የጦርነት መዘዝ ቀላል እንደልሆነ በመጠኑ ስለሚገባኝ እሄ ጦርነት መካሄድ እንዳሌለበት ከጦርነቱ በፊት በተደጋጋሚ ፅፍያለሁ ።ለማሳያ ያክል ጦርነቱ ሊጀመር ሁለት ወር እና ሁለት ቀን ሲቀረው የፃፍኩትን አያይዣለሁ።
በአጭሩ ጦርነቱ ውስጥ መግባት አጥፍቶ መጥፋት ነው ቢዬ ነበር።
ከዚያ በኃላ ስለጦርነቱ አንድም ቃል አልፃፍኩም ።
ከጦርነቱ በፊት ያልተሰማን ጦርነት እየተካሄደ እንሰማለን ብሎ ማሰብ ዘበት ስለነበር ብዙም ላለመቀባጠር ነው።
ነገር ግን በተለይ መደበኛው ጦርነት ከተጠናቀቀ በኃላ
የተወሰኑ በጣም የሚገርሙኝ ነገሮች አሉ።
ወደሚገርሙኝ ነገሮች ከመግባቴ በፊት ጦርነትን በተመለከተ የኔን መሪህ ላስቀምጥ ። እኔ በሀገር ውስጥ ያሉ አልመግባባቶችን በተቻለ መጠን በሰላም መፈታት የዛሬም ሆነ የትላንት ቋሚ እምነቴ ነው። እሄ እምነቴ በነገሮች እና በቦታ ልዩነት አይቀያየርም።
ወደ ነጥቤ ስመለስ፦
መደበኛ ጦርነትን ለማሸነፍ የሰው ኃይል ብዛት እና ጥራት እንዲሁም የመሳሪያ ጥራት እጅግ ወሳኝ ነው።በዚሁ መሰረት የመደበኛው ጦርነት አልቋል።
ቀጥሎ የሆነው እና እየሆነ ያለው የደፈጣ ውጊያ ነው።
የደፈጣ ውጊያ ላይ ከኃይል ሚዛን በላይ የፖለቲካ ስራው እና የደፈጣ ውጊያው የሚካሄድበት አከባቢ ያለው የህዝብ ድጋፍ እጅግ ወሳኝ ነው።
አሁን ጥያቄው እዚህ ላይ ነው።
ትግራይ ውስጥ ከሚካሄደው ጦርነት ጋር ተያይዞ የኤርትራ ሰራዊት እና የአማራ ልዩ ኃይል መኖሩ የትግራይን ህዝብ ከፌደራል መንግስቱ ተቃራኒ እንደሚያቆመው እና የጦርነቱን ውጤት እንደሚያወሳስበው ግልፅ ነው። በአጭሩ የጦርነቱን አድማስ ከድርጅት ወደ ህዝብ ያሰፈዋል ።ጦርነቱ የቡድኖች ሳይሆን የህዝብ ከሆነ ደግሞ የጦርነቱ እድሜ ከማራዘም በላይ እልቂቱም እጅግ አሰቃቂ ይሆናል።
ከዚህ በተጨማሪ ከጦርነቱ በፊት በኤርትራ እና በትግራይ መካካል እንዲሁም በአማራ ክልል እና በትግራይ ክልል መካከል የነበረውን ንትርክ እናውቃለን። ይህም ከጦርነቱ በኃላ ለተፈጠረው ቀውስ የራሱ ድርሻ አለው።
በአጭሩ ከነዚህ ጋር በተያያዘ ያሉት ኃይሎች በአከባቢው መቆየታቸው ነገሮችን ከሚገባው በላይ ከማወሳሰብ ውጪ በአከባቢው ሰላም ለማምጣት ምንም አይፈይዱም።
እነዚህ ኃይሎች ያላቸው ጥያቄ መስተናገድ ያለበት በሀገሪቷ ህግ እና በዓለም አቀፍ ህግ ብቻ መሆን አለበት።
አለበለዚያ ከቀውሱ መውጫ መንገድ አይገኝም።
