Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

በነሐሴ 21 በጎንደር ከተማ ሊካሄድ የነበረው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን 14ኛ ጠቅላላ ጉባኤ በአዲሱ የጦርነት መቀስቀስ ፍራቻ ወደ አዲስ አበባ ተዛውሯል

Post by sarcasm » 20 Aug 2022, 08:55

የጎንደር ከተማ አሥተዳደር የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን የኢመርጀንሲ ኮሚቴ ያስተላለፈውን የጉባኤ ቦታ ለውጥ ውሳኔ እንደማይቀበል አስታወቀ።
Please wait, video is loading...
የከተማ አስተዳሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ዘውዱ ማለደ ለፌደሬሽኑ በጻፉት ደብዳቤ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን በ2014 ዓ.ም የምርጫ ጠቅላላ ጉባኤ ከነሐሴ 21 እስከ 22/2014 ዓ.ም ድረስ በጎንደር ከተማ እንደሚያካሂድ በ12/12/2014 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ ዝግጅት እንዲደረግ በማሳወቁ ወደ ሥራ መገባቱን አስታውቀዋል።

በዚህ መሠረት በከተማ ደረጃ የጉባኤ ቅድመ ዝግጅት ተጠናቆ ሆቴሎች እንዲያዙ ተደርገው፤ ሆቴሎችም የነበራቸውን ሌላ ውል ሰርዘው ለጉባኤው ትኩረት ሰጥተው፣ ገንዘብ ወጭ አድርገው አብዛኞቹ ሆቴሎች ዝግጅት ማጠናቀቃቸውን ገልጸዋል።

የጎንደር ሕዝብም ጉባኤው ጎንደር ላይ እንደሚካሄድ የእግር ኳስ ፌድሬሽን በሚዲያ በገለጸው መሠረት ተደስቶ ቅድመ ዝግጅት በማድረግ እንግዶችን ለመቀበል ተዘጋጅቶ እየጠበቀ በአለበት ሁኔታ፤ በአጠቃላይ የከተማው አስተዳደር እና ሕዝብ ጉባኤው በመልካም ሁኔታ ተጀምሮ በመልካም ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የተለያዩ ኮሚቴዎችን በማደራጀት በቂ ዝግጅት ማድረጉን አስገንዝበዋል።

ለዚህም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌድሬሽን የሱፐርቪዥን ልዑካን ቡድን 3 ኮሚቴ ያለው ወደ ጎንደር ልኮ በመልካም ቅድመ ዝግጅት ላይ እንዳለ ማረጋገጡን ጠቅሰዋል።

ሕዝቡና ከተማ አስተዳደሩ የጉባኤውን ቀን በጉጉት እየተጠባበቀ በአለበት ወቅት የከተማ አስተዳደሩም የክልል መስተዳድሩም በማያውቀው ጉዳይ ባልተጨበጠ ምክንያት ጎንደር ላይ ሊካሄድ የተወሰነው ውሳኔ የኢመርጀንሲ የእግር ኳስ ፌድሬሽን ኮሚቴ ጉባኤውን መሰረዙ ተገቢ ያልሆነ እና የጎንደር ከተማ አስተዳደርንና ስፖርት አፍቃሪውን ሕዝብ ያስከፋ ውሳኔ መሆኑን ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው አስገንዝበዋል።
ውሳኔውንም ከተማ አስተዳደሩ እንደማይቀበልና እንደገና እንዲታይ ጠይቀዋል፡፡