Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42814
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

መዓዛ አሸናፊና ሰለሞን አረዳ እነማን ናቸው?

Post by Horus » 17 Jan 2023, 23:48

ስለነዚህ ሁለት ሰዎች ታሪክ ትንሽ ጉግል አድርጌ ነበር። ሰለሞን አረዳ በትምህርት ዝግጅቱ ጠንካራ ነው ። አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በሕግ ባችለር አለው። ሃርቫርድ ሎው እስኩል ማስተርስ ኦፍ ሎው አለው። ኬኔዲ እስኩል ኦፍ ገቨርንመንት ፓብሊክ አድሚኒስትሬሽን ተምሯል። ስለዚህ በተግባር ያለውን ችግር ባላውቅም በትምህርት ዝግጅቱ በጣም ጥሩ ነው።

በሌላ በኩል መዓዛ አሸናፊ የሱፕሪም ኮርት ፕሬዚዳንት የሚያደርጋት የህግ ትምህርት ብቃት የላትም ። አቢይ አህመድ እንዳለው የሴቶች መብት ተሟጋች አክቲቪስት እንጂ የሕግ ሊቅ አይደለችም ። ለምሳሌ ከታች ዛሬ የጻፈችውን ተመልከቱ ። ዛሬ ፓርላማው በመአዛና ሰለሞን ቦታ ቴዎድሮስና አበባን ሾመ ማለት ሲገባት መአዛና ሰለሞንን የሚወክሉ ቴዎድሮስና አበባን ሾመ ትላለች! እንዴት ብላ ነው ያገሪቱ መጨረሻ ከፍተኛ ዳኛ የሆነችው?!!!

"On 1 November 2018, Meaza appointed unanimously by HoPR as the President of the Supreme Court, being the first woman in the cabinet of Prime Minister Abiy Ahmed.[7] After serving four years, she resigned that position with vice president Solomon Areda on 17 January 2023. The Ethiopian parliament appointed Tewdros Mihret as the president and Abeba Embiale as deputy president of the Supreme Court on behalf of Meaza and Solomon respectively.[8]"


https://en.wikipedia.org/wiki/Meaza_Ashenafi

Solomon Areda
https://en.wikipedia.org/wiki/Solomon_Areda


Post Reply