Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42831
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

አቢይ አህመድ ወላይታዎችን ምን ያህል እንደ ሚንቃቸው ይህ የሹመት ስድብ ምስክር ነው

Post by Horus » 30 Dec 2022, 23:21

አቶ ዳጋቶ ኩምቤ የወላይታ ዞን ፕሬዚዳንት ማለትም የወላይታ ብሄር ፕሬዚዳንት የነበረ ሎየር እና ወላይታ ራሱን የቻለ ክልልነት መብቱ ነው ብሎ ሲታገል አቢይ እስር ቤት ወርውሮ ሲያንገላታው የነበረ ልክ እንደ ጉራጌ ዞን መሪዎች ማለት ነው ፤ ያ ሁሉ ከሆነ በኋላና ወላይታ በግድ የመሃል ኢትዮጵያ ክልል ወስጥ አለምንም ሬፈረንደም ከተጨፈለቀ በኋላ በቁስሉ እንጨት ክተትበት እንደ ሚባለው ዳጋቶ ኩምቤን የሆነ የፌዴራል መዝገብ ቤት (ሰነድ ጠባቂ) የቢሮ ሰክሬተሪ ሾሜሃለሁ ብሎ እሱን አይደለም መላ ወላይታን ሙልጭ አድጎ ሰደባቸው! አዋረዳቸው! ወላይታ በትግሉ እንደ ጀመረው ለመብቱ ጸንቶ ቢቆም ኖሮ እንዲህ አይደፈርም እንዲህ አይሰደብም ነበር! ይህ በወላይታ ላይ የደረሰ ውርደት ያሳዝናልም፣ ያሳፍራልም!