Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
-
sun
- Member+
- Posts: 9582
- Joined: 15 Sep 2013, 16:00
Post
by sun » 27 Apr 2023, 20:41
Horus wrote: ↑27 Apr 2023, 14:31

-
Horus
- Senior Member+
- Posts: 42779
- Joined: 19 Oct 2013, 19:34
Post
by Horus » 27 Apr 2023, 20:54
አበረ፣
በTiago እይታ ያቢይ ቡድን ግርማን የገደለው አቢይ አህመድ አማራን ለመውረር ሰበብ ለመፍጠር ነው ብሏል ። አንተ ግን አቢይ ሰውዬውን ያስገደለው ለስልጣኑና አገዛዙ ወደፊት ችግር ይፈጥርብኛል በሚል ስሌት ነው ብለሃል ። አስገዳዩ በውነት አቢይ ከሆነ ያንተ እይታ ይበልጥ ጠንካራ ነው ። አቢይ ሕገ መንግስቱን ጠቅሶ አማራን መውረር ስለሚችል ግርማን ማስገደል አያስፈልገውም ብዬ ስለማምን?
እኔ አንድ እስከሁን ማንም ያልጠየቀው ጥያቄ ልጠይቅ? ግርማ የሺጥላን የግደሉት ያማራ የሽምቅ ተዋጊዎች የማይሆኑት ለምንድን ነው? አማራን ትጥቅ በማስፈታትና የአማራ አማጺ ፋኖና ልዩ ኃይል እንዲታደኑ የሚያደረገው ግርማ የሚመራው ያማራ ብልጽግና አይደለም ወይ? ያማራ ብጽግና የአቢይ አህመድ ዉሃ አመላላሽ መሆኑ እንዳለ ሆኖ ማለቴ ነው? ልክ አንድ የጉራጌ አማጺ ቡድን እርስቱን ቢገድለው እንደ ማለት ነው ።
-
Abere
- Senior Member
- Posts: 15429
- Joined: 18 Jul 2019, 20:52
Post
by Abere » 28 Apr 2023, 11:23
ሆረስ፤
ተገቢ ጥያቄ ነው። በመሰረቱ የአማራ ኃይሎች ከተጠርጣሪነት ዝርዝር ማንም ሊያወጣቸው አይችልም። ግን ማን የበለጠ የተጠርጣሪነት ግምት ይሰጠው የሚለው ነው። እንደጠቀስከው በአማራ ፋኖ እና በሟች መካከል ቆየት ያለ ቅራኔ አለ። በምርመራ ወቅት ከእነ ማን ጋር ወዳጅ ነበር ከእነ ማን ጋር ጠላት ነበር የሚለው ተገቢ ነው። ጥላት ብቻ ሰውን ገድሎ አያውቅም ወዳጅም ገዳይ ነው። " ከወዳጅ መሳይ ጥላት ጠብቀኝ ከጥላቴ እራሴን እጠብቃለሁ " የሚል ብሂል አለ። ለነገሩ አነሳሁት እንጅ እንደዚህ ከፍ ባለ ባለስልጣን ላይ ማን ወንጅል ሊፈጽም ይችላል? በተከታታይ ዕለታት ምንም ምን አይነት ተመሳሳይ ድርጊቶች ተፈጸሙ የሚል ግምት የተሻለ መላ ምት ይሰጣል ባይ ነኝ።
የፋኖ /አማራ ሃይል/ የኋልዮሽ ታሪክ እንደሚጠቁመው በከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ ግድያ ሙከራ አድርገው አልሰማንም። ያንን ለማድረግ የሚያስችል የመረጃ ኔትወርክ፤ ሎጅስቲክ እና ውስጥ አዋቂ ያለቸው አይመስልም። የፋኖ ችሎታ አካባቢያዊ እና የእራስን ደጃፍ ከመጠበቅ ያለፈ አይደለም። ይህን ማድረግ የሚችለው በአብይ አህመድ የሚመራው ቡድን ነው። መረጃ በቀላሉ ያውቃል - ዕቅድ ያወጣል-የዕቅዱ አስፈጻሚ ሰዎች ይሰማራሉ። High Profile crime are not within the reach of Fano/Amhara/force. All high profile crimes committed in the past are linked to Abiy Ahmed. Remember, he is the head spy of TPLF in the past. It is very unfortunate Ethiopia has a "leader" whose career specialty is spy. He is not intelligent but he is a criminal.
