መስከረም አበራ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለች
December 14, 2022 – BBC Amharic
መስከረም አበራ
13 ታህሳስ 2022
“ኢትዮ ንቃት” የተሰኘ የዩቲዩብ ሚዲያ መሥራች እና ባለቤት የሆነችው መስከረም አበራ ዛሬ ማክሰኞ ታኅሣሥ 04/2015 ዓ.ም. ከሰዓት በኋላ አዲስ አበባ ውስጥ በፌደራል ፖሊስ በቁጥጥር ሥር መዋሏን ባለቤቷ ለቢቢሲ ተናገረ።
መንግሥትን አጥብቃ በመተቸት የምትታወቀው መስከረም አበራ ባለቤት አቶ ፍጹም ገ/ሚካኤል ለቢቢሲ እንደተናገረው ከሰዓት 10፡30 አካባቢ 22 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አብረው ሳሉ ሲቪል እና የፌደራል ፖሊስ የደንብ ልብስ የለበሱ ሰዎች መጥተው መስከረምን ይዘው ሄደዋል።
መስከረም የግለሰቦቹን ማንነት ስትጠይቅ የፌደራል ፖሊስ አባላት መሆናቸውን ከገለጹ በኋላ ሜክሲኮ አካባቢ ወደሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ መሥሪያ ቤት ይዘዋት እንደሚሄዱ ተናግረው በመኪና እንደወሰዷት ባለቤቷ ፍጹም ገ/ሚካኤል አስረድቷል።
በአሜሪካ – አፍሪካ የመሪዎች ጉባኤ ላይ ምን አይነት ጉዳዮች ይነሳሉ?13 ታህሳስ 2022
በጅግጅጋ አየር ማረፊያ የምክር ቤት አባሏን የገደለው የፖሊስ አባል ሞት ተፈረደበት13 ታህሳስ 2022
ኢትዮጵያ፡ ‘የማይናገሩት’ እና ‘የማይነገርለት’ የተንሰራፋው የወጣቶች ጭንቀት13 ታህሳስ 2022
ፍጹም እንደሚለው ባለቤቱ ታስራ ወደምትገኝበት ሜክሲኮ የፌደራል ወንጀል ምርመራ አቀንቶ መስከረምን ማግኘቱን እና በምን ወንጀል ተጠርጥራ በቁጥጥር ስር እንደዋለች እንደማታውቅ ጨምሮ ለቢቢሲ ተናግሯል።
ቢቢሲ መስከረም በምን ወንጀል ተጠርጥራ በቁጥጥር ሥር እንደዋለች ከፌደራል ፖሊስ ምላሽ ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም።
የፌደራል እና የክልል መንግሥታትን በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ አጥብቃ በመተችት የምትታቀው መስከረም አበራ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ስትውል ይህ የመጀሪያዋ አይደለም።
ባለፈው ዓመት ግንቦት 2014 ዓ.ም. በቁጥጥር ሥር ከዋለች በኋላ በ30ሺህ ብር ዋስትና ከእስር መለቀቋን ባለቤቷ ፍጹም አስታውሷል።
በሐዋሳ ዩኒቨርስቲ የቀድሞ መምህርት የነበረችው መስከረም ግንቦት አጋማሽ 2014 ዓ.ም. ሕዝባዊ አመፅ በመቀስቀስ ወንጀል ፍርድ ቤት ቀርባ ነበር።
ባለቤቷ ፍጹም እንዳለው መሰከረም የመምህርነት ሥራዋን በማቆም ሙሉ ትኩረቷ በሚዲያ ሥራ ላይ አደርጋ እንደምትገኝ ጨምሮ ለቢቢሲ ተናግሯል።
Share
-
Za-Ilmaknun
- Member
- Posts: 4487
- Joined: 15 Jun 2018, 17:40
Re: Meskerm Abera arrested again!
It tells you so much about the kind of leadership we have in the country. Jawar, Jal Maro , Jal Ibssa and Sibehat Nega are the kind of people the Gov't is standing with. There is going to be mass arrest of those Ethiopians who are strongly criticizing the OPDO gov't for failing to discharge its responsibilities.
Re: Meskerm Abera arrested again!
መስከረም አበራን የአማራ ቃቄ ወርድወት ብዬያት ነበር! መስከረም በዚህ ዘመን የተወለደች የዚያ ትውልድ አባል ነች! እንስት የትግል መሪ ብቻ ሳይሆን ጥልቅ የፖለቲካ ልህቂት ነች! አዳነች መስከረምን በማሰር ትግሉ ላይ ቤንዚን ነው የምትጨምረው! አዲስ አበቤ ሁሉ ያውቃል የኦሮሙማ ተረኞች በመላ ከተማው አፈሳ እያደረጉ እንደሆነ፤ ያ ደሞ ለኢትዮጵያዊያን ብርቅ አይደለም!! ቁም ነገሩ ጸረ ጎሳ ገዥነትና ጸረ ሰልቃጭ ትግሉን በሁሉም ቦታና ሕዝብ ውስጥ ማደረጀቱ ነው!