Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 15453
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

"Ethnocracy is a Mental Disorder" Horus. Can't Wait to Read a Book Published as Entitled from ሆረስ!

Post by Abere » 17 Nov 2022, 13:43

"Ethnocracy is a Mental Disorder" Horus. Can't Wait to Read a Book Published as Entitled from ሆረስ!
I fully concur with this theory and empirical evidence from Ethiopia's 31 years of wasteful journey is alive testimony. Can we have more evidence than the Tigre-Woyane's futile and suicide years of wrong action? Ethiopia has to cure herself from this mental disorder called ethnic/tribal political party and tribal federalism.

Horus
Senior Member+
Posts: 42840
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: "Ethnocracy is a Mental Disorder" Horus. Can't Wait to Read a Book Published as Entitled from ሆረስ!

Post by Horus » 17 Nov 2022, 16:04

አበረ፣
አንተ ትቀልዳለህ! ኤትኖክራሲን እንኳንስ እጅግ ውስብስብ አይጨበጤ በሆነው እንደ ኢሞሽናል እና ቶውት (emotional & thought) ዲሶርደር ለንገነዘብ ቀርቶ፣ እንኳንስ እንደ ፐርሰናሊቲ እና ሶሺያ ማንነት (personality & social identity) ዲስኦርደር ልንገነዘበው ቀርቶ ኤትኖክራሲን እንደ ፖለቲካዊ ርዕዮት (political ideology) እንኳን ተገንዝበነው ዴሞክራሲ ከሚባለው አይዲዮሎጂ ፍጹም ተጻራሪ ሃሳብ መሆኑን እንኳ ተቀብለን የፖለቲካ ዲስኮርሳችን ውስጥ አንከራከርበትም ። አይደለም በሶሺያል ሳይኮሎጂ ደረጃ ያለው ኤትኖክራቲክ የህሳቤ ዲስኦርደር በግለሰብ ደረጃ ያሉት እነዲፕሬሽን፣ አንክዛይቲ፣ ሳይኮሲስ እና የፐርሰናሊቲ ማንነት በሽታዎች እንኳ አይታወቁም በኢትዮጵያ።

አንተ ባነሳሃው ጉዳይ ቢያንስ ቢያንስ ኤትኖክራሲ በጽንሰ ሃሳቡም ሆነ በማህበራዊ ትግበራው ፍጹም የዲሞክራሲ ተጻራሪና ማሀበረሰብን በፖለቲካ ማደራጃ ፍልስፍናም፣ ቲኦሪም፣ ዘዴም፣ ድርጅትም፣ ፕራክቲስም እንዳልሆነ ጥርት ያለ እውቀት መፍጠር ብንችል ዛሬ ባይሆን የነገው ትውልድ ከዚህ ጭለማ መውጣት ይችላል ። ዛሬ ላይ ልብ ብለህ ከሆነ ዴሞክራሲ የሚለው ቃል ከኢትዮጵያ ሚዲያና ፓብሊክ ዲስኮርስ እየጠፋ ነው ። ፍትህ፣ ነጽነት የሚባሉት ቃላት እየጠፉ ነው ። ሕዝባችን ወደ ረጅም የባርነት ዘመን እየወረደ ለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለውም ። አሳ በውቅያኖስ ውስጥ ይዋኛል፣ ግ ን ውስቅያኖሱን አያየውም ። አበሻም ያለው ያን በሚመስል የኤትኖክራሲ ውቅያኖስ ውስጥ ነው የሚራኮተው!! እጅግ አስፈሪ ዘመን ነው ።

Post Reply