Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum

Ethoash
Senior Member+
Posts: 26144
Joined: 20 Apr 2013, 20:24

Re: Should Ethiopia shut down Ministry of Tourism and hire this guy instead?

Post by Ethoash » 02 Aug 2022, 10:12

አቶ ታምሩ ወድ እኔ ኤርትራዊ ወንድሜ
በጣም ጥሩ አሳብ ነበረህ ምን ያረጋል ኤርትራዊ ሆነህ በአገርህ እድሉ ስላላገኘህ ለኢትዬዽያ መመኘት ህ ፣ በአንድ በኩል አገር ስሌሌለህ ባዝንም ። ከነዚህ ቡዳዎች በበለጥ ደህና ደህና ነገር ማስብህ ደግሞ ያስደስተኛል።

የቱሪዝም ሚኒስተር ከቀበሌ ጀምሮ እስከከፍተኛ ስራቸው ማስናከል ነው ፣ እንጂ መስራት አይደለም፣ ሰለዚህ ማስናከናቸውን በደንብ እየስሩ አገሪቱን ወደሐላ አስቀርተዋታል። ለምሳሌ ሁለት ነጮች ከስሜን ተራራ ላይ ሊዘሉ ቢመጡ ፣ የጭቃ ሽሙ ፣ ፍቃድ ከኔ ወስዱ ብሎ አታካራ ያበዛል፣ እንግዲህ ያሳያቹሁ ይህ የስማይ ዝላይ አንድ ቱሪስት መሳቢያ መሆኑ ነበር ተሳክቶ ብዙ ቱሪስቶች መጥተው ከስሜን ተራራ ላይ ቢዘሉ፣ ግን የኛ የጭቃ ሹም ሊከለክላቸው ፈለገ፣ ሌላው ደግሞ አንድ ናጄራዊ የስሜን ተራራ ፓርክ ውስጥ ፎቶ ሊያነሳ ሲሞክር ሶስት ሺህ ዶላር (ናጀሪያው ተሳስቶ ሊሆን ይችላል ብር ማለታቸው ይሆናል ዋናው ነገር ገንዘብ ጠይቀዋል)አምጣ አሉት ፣ እንግዲህ ለራሳችን ሊያስተዋወቅልን ቢሞክር በነፃ ገንዘብ አምጣ ማለቱ ምን ጉድ ነው። ሌላው ይህ ናጄሪያ በቦሎ ላይ በፖሊስ ተዋክቦ ነበር እንግዲህ የቱሪዝም ሚኒስተር ፖሊሶቻችንን ማሰልጠን አለበት፣ የአገርን ገፅታ ላለማበላሽት ጥቁር አፍሪካኖችን በክብር መያዝ፣ አለብን ፣ እንደውም ማንኛውንም ስወ በክብር መቀበል አለብን ምንም ልዩነት ሳናረግ ይህንን በስልጠና ማግኘት ይችላል፣ ሌላው ቢቀር ተሳፋሪዎች ቅሬታ ሲያቀርቡ በቶሎ ምላሽ መስጠት አለብን ። እኛ አሜሪካ አይደለንም ፣ ቱሪስቶችን የምንፈልግ እንጂ እነሱ እኛን የሚፈልጉ አይደሉምና ለማንኛውም ይህንን ቪድዬ ተመልከት አምስት ሺህ ተመልካች ብቻ ነው ያለው ። ለምን ማንም ገገማ የውሽት ፖለቲካ ሲያወራ በሁለት መቶ ሺህ ስዎች የምንመለከተው ሲሆን ይህንን ቪድዬ የማናይበት ነገር ይገርመኛል።





ሁለተኛው ደግሞ ስርቆት ነው። አንድ ስው ሆቴላችን አድሮ ንብረቱ ቢስረቅ ማነው ሐላፊነቱን የሚወስደው። እንግዳውም የሁቴሉም ባለቤት በሙሉ ሐላፊነት አለባቸው ። ሐይሌ በየኮሪደሩ ላይ ቪዲዬ ማረግ ነበረበት ማን መጣ ማን ሄደ ለማየት ያንን የሚያክል ሆቴል በቀን ሶስተ መቶ ፣ አራት መቶ ዶላር እያስከፈለ ሴኩሪቲ ካሜራ የለም ማለት ሞኝነት ካልሆነ ጅልነት ነው ። ሐይሌ በጣም ነው በዚህ ያናደደኝ፣ ሲቀጥል በየክፍሉ ለፅዳት የሚገቡትን ስራተኞች ማን እንደሆኑ ማወቅ ያስፈልጋል ማንም ስራተኛ በየክፍሉ እየገባ የፈለገውን ማረግ የለበትም ። ይህ እንዲሆን ደግሞ የበሩ ቁልፍ ዲጅታል መሆን አለበት ፣ ለአንድ እንግዳ አንድ ካርድ በመስጠት ፣ የሚቀጥለው እንግዳ ደግሞ ሲመጣ ኮዱ ተቀይሮ ስለሚያገኘው ቁልፍ አስመስሎ መስራት አይቻልም ። በዚህ በኩል ሐይሌ ትልቅ ጥፋት አርጎዋል ማን ክፍሉ እንደገባ ካላወቀ።

