Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42769
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ያማራ ኢመደበኛ ምን?

Post by Horus » 23 May 2023, 01:50

እኔ ሆረስ የት ሄጄ ልፈንዳ፣ በሳቅ! :lol: :lol: :lol: ለመሆኑ ኢመደበኛ ድርጅት! ኢመደበኛ ዉጊያ! ኢመደበኛ ጦርነት ምንድን ነው? ኢመደበኛ በዘመነ ወያኔ የተፈጠረ ደደብ ቃል ነው። አሁን አማራ ያወጀው ሕዝባዊ ግምባር በፖለቲካ ጎኑ ሕዝባዊ የፖለቲካ ንቅናቄ ይባላል! ኋላ ላይ ሕዝባዊ አብዮት ይሆናል፤ በወታደራዊ ጎኑ የሽምቅ ወይም የጉዌሪላ ዉጊያ ይባላል። ቃሉ የፖርቱጋልና እስፓኝ ሲሆን ጉዌራ ማለት (እኛ ጎራ) የምንለው ጦርነት (ዋር) ማለት ነው። ኢመደበኛ ቅብጥርሴ ምን አመጣው ? የጉዌሬላ የጎሬላ ዉጊያ በጽናት ከከረመ ወደ ሕዝባዊ ጦርነት (ፒፕልስ ዋር) ይለወጣል ።

እኔ ደግሜ ልበለው፤ አማራ በጀመረው ሕዝባዊ ጦርነት ከጸናበት የኢትዮጵያ ፖለቲካ በጭንቅላቱ ይቆማል! አማራ በመላ ኢትዮጵያ አለ፣ በከተማም በገጠርም!! ይህ የጉዌሬላ ጦርነት በከተማም በገጠርም ብቅ ብቅ ቢል አትገረሙ ! ይህን ሁሉ ስል ካማራ ጋር ደብሎ የሚነሳውን ኢትዮጵያዊ ስልቆጥር ነው !!!