Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Axumezana
Senior Member
Posts: 19179
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

አብይ፥ ከአሜሪካ፥ ጋር ፥ እያደረገ፥ያለውን፥መቀራረብ፥ እንዲገታ፥ ኢሳያስ፥በአንዳርጋቸው፥ በኩል፥ የላከው፥ ልመና፤

Post by Axumezana » 13 Mar 2023, 17:15

) በዲፕሎማሲ ዘርፉ
ትልቅ ጥንቃቄ የሚያስፈገው ዘርፍ ነው። በአለም ላይ የተፈጠረው አዲስ የሃይል አሰላለፍ፣ በተለይ አሜሪካንን ብቸኛ ለእለ ሃያል ሃገር ያደረገው ዘመን ማብቃት፣ አሜሪካኖችን የሚይዙትና የሚጨብጡትን እያሳጣቸው ነው። የአፍሪካ ቀንድ አንዱ ከተጽኖአቸው ውጭ እንዲወጣ የማይፈልጉት ስትራተጂክ ቀጠና ነው። ከወያኔ ጋር የሙጥኝ ብለው የተጣበቁበት አንዱ ምክንያት ወዳጃቸው ወያኔ ከኢትዮጵያ ፖለቲካ ከወጣ በዚህ ቀጠና በሎሌነት የሚያገለግለን አካል አይኖረንም የሚል ስጋት ነው። የአሜሪካኖች አካሄድ ኢትዮጵያን በኢኮኖሚና በዲፕሎማሲ መስኮች እየጨመቁ ወያኔን በኢትዮጵያ ውስጥ ተጽእኖ ፈጣሪነቱ እንዲቀጥል ማድረግ ነው።
አሜሪካኖች በእርዳታ ስም የሚሰጡትን ገንዘብ ለመልቀቅ፣ ከአለም አቀፍ ተቋማት ኢትዮጵያ ብድር እንድታገኝ ወደ አገዋ እንደትመለሰ ቅደመ ሁኔታ ማስቀመጣቸው አይቀርም። ይህ ቅድመ ሁኔታ ደግሞ ወያኔን እንደ ድርጅት ማዳን ነው። ወያኔ የሚፈልገውን በተለይ ወልቃይትን በወያኔ አገዛዝ ስር መልሶ እንዲገባ ህገ መንግስቱን እያጣቀሱ መሞገት ነው። በኢትዮጵያና በኤርትራ መሃከል ያለው ግንኙነት እንዲሻክር ነው። ቢቻላቸው የኤርትራን መንግስት ቀድሞ ሲያደርጉት ወደነበረው አፈና ከበባ ውስጥ ማስገባት ነው። ኤርትራ ከሩሲያና ከቻይና ጎን በመቆም ለወሰደቻቸው አቋሞች ዋጋ እንድትከፍል ማድረግ ነው። በመጨረሻም ትልቅ ስትራተጂያዊ ጠቀሜታ ያላትን ኤርትራን መንግስቷን በመጣል የአሜሪካ አሻንጉሊት በሆነ መንግስት መተካት ነው።

የሚያሳስቡ ነገሮች እየታዩ ነው። አሜሪካኖች የሚፈልጉትን በመስጠት ኢትዮጵያ ከገባችበት ሁለንተናዊ ቀውስ ፋታ ታገኛለች በሚል የተሳሳተ ስሌት ሊሰራ የሚችል ነገር የከፋ አደጋ ይዞ ሊመጣ እንደሚችል መታወቅ ይኖርበታል። በአለም ላይ የተፈጠረው በሁለት የተከፈለው ጎራ፣ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚሆነውን ሁሉ አሜሪካኖች በከፍተኛ ትኩረት እንዲከታተሉት እንዳደረገ ሁሉ የሩሲያውና የቻይናውም ጎራ ይከታተሉታል።

