Za-Ilmakun,
You said,"The people leading the country have openly admitted that they are so tired of planning, fighting and leading...which could be implications of not having the resolve to elevate themselves to the demands of the current situations. Self preservation and solving problems of this magnitude are completely different." በትክክል!
እኔ ከወራት በፊት የኢትዮጵያ ጦር የመዋጋት ፍላጎቱ ዝቅተኛ ይሆናል ፣ የምር የሚዋጉት በትህነግ የተወረሩት አማሮችና አፋሮች ይሆናሉ ። በተለይ ከደቡብ ክልል የተመለመሉት ብዙ ሳይዋጉ እጅ ይሰጣሉ ብዬ ነበር ። 4ኪሎ ስልጣን የያዙት ኦሮሞ ስለሆኑ ከስልጣን ላለመባረር ጠንክረው ቢዋጉ አያስገርምም! ይህን በማለቴ ዲፊንድ ዘ ትሩዝ የሚባል የኦሮሞ ተረኛ ኤትኖክራት እስከ ዛሬ ሟረተኛ ይለኛል ። ሃቁ ግን ያልከው ነው ። ኢትዮጵያ ከፐርዢያ ወይም ሮማን ኢምፓየር ጋር አይደለም የምትዋጋው፣ የጣሊያን ወረራ አይደለም የምትከላከለው ። ሁለት የጎሳ ቡድኖች አይዲኦሎጂና የአላማ አንድነት ያላቸው ፣ ኢትዮጵያዊነት ኮሶ ኮስ የሚላቸው፣ ኢትዮጵያዊነትን "ነፍጠኝነት" ብለው የፈረጁ የትግሬና ኦሮሞ ቡድኖች ስልጣን ሽኩቻ ጦርነት ስለሆነ ወታደር መዋጋት ሰለቸው፣ ጄኔራሉ ጦር ማቀድ ሰለቸው፣ ሕዝቡ ሰንጋና ፍየል ማዋጣት ሰለቸው ቢል እጅግ ትክክለኛ ሪያሊቲ ነው።
ይህ ሁሉ ዉጊያና ሞት ከተካሄደ በኋላ ለኢትዮጵያ የሚተርፈው ትሩፋት የኦሮሞ ተረኞችን እና የትግሬ ተቀናቃኞችን ስልጣንና ሃብት ክፍፍል ነው ። ኢትዮጵያ ከሞንጎሊያ ወረራ አይደለም ራሷን ለመከላከል ምትዋጋው፣ ከራሷ ጋር ነው ። ስለዚህ ነገ አቢይና ደብረጽዮን ቢስማሙና ቢበለጽጉ ጉዳዩ ሰው ከዘመዱ አህያ ካመዱ (Birds of same feather flock together) እንደ ማለት ነው።