TGAA wrote: ↑05 Dec 2022, 11:00
ስለ ጋላቢዎቹ ለግዜው ወደጎን እንተውውና ሜዳውን አመቻቸተው ስለሚያስጋልቡት ብናወሳስ
1.. ከአራት አመት በፊት ድምጹ የሚይሰማ " ኦነግ " ከመከላከያ እኩል ዘመናዊ መሳሪያ ያስታጠቀው ማን ነው?
2.. አማሮች በወለጋ ለአራት አመት ተለይተው ባአማርነታቸው የሚገደሉበት ቦታ በተደጋጋሚ የታወቁ ቦታዎች ነቸው ለምንድነው መንግስት መከላከል ያልቻለው ፤ ካለቻለ ደግሞ ለምንድነው አማሮቹ አካቢያቸውን እንዲጠብቁ አሰልጥኖ የማይስታጥቃቸው ፤ መንግስት ፎቶ ና ዜና እንዳይወጣ ከማፈን በስተቀር ምንም የሚያደርገው ነገር የለም ፤
3። 400000 በላይ የሰለጠኑ ሚሊሻዎች ያሉበት ክልል እንዴት ነው እነዚህ የግድያ ክልሎችን መከላከል የምይችለው
4። መንገስት ከአብይ ጀምሮ እያንዳንዱ ባለስልጣን ይህንን የሰቆቃ ድግስ እያቃለሉ ችግሩን የሚናገሩት ፤ለምንድነው ?
የዚህ ሰቆቃ ማቆምያው " የኢትዮጵያ መንግስት ህዝብን ለመክለከል ምን እያደረገ " የሚለውን ጥያቄ ስንመልስ ነው እንጁ ጠላቶቻቸን ምን እያሰቡ ነው በማለት አይደለም ፤ ጠላትማ ሁልግዜም ጠላት ነው መጀመርያ .......
ከ 4 አመት በፊት ድምጻቸዉ ብዙም የማይሰማዉ አብን ና ፋኖ ተብዬዎቹ (አንድ መዋቅር ይኑራቸው የተለያዩ ይሁኑ ኢግዚያብሔር ነዉ የምያዉቀዉ) ዛሬ ስማቸዉ የጋነነዉ ና ከመንግስት እኩል ካልታጠቅን የማለት ደረጀ ላይ የደረሱት ከምን ተነስቶዉ ነዉ?
ይህን ጥያቄ መመለስ ከቻልክ ከላይ ያደመቅኩትን የራስህንም ጥያቄ መመለስ ትችላለህ።
ምንጩ አንድ ይመስለኛል።
አገሪቷን እርጋታ መንሳት፣ የደከመች ና አሁን ሀዪቲ በምትባለዉ አገር ዉስጥ እንደሆነዉ ሁሉ ኢትዮጵያንም በጋንግ የምትታመስ አገር ማድረግ ነዉ፣ ትልቁ አለማዉ።
መንግስት የሰራውን ሁሉ ማንቋሸሽ፣ እዉቅና መንሳት፣ ደጉን ነገር ሁሉ ገሸሽ በማድረግ መጥፎዉን ገጽታ ወደ ላይ ማራገብ፣ የመንጋን ሃይል ተጠቅሞ ብጥብጥ ና ግርግር ማስፋት፣ እዚህም ፎረም ላይ የምናየዉ የዚሁ ትልቅ አጀንዳ የሆኑትን አስተያየቶችን ነዉ፣ የአንተንም ጨምሮ።
የንተ ተነሳሽነት አማረን ለመታገድ ሳይሆን፣ አማራ እንዳይረጋጋ በማድረግ የትልቁን ግብ ተዋጽዎ ማበርከት ነዉ። ሀቁ ና እንቅጩ ይህ ነዉ!
The grand agenda remains the same: take out the source of Ethiopia's strength, which has been its unity all along, and make it vulnerable to any adverse situation, including instability.
That is what is happening in front of our very own eyes.