Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum


Abere
Senior Member
Posts: 15441
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: ኦርቶዶክስ የቤተክርስቲያኗን መፍረስ በቀጥታም በተዘዋዋሪም የደገፉትን ቁርባንና ፍታት መከልከል አለባት!

Post by Abere » 22 Feb 2023, 13:24

Selam,

ትንሽ ፈገግ የሚያደርግ አነጋገር ነው። መጀመርያ ሰዎቹ እኮ ቁርባን እና ፍታት የሚያስፈልጋቸው አይደሉም። ጴንጤ ወይም ፕሮቴስታንት ናቸው።ለእነርሱ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ማፍረስ በሰው ቁስል እንጨት እንደ መስደድ ነው። በሙጀሌ እግሩ እኮ ቤተ መቅደስ ያረከሰው ምድረ ውሃቢስት እና ጴንጤ ቁስጤ ነው እንጅ ኦርቶዶክስ ምዕምን አይደለም። ጉድ እና ጅራት ወደ ኋላ ነው የእነ አካለወልድ ሞገስ ጉድ አደባባይ ውስጥ አዋቂዎች እየዘከዘኩት ነው።
Selam/ wrote:
22 Feb 2023, 01:39

Sam Ebalalehu
Member
Posts: 3639
Joined: 23 Jun 2018, 21:29

Re: ኦርቶዶክስ የቤተክርስቲያኗን መፍረስ በቀጥታም በተዘዋዋሪም የደገፉትን ቁርባንና ፍታት መከልከል አለባት!

Post by Sam Ebalalehu » 22 Feb 2023, 14:15

የኔ ሀይማኖት ካንተ ይሻላል ፉክክር የ ድንቁርና መግለጫ ነው። ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ኢትዮጵያዊውያን የተወለዱበት አከባቢ ነው ሃይማኖታቸውን የሚወስነው። ምርጫ የላቸውም። በአለም በጠቅላላ። ሳውዲ አረቢያ ከተወለድክ እስላም ነህ Italy ብትወለድ ካቶሊክ ክርስቲያን ነህ። ጂኦግራፊ ነው የስውን ሀይማኖት የሚወስነው በአብዛኛው። የ አቢይ ፔንቴኮስታል ሀይማኖት መከተል ለምሳሌ በምርጫ የተደረገ ነው። በኔ ግምት ከ አንድ ፐርሰንት አይበልጡም የምርጫ ሃይማኖተኞች ። በጣም በአብዛኛው የጂኦግራፊ ምርኮኛ ነው።

Selam/
Senior Member
Posts: 17888
Joined: 04 Aug 2018, 13:15

Re: ኦርቶዶክስ የቤተክርስቲያኗን መፍረስ በቀጥታም በተዘዋዋሪም የደገፉትን ቁርባንና ፍታት መከልከል አለባት!

Post by Selam/ » 22 Feb 2023, 17:55

በኔ ግምት አብዛኛው የብልፅግና አባል ኦርቶዶክስ ነው፣ አንዳንዱ በስም ብቻ ቢሆንም። ቤተክርስቲያኗ ስትፈርስ አንገቱን አሸዋ ውስጥ ቢቀብርም፣ ሲሞት ስላሴና ገብርኤል እንዲቀበር ነው ምኞቱ። ድሮ የደርግ አባሎች ሶሻሊዝም ወይንም ሞት ቀኑን ሙሉ ሲሉ ውለው፣ ለሊት ለሊት ጋቢ ለብሰው ከሚስቶቻቸው ጋር ቤተክርስቲያን ይሳለሙ ነበር አሉ።

Post Reply