Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Right
Member
Posts: 4810
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

Eritrea mobilizing for a new war. Report.

Post by Right » 08 May 2023, 08:23

ኤርትራ በተለየ ሁኔታ የጦር ልምምድ እያደረገች ነው
May 8, 2023 – Konjit Sitotaw

የኤርትራ ጦር በአዲስ መልኩ የጦር ልምምድ መጀመሩ እያነጋገረ ነው ፤ ይህ በአራቱም የኤርትራ ማዕዘን የተጀመረው የጦር ልምምድ በቀጣይነት ወዴት ያመራል ወይንስ ከማን ጋር ውጊያ የመግጠም ሲልም ማንን ለማስፈራራት የሚደረግ የጦር ልምምድ ነው ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ይጠይቃሉ። መረጃ ኮም ከተለያዩ የኤርትራ ተወላጆችና በከሰላ፣ ከረን እና ሰንዐፌ አከባቢ እንዲሁም አስመራ ያሉ ምንጮቿን ተጠቅማ ባሰባሰበችው መረጃ መጭው ጊዜ የጦርነት ስጋት መኖሩ አመላካች ነው። በዚህ ሳምንት ውስጥ ስለሱዳን ያወሩት ፕሬዝዳንት ኢሳያስ የሱዳንን ሕዝብ የሚበጠብጠው ጎረቤት የሆነ የባዛር መንግስት ነው ሲሉ መተቸታቸው ይታወሳል።

ምንጮቻችን እንደሚሉት ኤርትራ ከፕሪቶሪያው ስምምነት በሗላ ከአብይ አስተዳደር ጋር ያላት ግንኙነት የቀዘቀዘ ሲሆን ኤርትራን ባገለለ መልኩ የሚደረጉ የፖለቲካ ጨወታዎች በችግር ግዜ መሸሸጊያ በደስታ ጊዜ እርግጫ ምንድነው የሚል ጥያቄ ከአስመራ ተነስቷል። አብይ አሕመድ አስመራን ለመሄድ ያላቸውን ፍላጎት ቢያሳዩም ባለፉት ወራት ሁለት ጊዜ ወደ ኤርትራ እንዳይመጡ የተከለከሉ ቢሆንም ለሶስተኛ ጊዜ አስመራን ለማየትና ከኢሳያስ ለመገናኘት ጠይቀው ፍቃድ እየጠበቁ መሆኑን ምንጮቻችን ነግረውናል።

የኤርትራው ፕሬዝዳንት በኢትዮጵያና በሱዳን ጉዳይ ጣልቃ ገብተዋል ጦርም አዝምተዋል ተብለው ይወቀሳሉ። ባለፈው ሳምንት የሱዳን ጉዳይ በተመለክተ በሰጡት መግለቻ ጥያቄ የተነሳባቸው የኤርትራው ፕሬዝዳንት የአማራን ፋኖ ያሰለጥናሉ ይረዳሉ ተብለው በአብይ አስተዳደር ካድሬዎች ይወቀሳል። በተለይ በወልቃይት ጉዳይ ላይ እጃቸውን አስገብተዋል ሕወሓትን ለመምታት መጠቀሚያ ሊያደርጉት ነው ሲሉ ታዛቢዎች ይተቻሉ። ኤርትራ በኢትዮጵያ እና በሱዳን ጉዳይ ጣልቃ ገብታለች ሲሉ በርካቶች ይስማማሉ።

የኤርትራ ሰራዊ በኢትዮጵያ ድንበሮች አቅራቢያ ባሉት አቅራቢያ ላይ የጦር ልምምድ እያደረገ ሲሆን ከፍተኛ የጦር መሳሪያዎችንም እያከማቸ ነው። በተጨማሪም ከትግራይ የተመለሱና ያፈገፈጉ ሃይሎቹን ሰብስቦ በቅርብ ርቀት በኢሮብ በዛላንበሳ በባድመ በፆረና እና በተለያዩ አከባቢዎች ማስፈሩ ታውቋል። ይህ የጦርነት እንቅስቃሴ ከፍተኛ ውጥረት እንዳይፈጥር ተሰግቷል። በተጨማሪም በመሃል ሃገር ኢትዮጵያ የተበተኑ የኤርትራ ተወላጆች በስለላ ስራ ላይ ተሰማርተዋል በትግራይ ተወላጅነት ስም የኢትዮጵያዊ መታወቂይ ይዘዋል ተብለው መከሰስ ጀምረዋል። ባለፈው ሳምንት የኤርትራ ተወላጆች በመቀሌ የትግራይ ተወላጅ መስለው መታወቂያ አውጥተው ሲኖሩ እጅ ከፍንጅ ተያዙ የሚል ዜና ከትግራይ መሰማቱ ይታወሳል።

