አንደኛ ያ ካልቸር የህዝቡን የኑሮ ዘዬ በሁሉም መልኩ ይገልጻል፣ ያንጸባርቃል፣ እነዚያን ዘዬዎች ይጠብቃል፣ ይንከባከባል!
ሁለተኛ ያ ካልቸራር ኢኮሎጂካል መሆን አለበት ። ያ ካልቸር ሕዝቡንና ኢንቫይሮንሜንቱን እንደ አንደ ተደጋጋፊዎች በማሰር ሕዝቡ እንደ ባህል አፈሩን፣ አየሩን፣ እንሰሳውን፣ እጸዋቱን እንደ ባለቤት ሃላፊ ሆነው መንከባከብ አለባቸው ። ይህን የማያደርግ ካልቸር ጥሩ ሊባል አይቻልም።
ሶስተኛው ያ ካልቸር መንፈሳዊነትን ማካተት አለበት ።
አራተኛ ያካልቸር ፈጠራን፣ ለውጥን፣ እድገትን የሚቆሰቁስ፣ የሚረዳ፣ የሚያበረታታና ዲማንድ እሚያደርግ መሆን አለበት ።
ይህን ሁሉ ለማለት የጎተጎተኝ ባህላዊው የመስቀል አዳብና የወጣት ወንድና ሴት መተዋወቂያና መተጫጫ በሆነው ባህል ዙሪያ ሚስ (ወይዘሪት) አዳብና የሚባል የልጃገረዶች የቁንጅና ውድድር ሊጀመር መሆኑን አንብቤ ነው ። በቃ ይህ ነው ካልቸራል ኢኖቬሽን፣ ፈጠራ ። ክሬቲቪትና አንድን ባህል ከዘመኑ ጋር ማዘመን ማለት!!!