Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 15450
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

የሼህ ሁሴን ጅብሪል ትንብይት ተፈጸመ ወይስ ገና ነው? በኢትዮጵያ ታሪክ 1 ሚልዮን ሰው የጨረሰ ጦርነት ተሰምቶም አይታወቅ።

Post by Abere » 22 Nov 2022, 14:11

የሼህ ሁሴን ጅብሪል ትንብይት ተፈጸመ ወይስ ገና ነው? በኢትዮጵያ ታሪክ 1 ሚልዮን ሰው የጨረሰ ጦርነት ተሰምቶም አይታወቅ።

የእርሳቸው ትንብይትን የያዘውን ጽሁፍ ያነበብኩት ከአስርት አመታት በፊት ነው። ከዚያ ወድህ ደግሞ በርካታ ዩቲዮቦች ዘግበዋል። ይህ ትንብይት ከአነበብኩት ውስጥ ሁለት ነገሮች ይገርሙኛል።

1ኛ) ወሎ ክፍለ ሀገር የጦርነት ዐውድማ እንደሚሆን

2) በጦርነቱ የሚያልቀው ህልቆ መስፈር እንደማይኖረው እና በቀናት እንኳን ተቀብሮ እንደምያልቅ በዚያውም በግልጽ" ከእንግድህ ለትግሬ የለው ወንድነት" የሚል ትንብይ ተናገረዋል - አንብቤዋለሁ።

Right
Member
Posts: 4827
Joined: 09 Jan 2022, 13:05

Re: የሼህ ሁሴን ጅብሪል ትንብይት ተፈጸመ ወይስ ገና ነው? በኢትዮጵያ ታሪክ 1 ሚልዮን ሰው የጨረሰ ጦርነት ተሰምቶም አይታወቅ።

Post by Right » 22 Nov 2022, 14:27

1000000
The people who are responsible for the deaths of so many are now free working for another military adventure.

Both the TPLF and PP leaders belongs to the ICC.

Misraq
Senior Member
Posts: 17859
Joined: 27 Sep 2009, 19:43
Location: Zemunda

Re: የሼህ ሁሴን ጅብሪል ትንብይት ተፈጸመ ወይስ ገና ነው? በኢትዮጵያ ታሪክ 1 ሚልዮን ሰው የጨረሰ ጦርነት ተሰምቶም አይታወቅ።

Post by Misraq » 22 Nov 2022, 14:31

ወንድሜ አበረ

በዚህ በሸህ ሁሴን ትንቢት አሸወድ፥፥ ሸህ ሁሴን ከአጼ ምኒልኪ በህዋላ ስለሆነው አልተናገሩም፥፥ በጣም የሚገርምህ የአብይ ካድሬዎች ጨምረውበት አውጥተውታል፥፥ የጨመሩበትም አብያን የሚያሞጋግስና ከጅማ የሚመጣ ለአርባ አመት ሃገሪቱን የሚያበለጽግ ምናምን የሚል ነው፥፥

ወያኔዎች የወሎን ሕዝብ ያስተኙት በሸህ ሁሴን ትንቢት ነው፥፥ ትግሬ ራያ ላይ ያልቃል ብለው፥፥ ትግሬ በሽሬ አላለቀም? በጋሸናስ?፧ በአፋርስ? ሽራሮስ? በማይጸብሪስ? ክሪቲካል ቲንኪንግ ብዙ ጥያቄ ያጭራል፥፥

ወያኔዎች የጎንደርን ሕዝብም በአባ ዘወንጌል በሚል ተረት አሸብረው ሱባኤ አስገብተውታል፥፥ ለዚህም ተባባርያቸው ዘረቢሱ ዘመድኩን በቀለ የሚባለው ተንከሲስ ነው፥፥ አባ ዘወንጌል እንዲህ ብለዋል ትንቢቱ ይፈጸማልና ቁጭ ብላችኡ ጠብቁ የሚል የስነልቦና ጦርነትም ከፍተው ነበር ሊያሽመደምዱት የሰሩት:: ያመነው አመነና ተቀመጠ፥፥ ያላመነው ፋኖ ግን ተመመ ትግሬንም ከመከላይከያ ጋር ሆኖ ወቃው፥፥

