Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Axumezana
Senior Member
Posts: 19218
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Aberha Desta the Tigrayan who have stood on the side of his people!

Post by Axumezana » 01 Nov 2022, 20:33

Aberha Desta is among the exemplary Tigrayan politicians who freed himself from the temptation of conforming with Abiy to be used as his banda and stood on the side of his people. Tigray needs more of Desta Abraha!

sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

Re: Aberha Desta the Tigrayan who have stood on the side of his people!

Post by sarcasm » 01 Nov 2022, 20:58

He is a man of principles!

ያኔ የት ነበርኩኝ?


በ27ቱ የህወሓት/ኢህአዴግ ግዜ የት ነበርኩ? አብዛኞቻቹ አሁን የፒፒ ቅልብተኞች ያኔ የህወሓት/ኢህአዴግ አሻንጉሊት ካድሬዎች ሆናችሁ ለሆዳችሁ ስትሉ የገዛ ህዝባችሁን ስታሰቃዩ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰውን ጭቆና ስቃወምና ሳጋልጥ ነበርኩ። በዚህም ለሁለት ዓመት ያህል በእስር አሳልፌያለሁ። እንደናንተ ከህዝብ ደሕንነት በላይ ድርጅትን ማስቀድም ብሆን ኖሮ ያኔ የህወሓትን የአባልነት ፎርም ሞልቼ ከናንተ በላይ የስልጣንና የቁስ ተጠቃሚ መሆን እችል ነበር። ህሊና ባይኖረኝ ፒፒን ደግፌ ሚኒስተር የመሆን ዕድል ነበረኝ።


==========
"የትግራይ ህዝብ እየተጨፈጨፈ ነው" ብዬ ስፅፍ "ሰሜን ዕዝ ሲመታ ምንም አላልክም፣ አማራና ዓፋር ሲፈናቀል የት ነበርክ? 27 ዓመት ሙሉ ኢትዮጵያውን ሲገደሉ የት ነበርክ?" የሚሉ ጥያቄዎች አስተናግዳለሁ።

በሰሜን ዕዝ ግዜ መቐለ ነበርኩ። ምንም መብራት፣ ስልክ፣ ኢንተርኔት፣ ባንክ፣ ምግብ፣ ተስፋ አልነበረንም። በዛ ግዜ የኢንተርኔት አክሰስ ቢኖረኝ ብዙ ምለው ነገር ነበረኝ። በትግራይ ህዝብና በራሴ ላይ የደረሰው በደልም ጭምር። ግን አልሆነም፣ ሁሉም ዝግ ነበራ!

የዓፋርና የአማራ ህዝብ ሲፈናቀል ግዜ ጦርነትን በመቃወሜ ምክንያት በፒፒ/ኢህአዴግ ተይዤ እስርቤት ነበርኩ። አምና በዚሁ ግዜ አዲስ አበባ ሦስተኛ (ፖሊስ ኮሚሽን) እስርቤት ነበርኩ። ታድያ እስርቤት ውስጥ ኢንተርኔት አልነበረንም! (አሁንም እስክታሰር ድረስ ስለ ትግራይ እየፃፍኩኝ ነው 😁)
በ27ቱ የህወሓት/ኢህአዴግ ግዜ የት ነበርኩ? አብዛኞቻቹ አሁን የፒፒ ቅልብተኞች ያኔ የህወሓት/ኢህአዴግ አሻንጉሊት ካድሬዎች ሆናችሁ ለሆዳችሁ ስትሉ የገዛ ህዝባችሁን ስታሰቃዩ በኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰውን ጭቆና ስቃወምና ሳጋልጥ ነበርኩ። በዚህም ለሁለት ዓመት ያህል በእስር አሳልፌያለሁ።
እንደናንተ ከህዝብ ደሕንነት በላይ ድርጅትን ማስቀድም ብሆን ኖሮ ያኔ የህወሓትን የአባልነት ፎርም ሞልቼ ከናንተ በላይ የስልጣንና የቁስ ተጠቃሚ መሆን እችል ነበር።