በተለይ አሜሪካ እስከዛሬ ድረስ የኤርትራ ጦር ከትግራይ አልወጣም ስትል ትወቅሳለጭ አሜሪካ በተደጋጋሚ በምታወጣው መግለቻ የኤርትራ ጦር በትግራይ እስከዛሬ ድረስ እንዳለና በሕዝቡ ላይ በደል እያደረሰ ትግራይንም እየዘረፈ ስትል ትወነጅላለች ። የኤርትራ ጦርም ትግራይን ለቆ እንድወጣ እየወተወተች ነው። ባለፈስ ቀናት የኢትዮጵያው ተቅላይ ሚኒስትር በውስጥ ጉዳያችን ጣልቃ ገብተው የሚፈተፍቱ ሲሉ በስም ያልተቀሱትን ሃገር ተችተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህን ከተናገሩ በሗላ ለጉዳዩ ቅርብ ማነው በሚል ግብጽ ብትጠረጠርም ጉዳዩን እና ወቅታዊውን ትኩሳት አስመልክቶ ኤርትራን እያሉ እንደሆነ ከድምዳሜ ተደርሷል። ጠቅላዩ ይህን ይበሉ እንጂ ከብልጽግ ና ሰፈር የሚሰሙ አንዳንድ በራሪ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ሰዎቻቸው ኤርትራን እንደ ተላት መመልከት መጀመራቸው አሳሳቢ ሆኗል።

በቅርብ ጊዜ በየከተማው ያሉ ኤርትራውያን ወደ ስደተኛ ካምፕ እንዲሰበሰቡ በተጨማሪም በኢሳያስ ላይ የኤርትራን መንግስት የሚቃወሙ ፓርቲዎች ተሰብስበው ውሳኔ እንዲሰጡና ጥገኝነት እንዲያገኙ ይደረጋል የሚሉ ሹክስክታዎች በስፋት እየተሰራጩ ነው። የኢሳያስን መንግስት እኔ ጥለዋል የሚለውን ቃል ለምዕራባውያን የገባው አብይ አህመድ በኤርትራ ያለውን መንግስት ለመለወጥ ከሕወሓቶች ጋር ጥብቅ ስራ እየሰራ እንደሚገኝ ተሰምቷል። ይህ ጉዳይ ወዴት እንደሚያመራ ባይታወቅም ኤርትራ የጦር ልምምድ ላይ እንዳለች ታውቋል።

Right
Member
Posts: 4810
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

Re: Eritrea mobilizing for a new war. Report.

Post by Right » 08 May 2023, 08:30

As predicted another major war is looming in the North between Ethiopia and Eritrea. The war may buy some time for the PP regime by distracting the opposition.
Weapons are pouring into Mekele with the blessing of the Ethiopian government.
The war addict PM of Ethiopia soon will be in his uniform.
Time will tell.

Union

Re: Eritrea mobilizing for a new war. Report.

Post by Union » 08 May 2023, 08:41

ኤርትራዊያን ሀማሴኖች በአዲስ አበባ መሳደዳቸው በደንብ ቀጥሏል። እኔ በግሌ ባለኝ መረጃ ከደርግ ግዜ በፊት ጀምሮ የነበሩ የኤርትራዊያንን ሳይቀሩ በየቤታቸው እየገቡ እየወሰዷቸው ነው። በቅርብ ግዜ የመጡት በኦሮሙማው ካድሬ መውጫ መግቢያ አጥተዋል። መስራት እና መንቀሳቀስ አልቻሉም

ሱፕር ማርኬት ውስጥ ለአመታት የሰራ ኤርትራዊ እንደነገረኝ ከሆነ ብዙ ዛቻ እና ማስፈራሪያ እያደረሱበት እንደሆነ ነው።
Right wrote:
08 May 2023, 08:23

Post Reply