Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Digital Weyane
Senior Member
Posts: 10184
Joined: 19 Jun 2019, 21:45

የሐሰት ክስ - ስም ማጥፋት

Post by Digital Weyane » 01 Jan 2023, 14:31

የሐሰት ክስ - ስም ማጥፋት

ዲያብሎስ የታወቀው እና ሥራውን የጀመረው በሐሰት ንግግር መሆኑ ይታወቃል፡፡ በዓለመ መላእክት “እኔ ነኝ ፈጣሪ” ማለቱ እና አዳምና ሔዋንን በሐሰት ትምህርት ማጥመድ የሐሰት አባትነቱን አረጋግጦለታል፡፡ ጥንትም ሆነ ዛሬ በሐሰት አንደበት የግብር ልጆቹ የሆኑ ጁንታውያን እውነተኞች በሐሰት ሲከስሱ እና ስማቸውን ሲያጠፉ ይገኛሉ፡፡

በእግዚአብሔር ቃል ጸንተው እውነትን ይዘው የሚታገሉትን ኢትዮጵያውያና ኤርትራውያን ከሚገጥማቸው ፈተና አንዱ ከሐሰተኞች የሚሰነዘር ስም ማጥፋት ዘመቻ መሆኑ እየተለመደ መጥቷል፡፡ በመሠረቱ አይሁድ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በሐሰት መክሰሳቸውን ያስተዋለ ክርስቲያን በዚህ ሊደነቅ አይገባውም፡፡

በዘመነ ብሉይ ሶስናን ብናስታውስ ያልፈጸመችውን እንደ ፈጸመችው አድርገው በሐሰት ከሰዋት ለፍርድ ያበቋት ረበናት ለጊዜው ስም ማጥፋቱ ቢሳካላቸውም እውነቱ ሲገለጥ ግን ውርደቱ እና ቅጣቱ በእነርሱ ላይ ሆኗል፡፡ ጁንታውያን ንስሐ ካልገቡ ፍጻሜያቸው እንደ ረበናቱ ይሆናል፡፡




ቅድስት ሶስናን (Susanna ) በባቢሎን የሚኖር ስሙ ኢዮአቄም የሚባል አንድ ሰው አገባት፡፡ እርሷ ግን እጅግ መልከ መልካም የሆነች ፈጣሪ እግዚአብሔርንም የምትፈራው ነበረች፡፡

እናትና አባቷም ደጋግ ነበሩ፣ ለልጃቸውም ሙሴ የጻፋትን ኦሪት አስተምረዋት ነበር፡፡

ባሏ ኢዮአቄም ግን ግን እጅግ ባጸጋ ነበር በቤቱም አጠገብ የተክል ቦታ ነበረው ከሁሉ እርሱ ይከብር ነበርና አይሁድ ወደ እርሱ ይመጡ ነበር፡፡

ኃጢአት ከባቢሎን አገር ሕዝቡን እንጠብቃቸዋለን ከሚሉ ከግብዞች ወገኖች እንደወጣች እግዚአብሔር ስለ እነርሱ የተናገረባቸው ግብዞች የሆኑ ሁለት መምህራን በዚያ ወራት ታዩ፡፡

እነርሱም በኢዮአቄም ቤት የለመዱ የሚያገለግሉም ናቸው፡፡ የሚፈራረዱም ሁሉ ወደ እርሱ ይመጡ ነበር፡፡

ሕዝቡ ሁሉ ወደ ቤታቸው ከገቡ በኋላ ቀትር በሆነ ጊዜ ሶስና ወደ ባሏ ተክል ቦታ ገብታ በዚያ ትመላለስ ነበር፡፡

ገብታ በተመላለሰች ጊዜ እነዚያ መምህራን ሁሉ ጊዜ ያይዋት ነበርና ተመኘዋት፡፡ ልቡናቸውንም ለወጡ ሰማይንም እንዳያዩ ዐይኖቻቸውን ግልብጥ አደረጉ ሰማያዊ እግዚአብሔርን እንዳያስቡ እውነተኛ ሕግን አላሰቡም፡፡

ሁለቱም ወደዷት ፈቃዳቸውን መናገር አፍረዋልና እስበሳቸው በልቡናቸው ያለውን ነገር አልተነጋገሩም ይደርሱባትም ዘንድ ይወዱ ነበር ያገኟትም ዘንዱ ሁልጊዜ ይጠብቋታል፡፡

አንዱም አንዱን የምሳ ጊዜ ነውና ወደቤታችን እንግባ አለው እየራሳቸውም ተለያይተው ሔዱ፡፡ ተመልሰውም በጎዳና አንድነት ተገናኙ፣ ሁለቱም ተያዩ ያን ጊዜም ፍላጎታቸውን ተነጋገሩ ብቻ ለብቻ እሷን የሚያገኙበትን ጊዜ ተቃጠሩ፡፡

