ከዕለታት አንድ ቀን አንዲት ሴት ነበረች
ጦቢያ የተባለች፤
ውሽማዋ በዝቶ ብዙ የወለደች
ከብዙ ተኝታ ብዙ ያዳቀለች፤
ፍሬ ተዘርቶላት እንክርዳድ ያለማች
ገለባ ያፈራች፤
አሪቲ ኮሰረት በመርዝ የቀመመች
መለሎ ለግላጋን በእበት የለወጠች፤
ዝሙት ዳንኪረኛን ጀግና ያስመሰለች
ጦቢያ የምትባል አንዲት ሴት ነበረች፤
ሃቅ ወሽሟት ጉራን ያረገዘች
አለም ባሏ ሆኖ ጎሣን የወለደች
ጦቢያ የምትባል አንዲት ሴት ነበረች፤
በተኚዎች ብዛት ክብሯን ያቀለለች
በዝጉርጉር ሆዷ በልጅ ያልታደለች፤
ዘውጎች ወልዳ ወልዳ መክና የቀረች
ጦቢያ የምትባል በእጅጉ ያዘነች፤
አንዲት ሴት ነበረች ።
ሆረስ ዘኢትዮጵያ
ኤፕሪል 1995
(ከማስታወሻዎቼ ማህደር)
አንዲት ሴት ነበረች
Last edited by Horus on 17 Jan 2023, 14:05, edited 1 time in total.
Re: አንዲት ሴት ነበረች
አፋፍ ላፋፍ ስሄድ አገኘሁ ሚዳቋ፣
ጅራቷን ስይዛት አይኗ ፍጥጥ አለ!
(ይህ የሆያ ሆዬ ቤት የሚባለው የግጥም ዝርያ ወይም ዣንራ ነው!)
ሆያ ሆዬ ቤት አይመታም! ቤት የሚመታ ስንኝ እንኳ ቢሆን ...
ግጥምኮ አይደለም ሃ በ ሃ ቢሳካ
ዐረፍተ ነገሩ ስሜትን ካልነካ!
ብሎን ነበር ሊቁ መንግሥቱ ለማ።
የሰለቸን ነገር ቢኖር ያላዋቂ ብልግና ካድሬ ንፍጥ ልቅለቃ ነው!
ጅራቷን ስይዛት አይኗ ፍጥጥ አለ!
(ይህ የሆያ ሆዬ ቤት የሚባለው የግጥም ዝርያ ወይም ዣንራ ነው!)
ሆያ ሆዬ ቤት አይመታም! ቤት የሚመታ ስንኝ እንኳ ቢሆን ...
ግጥምኮ አይደለም ሃ በ ሃ ቢሳካ
ዐረፍተ ነገሩ ስሜትን ካልነካ!
ብሎን ነበር ሊቁ መንግሥቱ ለማ።
የሰለቸን ነገር ቢኖር ያላዋቂ ብልግና ካድሬ ንፍጥ ልቅለቃ ነው!