Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 15445
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

ለዘመናት ለነጻነታችሁ በፅናት በመቆም ከባድ መስዋዕት በመክፈል እርስት ማንነታችሁን ላስመለሳችሁ ለወልቃይት፥ሁመራ እና ራያ የአማራ ህዝብ በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ!

Post by Abere » 07 Jan 2023, 11:02

ለዘመናት ለነጻነታችሁ በፅናት በመቆም ከባድ መስዋዕት በመክፈል እርስት ማንነታችሁን ላስመለሳችሁ ለወልቃይት፥ሁመራ እና ራያ የአማራ ህዝብ በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ! ነጻ ህዝብ ለሌሎች በባርነት ቀንበር ለወደቁ አርአያ ነው።

እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ነጻ ያውጣ ህዝቧንም ከፍርሃት ቆፈን ከባርነት ቀንበር ይፍታው። የጌታችን መወልድ የነጻነት እና በብርሃን የመመላለስ አበነት እንጅ የባርነት፤የሌብነት፤ የግፍ እና የሃጥያት መገለጫ አይደለም። ዛሬ ኢትዮጵያ የአለም ሁሉ ሃጥያት የሚፋፋማበት፤ሰው ተዘቅዞቆ የሚሰቀልባት፤ የሰው ልጅ እራሱ የገና ፍሪዳ ሁኖ የሚጣልባት አስቀያሚ አገር ናት። ይህችን ምድር እግዜር ነጻ ያውጣት፤ህዝቧንም ህገ-አምላክ እንጅ ህገ-እንሰሳ እና አውሬ የሚገዛው አይሁን። የኢትዮጵያ ህዝብ የማስታዋል ሰው የመመስል እና ሰው የመሆን የባህርይ ጸጋ ይስጠው። ህዝባችን ከሰውነት ማማ በብዙ ተንኮታኩቶ ወድቋል። እግዜር ከሰውነት አዘቅት ወደ እውነተኛ ሰውነት ይመልሰው።