ሌላው ሰሞኑን በአማራ ታላላቅ ባለሃብቶች ላይ የተደረገው ሃብት የመንጠቅ ስራ የሚያመላክተው ዐብይ አህመድ በድርጊት ፕሮግራሙ መሰረት በስራ ላይ እንደተጠመደ ነው።
Horus wrote: ↑27 Apr 2023, 20:54
አበረ፣
በTiago እይታ ያቢይ ቡድን ግርማን የገደለው አቢይ አህመድ አማራን ለመውረር ሰበብ ለመፍጠር ነው ብሏል ። አንተ ግን አቢይ ሰውዬውን ያስገደለው ለስልጣኑና አገዛዙ ወደፊት ችግር ይፈጥርብኛል በሚል ስሌት ነው ብለሃል ። አስገዳዩ በውነት አቢይ ከሆነ ያንተ እይታ ይበልጥ ጠንካራ ነው ። አቢይ ሕገ መንግስቱን ጠቅሶ አማራን መውረር ስለሚችል ግርማን ማስገደል አያስፈልገውም ብዬ ስለማምን?
እኔ አንድ እስከሁን ማንም ያልጠየቀው ጥያቄ ልጠይቅ?
ግርማ የሺጥላን የግደሉት ያማራ የሽምቅ ተዋጊዎች የማይሆኑት ለምንድን ነው? አማራን ትጥቅ በማስፈታትና የአማራ አማጺ ፋኖና ልዩ ኃይል እንዲታደኑ የሚያደረገው ግርማ የሚመራው ያማራ ብልጽግና አይደለም ወይ? ያማራ ብጽግና የአቢይ አህመድ ዉሃ አመላላሽ መሆኑ እንዳለ ሆኖ ማለቴ ነው? ልክ አንድ የጉራጌ አማጺ ቡድን እርስቱን ቢገድለው እንደ ማለት ነው ።
---- In a true criminal investigation and criminal justice system, I would say, Abiy Ahmed is the
True Positive Suspect for this horrendous crime, while Amhara forces are
False Positive Suspect.
-
Horus
- Senior Member+
- Posts: 42779
- Joined: 19 Oct 2013, 19:34
Post
by Horus » 28 Apr 2023, 13:49
አበረ፣
ግርማ የሺጥላ በቅርቡ ያደረጋቸው ንግግሮች ደጋግሜ ስሰማቸው ሁለት ቁልፍ ነገሮችን አግኝቻለሁ ፤ አንዱ የንግግሩ ቁጣ ነው ። የሚናገረው ጥልቅ በሆነ ውስጣዊ ቁጣ ነው፣ ንዴት ነው ። አንድ ሰው የሚቆጣውና የሚናደደው ጥቃት ሲደርስበት፣ ሲከዳ ነው። ጥያቄው የግርማ የሺትላ ንዴት ማን ላይ ነው? የሚለው ነው ። በእኔ ግምት አንድም በትህነግ ሌላም በአቢይ ኦሮሙማ መሆን አለበት ።
ሌላው ያየሁት ነገር 'ጠላቶቻችን ' እያለ ደጋግሞ ደጋግሞ ያላት ቃል ነች ያለው አንድ ጠላት አይደለም (የትግሬው ትህነግ ብቻ ነው) እንዳንል! ከትህነግ ሌላ ያማራ ጠላት ማነው? ኦነግ ነው! ሸኔ ነው! አቢይ ነው! አይ ሰውዬው የሚያወራ ስለ ፋኖ ነው እንዳይባል ብዙ ያላቸው ነገሮች ፋኖ ማድረግ የሚችላቸው ነገሮች አይደሉም ። ለምሳሌ በነግዜው አጀንዳ ይሰቱናል ያለው ...
