Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Wedi
Member+
Posts: 8649
Joined: 29 Jan 2020, 21:44

BBC አማርኛ:- በትግራይ አንድ ኩንታል ጤፍ ከ17 ሺህ ብር በላይ እየተቸበቸበ ነው!!

Post by Wedi » 21 Aug 2022, 07:33



በትግራይ አንድ ኩንታል ጤፍ ከ17 ሺህ ብር በላይ እየተጀበጀበ ነው!!

:P

BBC አማርኛ

በትግራይ አንድ ኩንታል ጤፍ ከ17 ሺህ ብር በላይ መሆኑን ነዋሪዎች ተናገሩ

በትግራይ አንድ ኩንታል ጤፍ ከ17 ሺህ ብር በላይ መሆኑን ነዋሪዎች ተናገሩ

ሁለት ዓመት ሊሞላው ጥቂት ወራት የቀረው ጦርነት በተቀሰቀሰባትና መሰረተ ልማቶች በተቋረጡባት ትግራይ ውስጥ አንድ ኩንታል ጤፍ እስከ 17 ሺህ ብር እየተሸጠ እንደሚገኝ ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናገሩ።

በክልሉ ውስጥ በእርዳታ አቅርቦት ሥራ ላይ ተሰማርተው የሚገኙ ግለሰቦችም አንድ ኩንታል ጤፍ ከ15 እስከ 17 ሺህ ብር እየተሸጠ እንደሆነ ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።

ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የአንድ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች ሠራተኞች እንዳሉት ክልሉን እያስተዳደሩ ያሉት ባለሥልጣናት በጤፍ የመሸጫ ዋጋ ላይ ተመን ማውጣታቸው የዋጋ ጭማሪውን እንዳባባሰው ተናግረዋል።

የመቀለ ከተማ ነዋሪ የሆነው ዳንኤል በአሁኑ ወቅት ሕዝቡ በአስከፊ የኑሮ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኝ ገልጾ፤ በተለይ የጤፍ ዋጋ ከሕብረተሰቡ አቅም በላይ ሆኗል ብሏል።

ለቢቢሲ አስተያየተቸውን የሰጡ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የግረሰ ሰናይ ድርጅቶች ሠራተኞች እንደሚሉት፣ በአሁኑ ወቅት የጤፍ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ እንዲጨምር በክልሉ የተጣለው የመሸጫ ዋጋ ተመን እጥረት እና የዋጋ መናርን ማስከተሉን ይናገራሉ።

“ጤፍ እጅግ በጣም ተወዷል። ነጋዴዎች በማኅበረሰቡ ላይ ጨክነዋል። የሕብረተሰቡን ሁኔታ ያላገናዘበ ተግባር ነው እየፈጸሙ ያሉት። ከባድ ሁኔታ ነው እያሳለፍን ያለነው። ብዙዎች እንጀራ መመገብ የማይችሉበት ደረጃ ላይ ደርሰናል” በማለት ዳንኤል ያለውን ሁኔታ አስረድቷል።

ሌላኛው በርኽ የተባለ አስተያየት ሰጪ በበኩሉ “ረሃብና ድርቅ አለ። ሕዝቡ ያለውን ተካፍሎ ለመኖር እየሞከረ ነው። ሰዎች ከትግራይ ውጪ ከሚገኙ ቤተሰቦቻቸው እንደምንም ብሎ የሚደርሳቸው ገንዘብ ምንም ነገር ሊገዙበት አልቻሉም። በተለይም የጤፍ ዋጋ የሚቀመስ አይደለም” ብሏል።

በርኽ እንደሚለው በአሁኑ ጊዜ ያለው የጤፍ ዋጋብቻ ሳይሆን የስንዴና የስንዴ ዱቄት ዋጋም ከሕብረተሰቡ የመግዛትአቅም ጋር በፍጹም የሚመጣጠን አይደለም።

“አንድ ሰው ሁለት እና ሦስት ሺህ ብር ከቤተሰብ ተልኮለት 25 ኪሎ ጤፍ እንኳን መግዛት የማይችልበት ጊዜ ላይ ነው ያለነው። ሩብ ኩንታል ለመግዛት ከ4 ሺህ ብር በላይ ሊኖርህ ይገባል” ሲል ጨምሮ ገልጿል።



https://www.bbc.com/amharic/articles/c3g12vpw4qno