Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42868
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

ድፊትና ትህነግ

Post by Horus » 19 Oct 2022, 00:45

አንድ ትህነግ አፍቃሪ የሆነ ሰው አሁን ትህነግ እየሰራ ያለው ድፊት ሰርቶ ጥምር ጦሩን እዚያ ድፊት ውስጥ ለመያዝ ነው የሚል የዉጊይ እስትራተጀም ጠቅሶ ነበር ። ምናልባት ነገ ከነገ ወዲያ ትህነግ ይህን ሁሉ ፈጣን ማፈግፈግ የምናደርገው ጥምር ጦሩን እዚያች ድፊት ውስጥ ከተን ለመክበብ ነው ይሉ ይሆናል። ግን ይህ ድፊት ለትህነግ አይሆንም ። ለምን ብትሉ ጥምር ጦሩ ከደጀኑ ርቆ በጥልቀት ትግሬ መግባቱ የሎጂስቲክስ ችግር ሊይመጣበት ይችላል ። በኔ እምነት ያን ችግር ስለፈታ ነው ጦሩ ትግሬ የገባው። ደሞም ትህነግ አደረጃጀቱን ወደ ትናንሽ የጎሬላ ዩኒትነት ለውጦ በገጠርም በከተማም የጎሬላ ዉጊያዎች ያዘጋጅ ይሆናል። ነገር ግን ከበባ አድርጎ ጥምሩን ድፊት ሊያስገባ አይችልም ። በጄትና ድሮን ስለሚደበደብ ። ሰፊ የጎሬላ ዉጊያ ለማድረግ ቢያቅድ እንኳን መሳሪያ፣ ምግብ፣ መድሃኒት አቅርቦት ይፈልጋል ። ለዚህ ደሞ እስከ 1 ሚሊዮን የሚሆን ጥምር ጦርና የሲቪል ህዝብ መንግስት ማሰማራት ከቻለ ጎሬላው የሚዋኝበትን ባህር ሊያደርቀው ይችላል። ዘመኑ የሳተላይት ዘመን ስለሆነ ። ስለዚህ አቢይ በቂ የሆነ ግዙፍ ሪሶርስ በትግሬ ላይ ካፈሰሰ ትህነግ ከመክሰም አይተርፍም! ድፊቱን እርሱት!