ስንት አይነት መጅ እራስ ስናዳሪ ነው ያለው እባካችሁ። መንግስትን ያዋረደ፣ መሪውን የሰደበና ያንጓጠጠ በአደባባይ ይሰቀል አሉ ዛሬ ደግሞ። ሲጀመር መንግስት እኮ ሀገር በሚያፈርስና ሰላም በሚንድ ህግ ነው የሚተዳደረው። ውስጡ የተሰገሰጉ ጎጠኞችንና ጅቦችንስ ምን ሊያደርጓቸው ነው መሪን ያንጓጠጠን ሰው ማሰርና መስቀል ከተጀመረ?
መሪን መስደብ ባልደግፍም ፣ በህግ ይከልከል የሚባለውን አልደግፍም። ከሆነም መጀመሪያ ህዝብን የሚሰድብና ያለአግባብ ዜጎችን የሚያጉላላ የመንግስት አስተዳደር ነው መታሰርና መሰቀል ያለበት። እነዚህ አድርባይ ጋዜጠኞችና ዩትዩብ ፍርፋሪ ለቃሚዎች የት ነበሩ፣ ሀገር ሲያፈርሱ ተይዘውና ታሰረው የነበሩት በነፃ ሲለቀቁ? የት ነበሩ መንግስት እራሱ አሸባሪ ያላቸው ወሮበላዎች ለድርድር ሲቀርቡ?