ሌላው ጠቅላይ ሚንስትር አቢይ ደጋግመው እንዳሉት ትግራይ ውስጥ የሚካሄደው ጦርነት የተወሰኑ የህወሃት ሰዎችን በቁጥጥር ስር በማዋል የህግ በላይነትን ለማረጋገጥ የሚደረግ ጦርነት ነው። ከዚህ አንፃር መንግስት ከሌሎች የህወሃት ሰዎች ጋር የማይደራደርበት ምክንያት አይታየኝም ነበር። ነገሮች እንዴት ጠቅላይ ሚንስትሩ መጀመሪያ ሲያቀርቡልን ከነበረው ጥቂት የህወሃት አመራርን ከመቆጣጠር ህወሃትን በአሸባሪነት ወደ መፈረጅ እንደደረሰ አልገባኝም። በእርግጥ መንግስታችን ስልጣን ከያዘ በኃላ የሚያደርጋቸው ብዙ ነገሮች እየገቡኝ አልነበረም። እሄም ያው ነው ለማለት ነው።
በአጭሩ በአከባቢው ሰላም ለማስፈን ድርድርን ሙሉ በሙሉ ተፀይፎ መነሳት በመሪህ ደረጃ የተሳሳተ ነው።
ባይሆን በድርድሩ ውስጥ ቅድሚያ ሁኔታ ታስቀምጣለህ እንጂ ድርድርን ሙሉ በሙሉ አልቀበልም ማለት በአሁኑ ጊዜ የዓለም አሰራር አይደለም። ሰላምም አያመጣም። የሰላም ሰውም አያደርግህም።
ስለዚህ
1 የአማራ ልዩ ኃይል እና የኤርትራ ሰራዊት ከአከባቢው መልቀቅ የኢትዮጵያ ህግ የሚያስገድደው ነው።
አከባቢው ላይ ሰላም ለማስፈንም እጅግ ወሳኝ ነው።
ይህንን እርምጃ መውሰድ በአከባቢው ሰላም ማምጣት ብቻም ሳይሆን ሁለቱንም ኃይሎች በእጅጉ ይጠቅማል።
የፌደራል መንግስቱን እና የትግራይን ህዝብ ደግሞ በአጅጉ ይጠቅማል ። በእርግጥ መንግስትም የኤርትራ ሰራዊት ከይግራይ እንደሚወጣ ገልፀዋል። የኤርትራ መንግስትም ተስማምቷል። እሄንን ህደቱን ማፋጠን እና ግልፅነት በለው መልኩ መፈፀም እጅግ ወሳኝ ነው።
2 የፌደራል መንግስቱ የሰው ኃይል ካነሰው በሀገራችን ካሉት ከተለያዩ ክልል ልዩ ኃይሎች በመውሰድ ተጨማሪ ስልጠና ከሰጠ በኃላ በፌደራል መንግስት እዚ ( በመከላከያ ወይም በፌደራል ፖሊስ ) ስር በማስገባት መጠቀም ይችላል ።
ከዚያ ውጪ አሁን በለው የሀገራችን የብሄር ፖለቲካ ጡዘት የአንድን ክልል ልዩ ኃይል በሌላ ክልል ውስጥ መጠቀም የእርስ በራስ ግጭት ከመቀስቀስ በምንም አይተናነስም።
3 አሁን በለው የሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ በየትኛውም አከባቢ ያሉትን ግጭቶች መንግስት ለመፍታት ቅድሚያ መስጠት ያለበት ለድርድር እና ለውይይት ነው።
ከዚያ ውጪ በመሪህ ደረጃ ውይይትን አልቀበልም ማለት የአሁኗ የአለማችን አሰራር አይፈቅድም።
Please wait, video is loading...