ኢማጂን እንግዲህ በዚህ ዘመን እራሳቸውን የኢትዮጲያ ጠባቂ ሌላውን ደግሞ ከአፍራሽነት ተጠባቂ አድርገው ይገልፃሉ።
ያልገባችው ግን ዘመኑ መቀየሩ ነው። እነሱ የሀገር ጠባቂ ሌላው ደግሞ የሀገር ስጋት ሆኖ በመሳቀቅ እና በማሳቀቅ የሚኖርበት ዘመን አክትሟል። በጋራ ተከባብረህ በእኩልነት ትኖራለህ ካልሆነ ደግሞ "አብሮ መኖሩ ካላለልን እስኪ እንሞክረው ተለያይተን" ተባብለህ ሀገር ትመሰርታለህ።
እራሳቸው የሀገር አፍራሽ ብለው ይገፉሃል፣ ገፍተውህ ሀገር ለመሆን ስታስብ ደግሞ ያዙኝ ልቀቁኝ ይላሉ። መገፋፋት ይቅር ሀገር እንታደግ የሚለው ቢቀድም ለኢትዮጲያ ያዋጣታል።
የለም መገፋፋት ይሻለናል ከተባለ ግን ከሁሉም በላይ ሀገር አልባ የሚሆነው ምርጥ ኢትዮጲያዊው ነው። ሌላው ቢቀር አዲስ አበባ ጠቅልላ ፊንፊኔ ስትሆን ፓስፖርት አልባ ዜጎች ሚልዮኖች ይሆናሉ። ሀገርህ የት ነው ሲባል ኢትዮጲያ እንዳይል መከባበር አቅቶት አፍርሷታል። አዲስ አበባ እንዳይል ባለቤት አላት። ይህ ከሚሆን እንደ ህዝብ እንከባበር!!
Please wait, video is loading...