ከዚህም በኋላ በቀን ሲጠብቋት ሶስና ሁልጊዜ ትገባ እንደነበር ከሁለቱ ደንገጡሮቿ ጋር ገባች፡፡ አልቧታልና በተክል ውሰጥ ትታጠብ ዘንድ ወደደች፡፡ ተሠውረው ከሚጠብቋት ከሁለቱ ረበናት በቀር በዚያ ማንም ማን አልነበረም፡፡

ዘይትና ሽቱ አምጥተው ያጥቧት ዘንድ ልትታጠብ የተክሉንም ደጅ ይዘጉ ዘንድ ደንገጡሮቿን አዘዘቻቸው፡፡ እነርሱም እንዳዘዘቻቸው አደረጉ፣ የተክሉን ደጃፍ ዘግተው ያዘዘቻቸውን ያመጡ ዘንድ በሥርጥ ጎዳና ወጡ፣ የተሠወሩ እነዚያን ረበናት አላዩአቸውም፡፡

እነዚያ ደንገጡሮች ከወጡ በኋላ ሁለቱ ረበናት ተነሥተው ወደርሷ ሮጡ እነሆ የተክሉ ደጃፍ ተዘግቷል የሚያየን የለምና እንደርስብሽ ዘንድ እንወዳለንና እሺ በይን አሏት፡፡ ይህ ካልሆነ ካንቺ ጋር ሰውን እንዳገኘን ተናግረን እናጣላሻለን ስለዚህም ደንገጡሮችሽን ከአንቺ አስወጥተሸ ሰደድሽ፡፡

ሶስናም አለቀሰች፣ በሁሉም ተጨነቅሁ ባደርገው እሞታለሁ ባላደርገውም አልድንም ከእጃቸው ማምለጥንም አልችልም በእግዚአብሔር ፊት ከምበድል ኃጢአት ሳልሠራ በእጃችሁ መውደቅ ይሻለኛል አለች፡፡

ሶስና ቃሏን አሰምታ ጮኸች፡፡ እነዚያም ረበናት ከእርሷ ጋር ጮኹ አንዱ ሮጦ ሂዶ የተክሉን ደጃፍ ከፈተ፣ በቤቷም ያሉ በተክል መካከል ጩኸትን ሰምተው ወጡ ምን እንደሆነ ያዩ ዘንድ በሥርጥ ጎዳናም ሮጡ፡፡

እነዚህ ሁለቱ ረበናት ይህንን ነገር በተናገሩ ጊዜ በሶስና ላይ እንዲህ ያለ ነገር ተፈጽሞ ተሰምቶ አያውቅም ነበርና ዘመዶቿና አሽከሮቿ እጅግ አፈሩ፡፡

በማግሥቱም ሕዝቡ በባሏ በኢዮአቄም ዘንድ ተሰበሰቡ፡፡ እነዚያም ሁለቱ ረበናት ሶስናን ያስገድሏት ዘንድ ከዐመጸኛ ልባቸው ጋር መጡ፣ በሕዝቡ ሁሉ ፊት ያመጡአት ዘንድ ወደ ኢዮአቄም ሚስት ወደ ሶስና ላኩ፣ ብለው አዘዙ ወደ እርሷም ላኩባት፡፡ እርሷም ከእናት ከአባቷ ከወገኖቿ ከዘመዶቿ ከሚያውቋትም ጋር ሁሉ መጣች፡፡

ሶስና ግን እጅግ ደመ ግቡ ነበረች መልኳም ያማረ ነው፡፡ አመጸኛ የሆኑ እነዚያ ሁለቱ ረበናት መልኳን ይጠግቧት ዘንድ አዘዙና ገለጧት፡፡ አባቷ እናቷ ቤተሰቦቿ የሚያውቋትም ሁሉ አለቀሱላት፡፡ እነዚያም ሁለቱ መምህራን በሕዝቡ መካከል ተነሥተው እጆቻቸውን በራሷ ላይ አኖሩ፡፡ እርሷ ግን ልቡናዋ በእግዚአብሔር ታምኗልና እያለቀሰች ወደ ሰማይ ተመለከተች፡፡