አሁንም ስለ ትግራይ ምፅፈው (1) ስላልታሰርኩ፣ (2) ኢንተርኔት አክሰስ ስላለኝ፣ (3) ሰላማዊው የትግራይ ህዝብ በግፍ እየተጨፈጨፈ ስለሆነ፣ (4) ህሊና ስላለኝ ነው። (ህሊና ባይኖረኝ ፒፒን ደግፌ ሚኒስተር የመሆን ዕድል ነበረኝ። በህወሓት ግዜም እንደዚሁ)

ህዝቤ ላይ ጦርነት ታውጇል። ለህዝቤ ድምፅ መሆን ግዴታዬ ነው!
Please wait, video is loading...

Sam Ebalalehu
Member
Posts: 3639
Joined: 23 Jun 2018, 21:29

Re: Aberha Desta the Tigrayan who have stood on the side of his people!

Post by Sam Ebalalehu » 01 Nov 2022, 21:23

Mr. መቃወም : ሚኒስቴር መሆን ስችል አልሆንኩም ህወሓትን ስለተቃወምኩ ጥሩ ክርክር አይመስለኝም። ህወሓትን ከተቃወምክ አንተ ሳትነግረን የህወሓትን የሚኒስትርነትን ማባበያ እንደማትቀበል እንገምታለን።
የማንገምተው ግን አንተ ስለህሊናህ ንፁህነት ብዙ ያልክ ሰው "ህዝቤ" ላይ ጦርነት ታውጆአል" የሚለውን አረፍተነገርህን ነው። ያ አረፍተነገርህ ከምንም በላይ ማንነትህን ይገልፃል። የ ትግራይን ህዝብ "ህዝቤ" ስትል ኢትዮጵያኖችን እንዴት ልትገልፅ ይቻልሀል። በትክክል ካስታወስኩ አንተ አንድ ወቅት the we versus they ፖለቲካ ትቃወም ነበር። ለውጥ ካለ በአንተ አስተሳሰብ ነው።

Axumezana
Senior Member
Posts: 19218
Joined: 27 Jan 2020, 23:15

Re: Aberha Desta the Tigrayan who have stood on the side of his people!

Post by Axumezana » 01 Nov 2022, 21:32

አብርሃ ፥ ደስታ፥ ዜግነቱ፥ ኢትዮጵያዊ፥ ነው፥ ማንነቱ፥ ደግሞ፥ ትግረዋይ፥ ነው። ህዝቤ፥ ሲል፥ በማንነቱ፥ ላይ፥ ተሞርኩዞ፥ የትግራይ፥ ህዝብን፥ ማለት፥ ሲሆን፥ በዜግነቱ፥ ደግሞ፥ የኢትዮጵያን፥ ህዝብ፥ ህዝቤ፥ እንደሚል፥ ግልጽ፥ ነው። እንደየሁኔታው፥ አንድ፥ ትግረዋይ፥ የትግራይንም፥ ህዝብ፥ ሆነ፥ የኢትዮጵያን፥ ህዝብ ፥ ህዝቤ፥ ቢል፥ ተቃርኖም፥ ሆነ፥ስህተት፥ የለውም።

Sam Ebalalehu
Member
Posts: 3639
Joined: 23 Jun 2018, 21:29

Re: Aberha Desta the Tigrayan who have stood on the side of his people!

Post by Sam Ebalalehu » 01 Nov 2022, 21:49

ስለማንነትና ዜግነት ልዩነት ማብራሪያህ ደካማ ነው። እኔ ኢትዮጵያኖችን ነው ህዝቤ የምለው። የመለሰን ኢትዮጵያዊ ከመሆኔ በፊት ትግራያዊ ነበርኩ አይነት ክርክር ነው የምትከራከረው ያለሀው። ዋናው ነጥቤ which was implied አብርሀ ደስታ principle ያለው ሰው አለመሆኑን ማሳየት ነው። ህሊና ቢኖረው ኑሮ የ ኢትዮጵያ መንግሥት በ "ህዝቤ" ላይ ጦርነት አውጆአል የሚል ውሸት አይዋሽም ነበር።

Post Reply