እኔ ሆረስ እጅግ ቀደም ብዬ የዚህ ጦርነት ታሪክ መጨረሻ ላይ እንዴት ይጽፋል? ብዬ ሳበቃ 'ተዋግተው ተዋግተው ውጊያ አቆሙ' ተብሎ በታሪክ ይመዘገባል ብዬ ነበር ።
ምን ማለቴ ነው? ጦርነት በአምጽ የሚካሄድ ፖልቲካ ነው ። ማለትም ጦርነት ፖልቲካ ነው። የፖለቲካ አላማዎች ቢያንስ አራት ናቸው፤ (1) ስልጣን/ሃይል፣ (2) ገንዘብ/ሃብት፣ (3) ዝና/ስም/ሬፑቴሽ፣ (4) ክብር/ማንነት ናቸው።
ስልጣን ማለት የመወሰን ሃይል ማለት ነው ። ማን ምን ያገኛል፣ ይደርጋል? ማን ስንት እና እንዴት ያገኛል? ማ ምን መሆን አለበት? መወሰን መወሰን መወስን !!!!! የተቀሩት ግልጽ ናቸው ክብር ወይም ዲግ ኒቲ የማንነት መከበር ማለት ነው ።
ስለዚህ የጦርነት ተግባር እነዚህን አላማዎች በጉልበት ማስፈጸም ነው ። ሰላም ሰላም የሚባለው ባዶ ቃል ነው !!! ቡና ላይ ተቀምጠው የላይኞቹን አራት ፍላጎቶች ማን ምን ይድረሰው ብለው የሚነጋገሩ የሰለጠኑ ሕዝቦችና በእውቀት የሚመሩ፣ በሳይንስ የሚገዙ፣ ሰዎች ናቸው ። ቀድሞውኑ ዉጊያ አይሄዱም፣ ችግራቸውን በንግግር ስለሚጨርሱ ማለት ነው።
ስለዚህ የወልቃይት መሬት የማነው የሚለው የሃብት/ሪሶርስ ባለቤትነት ውሳኔ በአመጽ ለመተግበር እየተዋጋ አንድ ሰው ስለሰላም ሊያወራ አይችልም ።
መጀምሪያ ማንኛው ፖለቲካ አለ ጦርነት መተግበር መመሪያ ያደረገ ስልጡን እንሰሳ ብቻ ነው ስለሰላም ማውራት የሚችል ።
አይ ፖለቲካዬን በጉልበትና አመጽ ነው የምከውን ያለ ሰው ደሞ በአንጻሩ ሌላው ወታደር አቁሙ ይዋጋዋል ። አንዱ ወገን በጉልበት አሸንፎ ስልጣን፣ ሃብት፣ ዝናና ክብር ቢቀማ እንኳን የሁለቱ ተፎካካሪዎች ጥብ አይፈታም ። የተሸነፈው ለግዜው ቤቱ ሄዶ ለሚቀጥለው ዉጊያ ይዘጋጃል ። የፖለቲካ አላማ ፍትሃዊ በሆነ ተስማሚ መንገድ ስላልተቋጨ ማለት ነው።
ለዚህ ነው ታሪክ ተዋገተው ተዋግተው ዉጊያ አቆሙ ብሎ የሚደመድመው ። ጦርነት ተዋግቶ ማሸነፍና የፖለቲካ አላማዎችን ፍላጎቶችን ሁለቱ ተገዳዳሪዎች በሚቀበሉት መንገድ ምፍታት እንደ ቀናን ለሊት የተለያዩ ናቸው!
ስለዚህ እስቲ ከናንተ መሃል ትህነግ የሚፈልገው ስልጣን/ ሃይል፣ ሃብት፣ ዝናና ክብር ምን ምን እንደ ሆኑ ነገሩን???????? በተመሳሳይ መንግስት ወይም ብልጽግ ና የሚፈልገው ስልጣን/ሃይል፣ ሃብት፣ ዝናና ክብር ምን ምን እንደ ሆኑ ነገሩን???????? እናም አንዱ ቢያሸንፍ በጉልበት የሚቀማቸውን ስልጣኖች፣ ሃብቶች፣ ዝናዎችና ክብሮች ብትጠቁሙን
The New Africa led negotiation - by Obasanjo , Kenyatta, & Mlambo-Kguka of South Africa.....
https://www.yahoo.com/news/ethiopia-gov ... 10282.html
