Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Axumezana
Senior Member
Posts: 19180
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

ጠቅላይ፥ሚኒስቴር፥ አብይ፥ጥሬ፥ ስንዴ፥ መላክ፥ይሻላል፥ወይስ፥ ዱቄት፥ፓስታ፥ መኮሮኒ?

Post by Axumezana » 21 Feb 2023, 16:08

መልካም፥ ጅምር፥ ነው፥ እያልኩ፥ የሚከተሉትን፤ ልበል፤

(1) ስንዴን፥ እንደግብአት፥የሚጠቀሙ፥ እንዱስትሪዎች፥ በስንዴ፥ እጥረት፥ ችግር፥ ላይ፥ ከወደቁ፥ ብዙ፥ አመታት፥ አልፏል፥ ታድያ፥ እሴት፥የተጨመረበትን፥ ምርት፥ በጥራት፥ አምርቶ፥ ኤክስፖርት፥ ማድረግ፥ ይሻላል፥ ወይስ፥ ጥሬውን፥ ስንዴ?
(2) ለመሆኑ፥ ጥሬ፥ ስንዴ፥ ኤክስፖርት፥ ሲደረግ፥ አዋጭ፥ ነው? ካልሆነ፥ ግን፥ የአንድ፥ ሰሞን፥ ወሬ፥ ሁኖ፥ ይቀራል፤

(3) የመሬት፥ ስርአቱ፥ ላይ፥ ለውጥ፥ ተደርጎ፥ ትላልቅ፥ አርሻዎችን፥ ግለሰቦች፥ በቀላሉ፥ ማግኘት፥ እንዲችሉ፥ ቢደረግ።






Noble Amhara
Senior Member
Posts: 13728
Joined: 02 Feb 2020, 13:00
Location: Abysinnia

Re: ጠቅላይ፥ሚኒስቴር፥ አብይ፥ጥሬ፥ ስንዴ፥ መላክ፥ይሻላል፥ወይስ፥ ዱቄት፥ፓስታ፥ መኮሮኒ?

Post by Noble Amhara » 21 Feb 2023, 16:20



መንግስት በስንዴ ምርት ላይ ከፍተኛ ለውጥ አምጥቼ ለኤክስፖርት ደርሻለሁ ቢልም የሃገር ውስጥ ፋብሪካዎች ግን በምርት አጥረት እየተቸገሩ እንደሚገኙ እየገለጹ ነው፡፡
በሃገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች የስንዴ ምርት በብዛት እንዲመረት ለማድረግ ጥረት እየተደረገ ሲሆን ለኤክስፖርት የሚሆን ስንዴ እንዲያዘጋጁም ክልሎች ኮታ እንደተጣለባቸው ሲነገር ነበር፡፡

በቅርቡም ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በተገኙበት ከኦሮሚያ ክልል የስንዴ ምርትን ወደ ውጭ መላክ መጀመሩ አይዘነጋም፡፡
ይህ በሆነ ማግስት ግን የዱቄት፣ፓስታና መኮሮኒ አምራች ፋብሪካዎች የስንዴ ምርት እጥረት ገጥሞናል፤በዚህም ስራ ለማቆም ተገደናል ብለዋል፡፡

የዱቄትና የዱቄት ውጤቶች አምራቾች ማህበር ፕሬዝዳንት አቶ ሙሉነህ ለማ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፤ ስንዴ በአሁኑ ወቅት ኮንትሮባንድ ሆኗል፤ማንም እንደፈለገ መግዛትም ሆነ መሸጥ አይችልም ብለዋል፡፡

መንግስት ለኤክስፖርት የሚሆን ስንዴን ለማግኘት ሲል ዩኒዮኖች ብቻ እንዲገዙ ፈቀደ፣ለዱቄት አምራቾችም በዩኒዮኖች በኩል ታገኛላችሁ ተባሉ፣በኋላም 12 ባለሃብቶች ተመርጠው ወደ ስራ ገቡ፣ዱቄት አምራቾች ግን ስንዴ ሊያገኙ አልቻሉም ብለዋል፡፡

ይህ ችግር ከተፈጠረ 2 ወራትን አስቆጥሯል የሚሉት አቶ ሙሉነህ፣አምራቾች በእጃቸው ያለችውን ስንዴ እየቆጠቡ ሲጠቀሙ ቆይተው አሁን ላይ ስራ ማቆም ደረጃ ላይ መድረሳቸውን ገልጸዋል፡፡በዚህም በዳቦ ላይ የሚስተዋለው ጭማሬ እንዳለ ሆኖ የ1 ኪሎ መኮሮኒ ዋጋ ከ40 ብር ወደ 80 ብር ከፍ እንዲል አድርጎታል ነው የተባለው፡፡

እንደ አቶ ሙሉነህ ገለጻ በአሁኑ ወቅት ስንዴ እንደ ኮንትሮባንድ ተቆጥሮ በየኬላዎች በፍተሻ እየተያዘ ነው፡፡ በዚህም አምራቾች ገዝተው መተቀም አይችሉም፡፡ በአንዳንድ አካባቢዎች መጋዘን ላይ ስንዴ የተገኘባቸው ዱቄት ፋብሪካዎችም ሆነ ነጋዴዎች በህገ ወጥ መንገድ ግብይት ፈጽማችኋል በሚል ወከባ እየደረሰባቸው እንደሚገኝም አንስተዋል፡፡

በመሆኑም ከሁሉም ነፊት የሃገር ውስጥ ፍላጎትን ማሟላት ይቀድማልና ችግሩን ለመፍታት መንግስት ትኩረት እንዲሰጥ አቶ ሙሉነህ ጠይቀዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

የካቲት 14 ቀን 2015 ዓ.ም

Axumezana
Senior Member
Posts: 19180
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: ጠቅላይ፥ሚኒስቴር፥ አብይ፥ጥሬ፥ ስንዴ፥ መላክ፥ይሻላል፥ወይስ፥ ዱቄት፥ፓስታ፥ መኮሮኒ?

Post by Axumezana » 21 Feb 2023, 16:37

የስንዴ፥ ምርቱ፥ እስካለ፥ድረስ፥ የኤሌትሪክ፥ ሀይል፥ምንጭም፥ በተነፃፃሪ፥ ርካሽ፥ ስለሆነ፥የምግብ፥እንዱስትሪው፥ በጥራት፥ አምርቶ፥ ኤክስፖርት፥ቢያደርግ፥ መልካም፥ነው። ኤርትራ፥ ራሷ፥ ጥሩ፥ገበያ፥ ትሆናለች፤

DefendTheTruth
Senior Member
Posts: 13243
Joined: 08 Mar 2014, 16:32

Re: ጠቅላይ፥ሚኒስቴር፥ አብይ፥ጥሬ፥ ስንዴ፥ መላክ፥ይሻላል፥ወይስ፥ ዱቄት፥ፓስታ፥ መኮሮኒ?

Post by DefendTheTruth » 21 Feb 2023, 17:00

የምሻለዉ የነበረዉ ዱቄት ወይም ፓስታ አድርጎ ማለክ ነዉ፣ ነገር ግን ወሬ ማሳለቅ እንጂ መስራት ንቀት በሆነበት አገር ምን ሌላ አማራጭ አለ?

የቡልዶዘር ዘመን!

Post Reply