እነዚያም ረበናት ብቻችንን በተክል ውስጥ ስንመላለስ እርሷ ከሁለቱ ደንገጡሮቿ ጋር ገባች ደንገጡሮቿንም ልካቸዋለችና የተክሉን ደጃፍ ዘግተው ሔዱ፡፡ ከዚያም በኋላ አንድ ጎልማሳ ከተሠወረበት መጥቶ አብሮዋት ተኛ፡፡ እኛ ግን በዚያ ተክል ዳርቻ ሆነን ኃጢአታቸውን አየን ወደ እነርሱም ሮጥን አንድነት ተኝተው አገኘናቸው፡፡ እኛም እርሱን መያዝ ተሳነን እርሱ በርትቶብናልና አመለጠን የተክልንም ደጃፍ ከፍቶ ወጣ፡፡ እርሷን ግን ይዘን ሰውዬው ማን እንደሆነ ጠየቅናት አልነገረችንም ለዚህም ነገር ምስክሩ እኛ ነን አሉ፡፡ የሕዝቡ መምህራንና መኳንንትም ነበሩና በአደባባይ የተሰበሰቡ ሰዎች ነገራቸውን አመኑላቸው ትሙት በቃ ብለው ፈረዱባት፡፡

ሶስናም ቃሏን አስምታ ጮኸች ዘላለም ጸንተህ የምትኖር የተሠወረውን የምታውቅ የሚደረገውን ሁሉ ሳይደረግ የምታውቅ ፈጣሪ ሆይ በሐሰት እንዳጣሉኝ አንተ ታውቃለህ እነዚህን መምህራን ክፉ ነገርን ባደረጉብኝ ገንዘብ የሠራሁት ኃጢአት ሳይኖር እነሆ እሞታለሁ አለች፡፡ እግዚአብሔርም ሰማ፡፡

ይገድሏት ዘንድ ሲወስዷት እግዚአብሔር ስሙ ዳንኤል በሚባል ልጅ ላይ ልቡናን አነሣሣ እኔ ከዚች ሴት ደም ንጹሕ ነኝ ብሎ ቃሉን አሰምቶ ተናገረ፡፡

ሕዝቡም ሁሉ ወደ እርሱ ተመልሰው አንተ የምትናገረው ይህ ነገር ምንድነው አሉ፡፡

ዳንኤልም በመካከላቸው ቁሞ አላዋቆች የምትሆኑ እናንተ የእስራኤል ልጆች ሳትመረምሩና ነገሩን ሳትረዱ በእስራኤል ልጅ ላይ እንዲህ አድርጋችሁ እንደዚህ ያለ ፍርድን ትፈርዳላቸችሁን አለ እነዚህ መምህራን በሐሰት አጣልተዋታልና ወደ አደባባይ ተመለሱ አላቸው፡፡

ሕዝቡም ሁሉ እየሮጡ ወደ አደባባይ ተመለሱ አለቆችም ዳንኤልን እግዚአብሔር አንተን አልቆሃልና በመካከላችን ተቀምጠህ ተናገር አሉት፡፡ ዳንኤልም እየራሳቸው አራርቃችሁ አቁሟቸው እኔም ልመርምራቸው አላቸውና አንዱንም አንዱን አራርቀው አቆሟቸው፡፡

ዳንኤልም ከእርሳቸው አንዱን ጠርቶ ከዚያ ሰው ጋር በምን ዕንጨት ሥር ሲነጋገሩ አየሃት አለው በኮክ ዕንጨት ሥር ሲነጋገሩ አየኋቸው አለ፣ እርሱንም አርቆ ሁለተኛውን ሲነጋገሩ ያየህበት ዕንጨት ምንድነው አለው ሮማን ከሚባል ዕንጨት ሥር ነው አለ፡፡ ሕዝቡም ሁሉ ቃላቸውን አሰምተው በመጮህ ያመነችበት ሶስናን ያዳናት እግዚአብሔርን አመሰገኑት፡፡

ከቃላቸው የተነሣ ዳንኤል አስነቅፏቸዋልና ምስክርነታቸውንም ሐሰት አድርጎባቸዋልና በነዚያ ሁለቱ መምህራን ላይ በጠላትነት ተነሥተው ገደሏቸው፡፡


Digital Weyane
Senior Member
Posts: 10184
Joined: 19 Jun 2019, 21:45

Re: የሐሰት ክስ - ስም ማጥፋት

Post by Digital Weyane » 01 Jan 2023, 17:59

የመዋሸትና የስም ማጥፋት ዘመቻ በዋነኝነት ሕወሓት የተቋቋመለት መርህ ነው። ያልዋሸ ያልዘረፈ ትግራዋይ አይበላም፣ ሥራ ወይም ሥልጣን አይሰጠውም፣ በጠላትነት ተፈርጆ ዘሩ ከምድረ ገፅ እንዲጠፋ ይደረጋል። :roll: :roll:

Fiyameta
Senior Member+
Posts: 21719
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

Re: የሐሰት ክስ - ስም ማጥፋት

Post by Fiyameta » 01 Jan 2023, 20:05

:shock: :shock: :shock: :shock:

Fiyameta
Senior Member+
Posts: 21719
Joined: 02 Aug 2018, 22:59

Re: የሐሰት ክስ - ስም ማጥፋት

Post by Fiyameta » 01 Jan 2023, 22:14




Post Reply