Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42902
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የአቢይና ደብረጽዮን ጦርነት ወታደራዊ ግብ የለውም! የፖለቲካ ጦርነት ነው!!

Post by Horus » 28 Aug 2022, 22:58

ማለትም አሁን የሚካሄደው የወያኔ ወረራም ሆነ የአቢይ መልሶ ማጥቃት ዉጊያዎች ናቸው እንጂ ጦርነቱ ፖለቲካ ነው ወታደራዊ አይደለም። አቢይ አህመድ ትህነኝ በጦር ግምባር ቢያሸንፍ እንኳ የፖለቲካ ድል አይሆንም ። ትግሬዎች ድሮም እስትራተጂ አለነበራቸውም ዛሬም ያው ነው። ታክቲካ ሎጂስቲክስ ለመዝረፍ ነው ይህን ሁሉ ህይወት የሚገብሩት ።

ሌላ ፖስት ላይ እንዳልኩት አቢይ ትህነግን በፖለቲካ ሊያሸንፍ የሚችለው ትግሪዎች ያዋቀሩትን የዘር ሴር በሰባብርና ትግሬን ከክልልነት ወደ ድሮ ጠ/ግዛት ቢለውጥ ነበር ። አሁን አቢይ እራሱ የቆመበትን ምንጣፍ ሊጎትት አይችልም፣ እራሱ አብሮ ስለ ሚወድቅ! ይህ ነው ሳይንሱ!

ከዚህ ባለፈ ትግሬም ተዋግቶ አዲሳባን ልይዝ አይችልም! መገንጠል ከፈለገ ደሞ አዳነች አቤቤ የዛሬ አመት እንዳለችው አንቀጽ 39 ጠቅሶ መገንጠል ይችላል። የጦርነቱ አላማ የትግሬ መገንጠል አይደለም ። አቢይም ነገ ቢያሸንፍ ትግሬ ራሱን የቻለ ክልል ስለሆነ ስልጣኑን ለትግሬዎች አስረክቦ ወደ አዲሳባ መመለስ ይኖርበታ ።

ስለዚህ ይህን ዉጊያ እንደ ጦርነት የምትመለከቱ ፍጹም ስህተት መሆናችሁን ተገንዘቡት!

የድርድር ጥምካሬ ምግኛ መንገድ ነው ለምትሉ ደሞ መልሱ ቀላል ነው ። የድርድሩ ግብ እራሱ ምን እንደ ሆነ ግልጽ አይደለም! ትህነግን ወደ ፒፒ ለመመለስ ነው? ወንጀሎችን ለመያዝ ነው? ፌዴራል መንግስትን ትግሬ ውስጥ ለማስገባት ነው? ምንድን ነው የድርድሩ አላማ? ትህነግ ዝም ብሎ ዲማን መቆለሉን እንደ ቅድመ ሁኔታ ይቀትላል ። ሌላ ቦታ እንዳልኩት ትግሬ ትልቅ ረሃብ ቢገባ ለትህነግ ደስታው ነው!!