Ethiopian Press Agency /የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት/
መንግሥት ዛሬ ባወጣው መግለጫ ያስተላለፋቸው ዋና ዋና መልዕክቶች

ሕወሐት በሙሉ ዐቅሙ ጥቃት ከመክፈቱ በፊት የኢትዮጵያን የአየር ክልል ደጋፊዎቹ በሆኑ የኢትዮጵያ የውጭ ጠላቶች ሲያስደፍር ቆይቷል፤

በዚህም የተነሣ የኢትዮጵያ መንግሥት የሀገሪቱን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት የመጠበቅ ግዴታውን እንዲወጣ አስገድዶታል፤

ስለሆነም የሀገሪቱን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ለማስከበር የኢትዮጵያ መንግሥት የአውሮፕላን ማረፊያዎችን፣ የፌዴራል ተቋማትንና ታላላቅ መሠረተ ልማቶችን የግድ መጠበቅ አለበት ማለት ነው፤

የኢትዮጵያመንግሥት የሚወስዳቸው ርምጃዎች የግድ አስፈላጊ የሆኑት በሕወሐት ተደጋጋሚ ጥቃት የተነሣ ብቻ ሳይሆን ከሀገሪቱ ታሪካዊ ጠላቶች ጋር ተቀናጅቶ በሚፈጽማቸው ተግባራት ምክንያት ጭምር ነው፤

ይህም የሀገሪቱን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት በተለይም የአየር ክልልን በሚገባ ከማስከበር አንጻር መጠበቅን የግድ አድርጎታል፤

እነዚህ ተግባራት መፈጸሙ መንግሥት ሰብአዊ ርዳታን ለተረጂዎች በተገቢው ሁኔታ እንዲያሣልጥ የሚረዳው ይሆናል፤

በአንድ በኩል እነዚህን ዓላማዎች እያስፈጸመ በሌላ በኩል ደግሞ በአፍሪካ ኅብረት አማካኝነት ለሚካሄደው የሰላም ውይይት ዝግጁ መሆኑን የኢትዮጵያ መንግሥት በድጋሚ ያረጋግጣል፤

ዘላቂ ሰላም እንዲመጣ ሁለንተናዊና በንግግር ላይ የተመሠረተ ስምምነት አስፈላጊ መሆኑን መንግሥት ያምናል፤

የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አግባብነት ባላቸዉ አሠራሮችና በዓለም አቀፍ የሰብአዊ ሕጎች በጽኑ የሚገዛ መሆኑን መንግሥት ግልጽ ለማድረግ ይፈልጋል፤

ንጹሐን እንዳይጎዱ ለመከላከል እንዲቻል የኢትዮጵያ የመከላከያ ሠራዊት ጦርነቱ በከተሞች ውስጥ እንዳይደረግ ጥንቃቄ እያደረገ ይገኛል፤

ይሄንን በጽኑ ለመፈጸም እንዲቻልም ለሁሉም ተዋጊ አሐዶች ጥብቅ መመሪያ ተላልፏል፤

ከዚህም ባሻገር በመንግሥት ቁጥጥር ሥር በሆኑ አካባቢዎች ሰብአዊ ርዳታ በተሻለ መንገድ መቅረብ እንዲችልና የርዳታ ሠራተኞች ደኅንነት የተጠበቀ እንዲሆን መንግሥት ከርዳታ ድርጅቶች ጋር አብሮ ለመሥራት ዝግጁ ነው፤

ሕወሐት ንጹሐንን እንደ ጦር መከላከያ የመጠቀምና ሲቪል ተቋማትን ለወታደራዊ ሠፈርነት የመጠቀም የቆየ ልማድ አለው፤

ስለሆነም ሕዝቡና የርዳታ ሠራተኞች ራሳቸውን ከሕወሐት ወታደራዊ ተቋማት እንዲያርቁ የኢትዮጵያ መንግሥት ጥሪ ያደርጋል፤

የርዳታ ሠራተኞችን ጨምሮ በሲቪሎችን ላይ ለሚደርሰው ማንኛውም ጉዳት መንግሥት ኀዘኑን በዚህ አጋጣሚ ይገልጣል፤

እውነቱን ለማወቅና ያልተገደበ የርዳታ ተደራሽነትን ለማረጋገጥ እንዲቻል ጉዳቶች ከተከሠቱ የሚያጣራ ይሆናል፤

በትግራይ ክልል የሚገኙ ዜጎቹን ደኅንነት ለመጠበቅ በሕግ የተሰጠውን ሕገ መንግሥታዊ ግዴታውን ለመወጣት የኢትዮጵያ መንግሥት ያለውን ዝግጁነት ያረጋግጣል፤
