Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

በኢፌዲሪ መንግሥት የሚተዳደሩ ተቋማትን ለመጠበቅ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በዛሬው ዕለት ትግራይ ክልል መቐለ ከተማ ገብቶ ሥራ መጀመሩን ገለጸ። EBC

Post by sarcasm » 29 Dec 2022, 11:18

ኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ የፌዴራል ተቋማትን ለመጠበቅ መቐለ ገባ
***********************


በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕገ መንግሥት መሠረት በኢፌዲሪ መንግሥት የሚተዳደሩ ተቋማትን ለመጠበቅ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በዛሬው ዕለት ትግራይ ክልል መቐለ ከተማ ገብቶ ሥራ መጀመሩን ገለጸ።

መንግሥትና ህወሓት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የደረሱባቸውን የሰላም ስምምነት ተከትሎ የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ በትግራይ ክልል የሚገኙ በኢፌዲሪ መንግሥት የሚተዳደሩ አየር ማረፊያዎች፣ የኤሌክትሪክ ኃይል፣ የቴሌኮም አገልግሎት፣ የባንክ እና ሌሎች ለኅብረተሰቡ አገልግሎት የሚሰጡ የፌዴራል ተቋማት አስተማማኝ ጥበቃ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ቀደም ብሎም በትግራይ ክልል አካባቢዎች በመግባት ኅብረተሰቡን በማረጋጋት ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ በማድረግ የፀጥታ እና ደህንነት የማስከበር ሥራዎችን እየሠራ መቆየቱ ይታወቃል።
Please wait, video is loading...