ይህን ሁሉ ስመለከት ግርማ የሺጥላና አቢይ አህመድ ቅራኔ ውስጥ የነበሩ ይመስለኛል ። ስለሆነም ግርማ የአማራ ብልጽኛ መሪ ሆኖ ከወጣ ያማራ ፒፒን ከቁጥጥር ውጭ ያደርግብኛል ብሎ የገደለው ነው የሚመስለኝ ። ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ ይባላልና ግርማ የሺጥላ መጨረሻ ላይ መንዜነቱ ላይ ተመልሶ ሊሆን ይችላል ።
አሁን ትልቁ ቁም ነገር የዚህ ግድያ ውጤት ምን ሆነ? የሚለው ነው ። ሁሉ ነገር ኮንሲኩዌንስ አለው ። አጠቃላይ በሚባል ደረጃ በአቢይ ገዳይነት ሕዝቡ እየተስማማ ነው ። ይህ ብሄራዊ ያመለካከት ድምዳሜ ለዲክታተሩ ግዙፍ ግዙፍ ኪሳራ ነው ። ዋናው ነገር እንደኛ ያለው ተቃዋሚ ባቢይ ገዳይነት መስማማታችን አይደለም ። የራሱ አሽከሮችና ደጋፊዎች የግርማ ዕጣ ፈንታ እንደ ሚጠብቃቸውና አቢይ አህመድ ልክ የአንድ ማፊያ ቦስ እንደ ሚያደርገው ተቃዋሚውን አለምህረት እንደ ሚያስገድል እያወቁ የሱ አሽከር ሆነው ለሚኖሩት ግዙፍ የሳይኮሎጂና የህልውና ትራማ ነው ። ስለዚህ ይህ የማፊያ ድርጅት ግልጽ ቀውስ ውስጥ እየገባ ነው ።
በሌላ በኩል የግርማ የሺጥላ መገደል እራሱ ያማራ ፒፒን ከስሩ የሚያምሰው ጉዳይ ነው። ማለትም ያማራ ፒፒ ወይ ካማራ ሕዝብ ጋር ቆሞ የሕዝብ ፍቅር የለው፣ ወይ ክወረሞ ጋር ቆሞ ያማራን ጥቅም አያስጠብቅ። ትንሽም ትሁን ወረሞን ሲገዳደር ባቢይ የሚገደል ከሆነ የግርማ መገደል ያማራና ወረሞ ፒፒዎችን የባሰ የሚያራርቅ እንጂ የዲክታተር አቢይን ችግር የሚፈታ አይሆንም ።
ባንድ ቃል አቢይ ድርማን ገድሎ ከሆነ የደደብ ስራ ነው የሰራው! በሁለት በኩል ኪሳራ ስለደረሰበት !
-
Abere
- Senior Member
- Posts: 15429
- Joined: 18 Jul 2019, 20:52
Post
by Abere » 28 Apr 2023, 14:10
ሆረስ፤
አሳማኝ ትንታኔ ነው የሰጠኸው። ሟች በአደባባይ ለአማራ ህዝብ የሚለውና በኦነግ መራሹ የብልጽግና ዝግ ስብሰባ ላይ ያለው አቋም ምናልባት አንድ ላይሆኑ ይችላሉ። እንደማስታውሰው በቅርብ አንድ ብ አደን ለሽመልስ አብድሳ የቁሞ ቀር ስድብ ግብረ-መልስ ሰጥተው ነበር። በዚያ ግብረ-መልስ ላይ ይህ ሰው ሚና አለው የሚባል ነገር ነበር ምንም እንኳን በኋላ ትጥቅ ማስፈታት ላይ ከጅ/ል አበባው ታደሰ ጋር እየሰራ ነው የሚባል ዜና ቢኖርም። ለማንኛውም በብ አደን ዘንድ ከፍተኛ ተጽ እኖ ፈጣሪ እና የብ አድን አመለካከት ከህዝብ ጋር እየሆነ ከመጣ አብይ ይህ ሊያስፈረው ይችል ነበር። ሆኖም ግን ዐብይ የፈጸመው አጥፍተህ ጥፋ ነው - አንተም ጠቅሰኸዋል። 1ኛ) ማንኛውም ብ አደን ከእንግድህ በስጋት የሚኖር እንጅ የአብይ ደጋፊ ላይሆን ይችላል - ወይ ከህዝብ ይወግናል ወይ ለይስሙላ ይሰራል 2ኛ) የኢትዮጵያ ህዝብ አብይ አህመድን ነፍስ አጥፊ የሚረሽን (ያለ ዕድሜያቸው የሚያበላሽ ቤተሰብ የሚበትን) ከመንግስቱ ሃይለማርያም የከፋ ራሻኝ ይሆናል - ማንም አያምነውም። ብቻውን እያጨበጨበ ብቻውን ይገኛል። የአማራ ህዝብ ከሰው አይቆጥረውም። ማንን እንደሚያስተዳድር ይገርማል።
"ስልጣን" ሲወጣ መግደል የመሸነፍ ምልክት ነው እንዳለው አሁን በድርጊቱ መሸነፉን እያረጋገጠልን ነው።አሁንስ ቀሪዎች ባለ ስልጣን ነን ባዮች ምን ትምህርት ወሰዱ? ወይስ እባብ መርዙን ከእርቀት እንደረጨባት አይጥ ወይም ወፍ አይናቸውን ቁልጭቁልጭ እያደረጉ ተራቸውን ይጠባበቃሉ? መግለጫ አውጡ ሲባሉ በፍርሃት እየተሽመደመዱ ያነባሉ?