8m ·
በቁጥጥር ስር ውለዋል
ለምስራቅ አማራ ፋኖ ምክትል አዛዥ በደረሰው ጥቆማ መሠረት አባላቱን ይዞ ሲከታተል ከቆየ በኃላ ዛሬ 10: 00 ሰዓት አካባቢ ቆቦ ከተማ አስራ ሁለቱንም ተጠርጣሪዎችን መያዙን ገልጿል። የፋኖው ምክትል አዛዥና ባልደረቦቹ ባደረጉት ፍተሻ ተጠርጣሪዎቹ በመኪና ተሳፍረው አቆራርጠው ጠላት ወዳለበት ሊሄድ የነበረ 19 ሚሊየን 7 መቶ ሺ ብር እና ግምቱ የማይታወቅ ቁሳቁስ ከተጠርጣሪዎቹ እጅ እንደተገኘባቸውም የምስራቅ አማራ ፋኖ ምክትል አዛዥ ገልጿል።
ተጠርጣሪዎቹ 7 ወንድ እና 5 ሴት ሲሆኑ ከብሩ በተጨማሪ ግምቱ ምን ያህል ብር ሊያወጣ እንደሚችል ያልታወቀ የምግብ ቁሳቁስ የሆነ የተፈጨ እና ያልተፈጨ በርበሬ ፣የተሰፉ እና ያልተሰፋ የጣቃ ጨርቅ ፣የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ እና ሌሎችን ይዘው ተገኝተዋል። ከተጠርጣሪዎቹ አብዛኛወቹ የተፈናቃይ መታወቂያ ያላቸው ናቸው። ባለ ሁለት መቶ የኢትዮጵያ የብር ኖት ከሁሉም ተጠርጣሪወች ጭኖቻቸው ላይ በፕላስተር በማሰር እንዲሁም በተለያዬ ኪሶች ብሮቹን ደብቀው መገኘቱንም ተመልክተናል። ሴቶቹ ተጠርጣሪወች ደግሞ የጡት ማስያዣቸዋን በመሠንጠቅ ብሩን ውስጥ አስገብተው በመስፋት ጡታቸው ላይ በማሰር ለማሳለፍ ሲሞክሩ ነበር የተያዙት።


