25m
·
የኢትዮጵያ መንግስት እና የህወሓት የወታደራዊ አመራሮች #ሰኞ ጥቅምት 28 ቀን 2015 ዓ/ም በጎረቤት ሀገር ኬንያ ፤ ናይሮቢ ሊገናኙ ነው።
በዛሬው ዕለት የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን መቀመጫቸውን በአዲስ አበባ ላደረጉ የዲፕሎማቲክ ማህበረሰብ አባላት ማብራሪያ በሰጡበት ወቅት ነው።
በዚህ መድረክ ላይ የሁለቱ ወታደራዊ አመራሮች በኬንያ ናይሮቢ ተገናኝተዉ በትጥቅ ማስፈታቱ ሂደት ላይ እንደሚወያዩ የተገለፀ ሲሆን በፕሪቶሪያ የተደረሰውን የሰላም ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ #ስራዎች_መጀመራቸው ተገልጿል።
በተደረሰው የሰላም ስምምነት መሰረት የህወሓት ታጣቂዎች ትጥቅ በሚፈቱበት ሁኔታ ላይ ለመወያየት ሁለቱ ወታደራዊ አመራሮች የስልክ ልውውጥ ማድረጋቸውን አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ተናግረዋል።
የፊታችን ሰኞ ደግሞ ናይሮቢ ውስጥ ተገናኝተው እንደሚወያዩ መገለፃቸውን የብሄራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ዘግቧል።
