በአክሱም የተገደሉት ከሃያ አይበልጡም::" በማለት የዘር ማጥፋት ወንጀሉን ለመደበቅ ጥረት በማድረግ- ከወራሪዎችና ጨፍጫፊዎች ጎን ቆመዋል::

8-የቤተክርስትያኒቱ ጳጳስ በእግዚአብሄር አምሳል የተፈጠረውን የሰው ልጅ ከሰይጣን ጋር በማነፃፀር 'እነሱ ከሚገዙን ሰይጣን ቢገዛን ይሻላል' ብለው ሲናገሩ ቤተክርስትያኒቱ ንግግሩ አለማውገ እውነትም የዶግማ እና ቀኖና ብቻ ሳይሆን የአስተምህሮ ችግር እንዳለ ያሳያል!

8-በጦርነቱ ወቅት በአዲስ አበባ ሃገረ ስብከቶች የነበሩት የትግራይ ተወላጅ ካህናትና አገልጋዮች በህገ ወጥ መንገድ ከቦታቸውና ከአገልግሎታቸወ ማባረር ማዋከብ ማሰር ውስጥ የሲኖዶስ ሰዎች ዋነኛ ተሳታፊ ነበሩ!

10-በጦርነቱ ወቅት ቤተክርስትያኒቱ "በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸው አከባቢዎች" በሚል ምክንያት ለአማራና ለአፋር ክልሎች የገንዘብና የቁሳቁስ እርዳታ ስታደርግ ለትግራይ ህዝብ ሰብኣዊ እርዳታ እንዳይደርስ: የቤተክርስትያኒቱ ጳጳሳት "በጦርነቱ ወቅት የተጎዳው ትግራይ ብቻ አይደለም:" በማለት በትግራይ ህዝብ ስቃይና ረሃብ ተሳልቀዋል::

-ከዚያም አልፎ! በኢየሩሳሌም ገዳም ውስጥ ለብዙ ጊዜ ያገለገሉት መነኩሳት ከገዳሙ በህገወጥ መንገድ ሲባረሩ: ፓስፖርታቸው ሲቀማና እንዳይንቀሳቀሱ ድርጊቱን ለማስቆም ሲኖዶሱ ምንም የወሰደችው እርምጃ የለም!


ስለዚህ! አሁን  ላይ ደርሰው ለሰሩት ጥፋትና ወንጀል " ጦርነቱ እንዲቆም በወቅቱ መግለጫ ባለመስጠታችን ይቅርታ እንጠይቃለን.." በሚል ሽፋን በፍፁም ተድበስብሶ የሚታለፍ ጥፋት አይደለም::


እኛም ለሕሊናችን እረፍት ስንል "የገል እሳት የሚስጭረን ጎረቤት እስከምናጣ ድረስ" እውነቱን መናገራችንን እንቀጥላለን!

ፈላስፋው ጭሰኛ
Please wait, video is loading...