Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42910
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

በጉራጌ ማህበረሰብ የመጨረሻው የበላይ ስልጣን እና ሃይል የጉራጌ ባሊቆች (ሽማግሎች) ሸንጎ ነው

Post by Horus » 03 Aug 2022, 23:46

ይህ የጉራጌ ሴራ ይባላል። የጉራጌ ስርዓት ማለት ነው ። ስርዓት በግዕዝ ሴራዎች ማለት ነው (የብዙ ስም)፤ የስርዓት ነጠላ ሴራ የሚለው ቃል ነው ። ስለሆነም አንድ ነጠላ ሲስተም ስርዓት ሳይሆን ሴራ ነው ። ስለሆነም በጉራጌ ሶሺያል ሲስተም አንድ የቤተሰብም ሆነ የማህበረሰብ ጉዳይ የመጨረሻ ዉሳኔ የሚሰጡት የጉራጌ አገር ሰነቻዎች ባሊቆች ናቸው ። በቅርቡ የጉራጌ ክልልላዊ መንግስት ሲደራጅም የሚሆነው ያ ነው ። ሕዝብ በአንድ ሰው አንድ ድምጽ የመረጣቸው የጉራጌ ፓርላማ ይኖራል። ለብቻው አስፈላጊና ፓርላማው መፍታት ያልቻላቸው ጉዳዮችን የሚፈታው ይህ የሽማግሎች ሸንጎ ነው ። ባሁኑ ሰዓት የብልጽኛ መንግስት ሰራተኛ የሆኑት አስተዳዳሪዎች አሉ። ጉራጌ የመረጣቸው የጉራጌ ምክር ቤት አለ። ሁለቱም የጉራጌ ባሊቅ ሸንጎ ከወሰነው ውጭ ማድረግ አይችሉም ። ባሊቅ ማለት ማለቅ (ማሊክ በአረብኛው) የሚለው ጽንስ ሲሆን ታላቅ፣ የበላይ፣ የላቀ ማለት ነው ። ድሮ ሜልኮ ማለት ንጉስ ወይም ንጋሲ ማለት ነበር ። ይህ ነው የጉራጌ ሴራ! ኤቦ !