የቃቄ ወርድወት፡ በአለም ላይ የመጀምሪያዋ የጉራጌ ሴቶች መብት ተሟጋች! እንቁ ምሳሌያችን ! እንኳን ለሴቶች ቀን አደረሰን !!
የቃቄ ወርድወት! አበጋዝ ቃቄ ሴት ወለደ! በጉራጌ ባህል የመጀምሪያ ወይም አንድ ዝነኛ ልጅ ባባቱ ይጠራል ! የቃቄ ወርድወት ማለት ያበጋዝ ቃቄ ሴት ልጅ ወይም ወለቱ ማለት ነው ። ለወንድ ወልድ፣ ወልድ፣ አርድ ስንል ለሴት ወልድወት፣ ወርድወት (ወልዲት) እንላለን ! የዚች ጀግኒት ስም ትርጉም ያ ነው ! ለምሳሌ ድሮ አንድ አባት ሰንበቶ ከተባለና የመጀመሪያ ልጁ ወንድ ከሆነ የሰንበቶ ወርድ (ወልደ ሰንበቶ) ይባል ነበር ! የልጁ ስም ደሞ ቆሬ ከነበረ አባትየው ሰንበቶ አባ ቆሬ ይባል ነበር!