Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42901
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Noble Amara: ስለ እንጊጫ እና ሻደይ

Post by Horus » 23 Aug 2022, 01:05

መጀምሪያ እንጊጫ የሚለውን ስም የሚጠቀሙት የት አካባቢ ያሉት አማሮች ናቸው? በጉራጌም (በተለይ በክስታኔ) እንጊጫ ነው የምንለው ። ዘፈን ሁሉ አለው! ከሆሳዕና ጋር ተያይዞ ማለት ነው። በትክክል ሃይማኖታዊ በዓል ነው ።

ሻደይና አሸንዳ ብላችሁ የምትከራከሩበት በጉራጌ የፍቃቆ ማይ ወይም የፍቃቆ ገዳ ይባላል። ገዳ ማለት በጉራጌኛ ግዜ ማለት ሲሆን ማይ እለት ማለት ነው ። ፍቃቆ ባማርኛ አክርማ ይባላል ። ለሙያ የደረሰች ሴት ሰንጥቃ ልዩ ልዩ ስፌት (ኢፋ፣ እንቅብ፣ ሰፌድ፣ ሌማት፣ መሶብ) የምትሰራበት የሳር አይነት ነው ።

ሻደይ ጸደይ ማለት እንደ ሆነ ሌላ ሃረግ ላይ ጠቅሻለሁ።

ልክ ለጋብቻ የደረሱ ልጃገረዶች አዳብና (ሎሚ መዋጊያ በዓል) እንደ ሚወጡት እስከ መስቀል ማብቂያ ድረስ የሴት ጓደኛሞች (ዬጎስቴዎች) ሹርባ ተሰርተው አበባና ፍቃቆ የሚለቅሙበት በዓል ነው ። ከዚህ በታች ምናሉሽ ረታ ድንቅ አድርጋ የዛሬ አመት ዘፍናለታለች፣ አዚያው አገር ቤት! ዬጎስቴ ንግስቴ ማለት ሲሆን የቅርብ ጓደኛ ልጀገረዶች እርስ በርሳቸው የሚጠራሩበት ስም ነው። ወንዶች ሞጎ። ሳውሜ፣ መሪ እንባባላለን እንደ ጓደኝነታችን ቅርበት!


Last edited by Horus on 23 Aug 2022, 01:22, edited 1 time in total.

Noble Amhara
Senior Member
Posts: 13728
Joined: 02 Feb 2020, 13:00
Location: Abysinnia

Re: Noble Amara: ስለ እንጊጫ እና ሻደይ

Post by Noble Amhara » 23 Aug 2022, 01:16

•የጎጃም አማራ ኢንጊቻን ያከብራል።
•በምእራብ ሸዋ የሚገኙ የጋፋት ሴቶችም የእንጊቻ በዓል አባይ ወንዝ አካባቢ ያከብራሉ(Muger)

Horus
Senior Member+
Posts: 42901
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: Noble Amara: ስለ እንጊጫ እና ሻደይ

Post by Horus » 23 Aug 2022, 01:35

Noble Amhara wrote:
23 Aug 2022, 01:16
•የጎጃም አማራ ኢንጊቻን ያከብራል።
•በምእራብ ሸዋ የሚገኙ የጋፋት ሴቶችም የእንጊቻ በዓል አባይ ወንዝ አካባቢ ያከብራሉ(Muger)
ይህ ፍጹም አስገራሚ ነው ።አንድ ቀን ወደፊት የምናቋቁመው የጉራጌ ምርምር ኢንስቲቲዩት ይህን ጉድ መርምሮ መዘገብ አለበት ። ባህል አይሞትም የሚባለው ይህ ነው ። አሁን ጉራጌና ጋፋት እንዴት አንድ ባህል የነበራቸው ሕዝቦች እንደ ነብሩ ታያለህ ። እነዚህ ጎጃሜዎች እንጊጫ ብለው የሚያከብሩት ልክ እኛ አዳብና የምንለው ነው። የነገሩ ትክክለኛነት የሚመሰክረ ይህ ምስራቅ ጎጃም መሆኑ ነው ። እዚያ ነው ጋፋቶች ከእንደ ገብጣን ከዛሬ አዲስ አለማ ግንደ በረት ሸሽተው አባይን የተሻገሩት ። ይህ ነው የእንጊጫ ምስጢር!

Noble Amhara
Senior Member
Posts: 13728
Joined: 02 Feb 2020, 13:00
Location: Abysinnia

Re: Noble Amara: ስለ እንጊጫ እና ሻደይ

Post by Noble Amhara » 23 Aug 2022, 01:40

ሁሉም ጋፋት ወደ አማራ አላመለጠም ብዙዎች በምዕራብ ሸዋ ቆይተው ኦሮምኛ መናገር ጀመሩ

Continued

In ፌቴጋር Province in todays ሰሜን ሸዋ ዞን but actually ምስራቅ ሸዋ you can see how Abysinnians used to be one the dance of ደቡብ አማራ is very similar to ጉራጌ of Aymallal Province according to 15TH century records


Horus
Senior Member+
Posts: 42901
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

Re: Noble Amara: ስለ እንጊጫ እና ሻደይ

Post by Horus » 23 Aug 2022, 02:06

Noble Amhara wrote:
23 Aug 2022, 01:40
ሁሉም ጋፋት ወደ አማራ አላመለጠም ብዙዎች በምዕራብ ሸዋ ቆይተው ኦሮምኛ መናገር ጀመሩ

Continued

In ፌቴጋር Province in todays ሰሜን ሸዋ ዞን but actually ምስራቅ ሸዋ you can see how Abysinnians used to be one the dance of ደቡብ አማራ is very similar to ጉራጌ of Aymallal Province according to 15TH century records

በተለይ ምንጃር! እዚያ ምንጃር እንዶዴ የሚባል አገር አለ ። አማውቴ በሚባለ ሶዶ እንዶዴ የሚባል መንደር አለ ። ወደ ኦሮሞነት ተለወጡ ያልከውም ትክክል ነው ። ተውና ጋፋት ጨቦ ጉራጌ ባብዛኛው ኦሮሞኝ ተናጋሪ ሆነ አይደል እንዴ ። የወንጪ ኦሮሞች እንሰት ተክለው ቆጮ በልተው የሚኖሩትን አየሃቸው አይደል? ቤታቸው የቤት እቃቸው ቁርጥ ጉራጌ አንድም ሳይለወጥ ማለት ነው ። ቋንቋቸው ብቻ የተለወጠው ።


Noble Amhara
Senior Member
Posts: 13728
Joined: 02 Feb 2020, 13:00
Location: Abysinnia

Re: Noble Amara: ስለ እንጊጫ እና ሻደይ

Post by Noble Amhara » 23 Aug 2022, 02:29

Minjarie Atse Zara Yacob(1399 – 26 August 1468) and Minjarie Atse Fasilades (Ge'ez: ፋሲልደስ; Fāsīladas; Born 20 November 1603 – Died 18 October 1667 who founded Gondar in Dembia) visited Lake Wonchi according to this Wonchi Local in ምዕራብ ሸዋ



and can someone tell me why does Waliso Habtegiyorgis Dinagade look like Berhanu Nega!



Post Reply