ቻይና እና ሩስያ በተከታታይ ምእራባውያኑ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ውስጥ የኢትዮጵያ ጉዳይ እንዲነሳና በኢትዮጵያ ላይ ጎጂ ውሳኔ እንዲወሰን የተደረገውን ተደጋጋሚ ጥረት ኢትዮጵያን ወግነው አክሸፈዋል። ኤርትራ በክፉ ቀን ከኢትዮጵያ ጎን በመቆም መስዋእተነት ከፍላ አለኝታነቷን አሳይታለች። እነዚህ አካላት የኢትዮጵያ መንግስት ውለታቸውን ዘንግቶ የአሜሪካ ጉዳይ አስፈጻሚ ወደ መሆን ሲሄድ ዝም ብለው የሚያዩት አይሆንም። የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ አንዱን መምረጥ ይኖርበታል። አሜሪካኖች የአጭርና የረጅም ጊዜ ጥቅሞቻቸውን አስልተው ኢትዮጵያ እንድትፈጽም የሚፈልጓቸውን ነገሮች መፈጸም ወይም አሜሪካኖች የሚጠይቋቸውን ፍትሃዊ ያልሆኑ ጥያቄዎች አልቀበልም በማለት መከፈል የሚገባውን መስዋእትነት ለመክፈል መዘጋጀት።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ እየሄደበት ያለው መንገድ አሳሳቢ ነው። ኢትዮጵያ በዲፕሎማሲ ስራዋ ሩቅ ካሉ ሃገሮች ይልቅ በአካባቢዋ ካሉት ጎረቤት ሃገሮቿ ጋር የሚኖራት መልካም ግንኙነት ዘለቄታ ጥቅሟን የሚያስከብር መሆኑን ማወቅ ይኖርባታል። ለአሜሪካኖች ተብሎ ከየትኛውም ሃገር ህዝብ በላይ የኢትዮጵያ ወዳጅ ከሆነ ከኤርትራ መንግስትና ህዝብ ጋር መቃቃር ለኢትዮጵያ ትልቅ ጉዳት የሚያስከትል ነው።

ኤርትራ አሜሪካ ብቸኛዋ ልእለ ሃያል ሃገር በነበረችበት ወቅት ተገልላ ስትኖር ከነበረበት አፈና የሚያወጣ አዲስ የአለም ስርአት ተፈጥሮላታል። እሷም ጥቅሟን ግምት ውስጥ በማስገባት አዲስ በተፈጠረው የአለም ጎራ ውስጥ የወሰደቻቸው በብልሃት የተሞሉ አቋሞች ትልልቅ ሃያላን ወዳጆች እንድታፈራ አድርጓታል። ዛሬ አሜሪካኖች ኤርትራን ከዚህ ቀደም ሲያደርጉት እንደነበር ማድረግ የሚችሉበት ሁኔታ የለም። የኢትዮጵያ ዲፕሎማሲ ይህን ሃቅ ግምት ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።

ዲፕሎማሲያችን አሜሪካ ላይ መለጠፍ ሳይሆን ከአሜሪካ ተጽእኖ እንዴት መላቀቅ ይቻላል በሚል ስሌት መመራት አለበት። ኢትዮጵያ በጦርነቱ ወቅት ከአሜሪካን ተጽእኖ ራሷን ለማላቀቅ ተፈጠሮላት የነበረውን እድል በማባከኗ፣ ወደፊት የምናየው ይሆናል፣ ብዙ ዋጋ ትከፍልበታለች። የበቃ እንቅስቃሴ በአጭር እንዲቀጭ በመደረጉ የምናዝንበት ቀን ይመጣል።

ሃቁ በአሜሪካ ተጽእኖ ስር ወድቀው የበለጸጉ፣ ሰላም ያገኙ፣ ዴሞክራሲያዊ ስርአት የገነቡ፣ የህዝባቸውን መብቶች ያስከበሩ ታዳጊ ሃገሮች ቀርቶ አንድም ሃገር የለም። ቢኖሩ ኖሮ የወይኔዋ ኢትዮጵያ አንዷ ትሆን ነበር። ይህን ሃቅ አገናዝቦ ብልሃትና ጥበብ በተሞላው መንገድ የዲፕሎማሲ አቅጣጫቻን ማስተካከል ይገባል። ይህ ጉዳይ ራሳቸው አሜሪካኖቹ እንደሚሉት “እንደሚናገሩት ቀላል እንዳልሆነ” ይገባኛል። ከባድ ያደረግነው እኛው ራሳችን መሆናችንን መገንዘብ ግን ይገባናል።

ስላነበቡ አመሰግናለሁ
አንዳርጋቸው ጽጌ