የትግራይ ህዝብ የመጨረሻ እና ትክክለኛ ፍልሚያ በተለምዶ" የደደቢት" ወይም የትህነግ እና ኦነግ ህገ-መንግስት ለመደምሰስ መታገል ብቻ ነው።
ሆድ ያበለውን ብቅል/ጌሾ ያወጣዋል እንድሉ አፍቃሪ ትህነግ ደጋፊው ቴድሮስ ጸጋዬ ሰሞኑን በቪድዮው እንዳለው የትህነግ-ኦነግ ህገ-መንግስት የትግራይን ህዝብ ዘለዓለማዊ አናሳ እና ክልል በሚባል የሰው ልጆች ዙ ተቸግሮ እና ታስሮ እንድ ኖር የሚያደርግ ነው። ለዛሬው ዓለም አቀፋዊ የትግራይ ህዝብ ውርደት፤ ችግር እና ዕልቂት ይህ የደደቢት ህገ-መንግስት ነው።ይህን ነው የትግራይ ህዝብ አሁን ሊታገል የወደፊት ዕጣው የሆነው። ይህን ሲያደርግ የትግራይ ህዝብ እውነተኛ አሸናፊ ይሆናል - ከውድቀቱ ይነሳል። ይህ የደቡብ አፍሪካው ድርድር የሁለት ወንበደዎች ስምምነት እንጅ ማንንም ከውድቀት አያነሳውም። ኢትዮጵያ የምታሸንፈው የኦነግ እና ወያኔ ህገ-ወጥ ህገ-መንግስት ሲደመሰስ ብቻ ነው። ከዚያ ውጭ እዘጭ እዘጭ ሰው እየገበሩ ስንደ እየለመኑ እየታረዱ መኖር ነው።