Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 15480
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

ኦነግ-ብልጽግና መቀሌን በድል ጠቆጣጥሮ ተደስቶ ከመጨፈር በበለጠ ሁኔታ ዐርበኛ ፋኖ ዘመነ ካሴን ለዕርቅ ብሎ አታሎ በመያዙ በደስታ ፈንድቶ ሊሞት ነው። የህጻን ደስታ

Post by Abere » 21 Sep 2022, 15:20

ኦነግ-ብልጽግና መቀሌን በድል ጠቆጣጥሮ ተደስቶ ከመጨፈር በበለጠ ሁኔታ ዐርበኛ ፋኖ ዘመነ ካሴን ለዕርቅ ብሎ አታሎ በመያዙ በደስታ ፈንድቶ ሊሞት ነው። የህጻን ደስታ - የዘመነ ካሴ አላማ በሚልዮኖች መካከል ቀጥሏል እሱን በክህደት ማታለል አትችሉም።

በመጀመሪያ ዘመነ ካሴ በጦርነት እንደ ግለሰብ አሸንፏቸዋል- በርካታ የኦሮምያ ልዩ ሃይል እና ኦነግ-መከላከያ ሰራዊት አንድ ሰው ለመያዝ ሲሉ ብቻ በመቶዎች እንደ ቅጠል ረግፈው ቀርተዋል። 1 ዘመነ በ300-400 ኦሮሞ ልዩ ሀይል ሞት። በመቀጠል የብልጽግና -ኦነግ መንግስት ነኝ ባይ ፍርሃት ብቻ ሳይሆን ከሃዲ መሆኑን በተደጋጋሚ አረጋግጧል። አስታርቁኝ ከዘመነ ጋር በማለት ሽማግሌዎች እግር ላይ ወድቆ ካገኘው በኋላ ማረኩት ማለት የፈሪ ፈሪ ነው። ዛሬ በየመገናኛው ውታፍ ነቃዮችን ጨምሮ የደስታው መግለጫ መብዛት ይገርማል። መቀሌ በድል የገባ ነው የመሰለው ኦነግ-ብልጽግና። መቸስ የብ አድን ሰዎች ለዚህ ስራቸው የደሞዝ እና የደረጃ ዕድገት ይጠብቃቸዋል።

ዘመነን መያዝ የአማራ ህዝብ ትግል ያቆማል ማለት አይደለም። አማራ የበለጠ እራሱን መንግስት ነኝ የሚለውን መሰሪ ጥላት እንድረዳ ይረዳዋል። የድያብሎስን ክፋት የአዳም ልጆች የተረዱን ከእየሱስ ክርስቶስ መስዋዕትነት በኋላ ነው። ክርስቶስ በመካከላቸው አብሯቸው በአካል እያለ እርሱ ስለሚላቸው ብዙዎች ማመን አልቻሉም ነበር። በሞቱ ሞትን ድል ካደረገ በኋል ግን ሚልዮኖች ያስተማረውን ሁሉ አመኑበት - በርካታ ሰማዕታት በአለም ዙርያ አፈራ። እንድሁ ዘመነ ሲል የነበረውን ሁሉ ሌሎች እንድያሳዩለት ሳይሁን እራሱ አሳየው። አገሪቱ ወደሞት የምትመራው በኦነግ ኦሮሙማ መሆኑን፥ ብአድን የአማራ ቁጥር 1 ጥላት መሆኑን፡ ትግሉ በጨለማው የድንቁርና መንገድ በሆነው ኦሮሙማ እና በኢትዮጵያዊያን የፍትህ እና ስልጣኔ አስተሰሰብ ዜጋዎች መካከል ነው።
ብዙ እንደ አብሪ ጥይት የኦሮሙማን ጨለማ የሚገፉ ዐርበኛ ፋኖዎች አሉ። ገና ምኑ ተይዞ ጉዞ?!