Abere
Senior Member
Posts: 15450
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: የሼህ ሁሴን ጅብሪል ትንብይት ተፈጸመ ወይስ ገና ነው? በኢትዮጵያ ታሪክ 1 ሚልዮን ሰው የጨረሰ ጦርነት ተሰምቶም አይታወቅ።

Post by Abere » 22 Nov 2022, 17:42

ምስራቅ፤

___ስለ ሼሁሴን ፍርድ ወይም ትንብይ የሰማሁት ከብዙ አመታት በፊት ነው። በዚህ ጦርነት ወቅት አንዳንድ ዩቲዩቦች የለጠፍትን አዳምጨዋለሁ - እርሳቸው ያላሏቸው ሰዎች ጨምረውበታል። አማርኛውም ይሁን አገላለጻቸው ሼህ ሁሴን ከፈረዱት ጊዜ ጋር አይሄድም። I do not seriously take the youtubers narratives.

__ ሸህ ሁሴን ጅብሪል በምኒልክ ጊዜ ቢኖሩም ከምኒልክ በኋላ በአጼ ሀይለስላሴ እን ከእርሳቸው በኋላ ስለሚሆነው በደንብ ተናግረዋል። እኔ ከጽሁፍ በፊት በህዝብ ስነ-ቃልም ሲባል አውቃለሁ። የተጻፈውን ደግሞ ያነበብኩት ከ3 አስርት አመታት በፊት አዲሰ አበባ ዩኒቨርስቲ ነው።

ለምሳሌ፤ ሃይለስ ላሴ እያሱን እንደሚያጠፉት እና ስልጣን እንደሚይዙ ተናግረዋል።እያሱ የሚባል ልጅ እንደማይረባ ተንብየዋል።

ተፈሪ የሚሏት አንድት ትንሽ ኩዛ፥
ኢትዮጵያን አየቻት መርዛ መርዛ። (ከሀረር ሃይለስላሴ እንደሚወለድ እና የእያሱን መንበር እንደሚቀማ )-

እንድሁም የንጉስ ዘመን እንድሚጠፋ እና አገር እንደሚታወክ - የድሃ ወይም የባለገር ልጅ ከየሚዳው ተነስቶ አገር እመራለሁ ብሎ እንደሚበጠብጥ፡

አይባሉም ንጉስ፤አይባሉም አጤ፥
አገር ይታመሳል - በመንደር ወጠጤ። ( በማለት - የቀበሌ ካድሬ ወዘተ ማለት ነው።)

በመቀጠልም አክራሪ እስልምና (ውሃቢዝም) እንደሚበራከት እና ምናልባትም መጤ እስልምና ኢትዮጵያን እንደሚያምስ ተንብየዋል።

ሳይንት ልሂድ እና ከአማሮቹ ዘንድ፥
ሲሰራ አይቻለሁ ***መስጊድ። [*** ያነበብኩት ቃላት መሃል ስልጠፋኝ ነው)። ወሎ ውስጥ ሳይንት እና ዋድላ ደላንታ እጅግ ወይም ሙሉ በሙሉ ክርስቲያን ነው። ሸህ ውሴን ባይገርማችሁ አማሮች (ክርስቲያን) መካከል መስጊድ ሲሰራ ታየኝ ማለታቸው ይመስላል።

ምናልባት የምጽአተ -ቀሪብ ትንብይት ሲነገር የሰማነው እርሳቸው ተናገሩት ከሚባለው ነው። በክርስትና ይህን ያህል አልሰማሁም። አንዳንዶች ቴድሮስ የሚባል ደግን ንጉስ ይመጣል የሚሉ ሰምቻለሁ። እኔ ከልጅነት እስከ ዕውቀት ግን ትልቅ የዕልቂት ማዕበል (apoclyptc)) ይመጣል ብለዋል የተባሉት እርሳቸው ብቻ ነው። ቁም ነገሩ ይህ አሁን ያየነው ዕልቂት የመጨረሻው ይሆን ወይ? እኔ ግን እንጃ እላለሁ። ከዚህ የከፋ ግን አያሳየን።

Misraq wrote:
22 Nov 2022, 14:31

Post Reply