ሞ ፋራህ ደግሞ ሴፍ እንስጥህ ሲባል እንቢ ማለቱ፣ በጣም ወድ እቃዎችን በክፍሉ ማስቀመጡ፣ አፍሪካ አገር ሲመጣ የምን ወርቅ ስዓት ይዞ መምጣት ያስፈልጋል። ስለዚህ ሞ ጥፋት አለበት በተለይ ሐይሌ ሁቴል ከሶስት መቶ ዶላር በላይ ክፍላቹሁ አታስቀምጡ የሚል ማስታወቅያ ስለለጠፍ ፣ የሁቴሉ እግም ስለሆነ ፣ ላይብሊቲው ከሶስት መቶ ዶላር አይበልጥም ማለት ነው። ግን ሞ ጠፋብኝ የሚለው አስር ሺህ ዶላር ነው።

ታድያ ፍርዱ የት ጋ ነው። እኔ እንደሚመስለኝ ሁቴሎች እንሹራንስ መግባት አለባቸው ለዚህ አይነቱ አደጋ፣ ሞ ም እቃዎቹን እንሹራንስ ገብቶ መምጣት ነበረበት። እንሹራንስ ኢትዬዽያ ውስጥ ስለማይታወቅ ፣ የዚህን ግዜ ነው የቱሪዝም ሚኒስተርን የሚያገባው ፣ የቱሪዝም ሚኒስተር አስር ሺህ ዶላሩን ቢከፍል ፣ ወይም ሐይሌ ከታክስ ቢቀነስለት ምን ነበረበት ፣ የአገራችን ስም ከመጥፋቱ ይተርፍ ነበር። እንዳልኩት ቪድዬ ባለመኖሩ ተጠያቂ ያረገናል በኔ ግምት እወነትም ተስርቆ ይሆናል። ስለዚህ ሞን አገራችንን ፕሮሞት እንዲያረግ በሚቀጥለው ግዜ ለሁለት ወር በነፃ ሆቴል ስጥቼሀለው ቢለውስ ፣ ሐይሌ የአራዳ ልጅ ሶስተ መቶ ዶላር የተኛበትን አልከፈለኝም ይላል።

እኔ በጣም ደስ ብሎኝ ነበር ሞ ብቻ በመምጣቱ እንደውም ለንደን ላይ አውቀን እንዲያሽንፍ ብንለቅለት ይሻል ነበር አራዳ ከሆን ለሙክታር ደግሞ ስላሳ እምስት ሺህ ዶላር ስለሚያጣ ያንን መተካትና ኢትዬዽያን ማስታወቅ ፣ ሞ ም ኢትዬዽያ በመምጣቴ ነው ያሽነፍኩት ስለሚል በዙ ብቻ በዙ ሚሊዬን ዶላር ከብዙ ቱሪስቶች እናገኝ ነበር።

ሐይሌ ሞ እንግዶቼን በጠበጠ ብሎዋል ታድያ እንደሞ ያሉትን ስዎች የተለየ ክፍልና የስፖርት መስሪያ ማዘጋጀት አለበት ። ልክ እንደ አንድ ቪላ ቤት ስርቶ ሞን በግሉ እንዲስለጥን ማረግ ይህ ለሞ ሳይሆን ለኢትዬዽያ ትልቅ የቱሪስት መሳቢያ ይሆን ነበር ። ግን ከተለመደው አስተሳስብ ወጭ የሚያስብ የለም ።




አንተ እንዳልከው እነዚህን ዩቱቦችን መደገፍ ታላቅ ጥቅም ይስጣል ። በቲቪ ላይ ማስታወቅያ ለመስራት በጣም ወድ ስለሆነ ፣ የኢትየዽያ አየር መንገድ በነፃ ትኬት ቢስጣቸው ኢትዬዽያ ለመምጣት ምን ይጎዳው ነበር። ቦታ ካልሞላ በተጠባባቂነት ጭኖዋቸው መብረር አየር መንገዱን አይጎዳም ፣ ዩቱበሩ ሄደ አልሄደም ወንበሩን የገዛ ስው ከሌለ ፣ ቀለጠ ማለት ነው። ግን ለዩቱበሩ ከተስጠው ቢቀር ቢቀር አየር መንገዳችንን ያስተዋወቅልናል።

ሌላወ ደግሞ ሐብረተስቡ በጣም ታማኝ መሆን አለብት ነጭ ስለሆነ ብቻ ዋጋ መጫን የለበትም፣ ሌብነቱንም መግታት ባይቻል መቀነስ፣ የቱሪዝም ሚኒስተር የቱሪዝም መዳረሻዎችን በሙሉ ገንዘብ ኢንቨስት በማረግ ቤዚክ የሆኑ ነገሮች እንዲሞሉ ማረግ አለበት፣ ለምሳሌ አፋር እሳት ጎመራው ጋ ፣ ስሙ ጠፋኝ ቦታው ቱሪስቶችን ሲወስድ በቀላኩ በሺ ዎች ዶላር ከአዲስ አበባ ተቀብሎ ነው የሚልካቸው ግን ስንቱ ብር ነው ለአፋር የሚደርስው ፣ በነፃ ቱሪስቶቹ መጥተው ያያሉ ምኑን አፋሮች ተጠቀሙ ግን ቱሪዝም ሚኒስተር በአፋር ላይ ኢንቨስት አርጎ አንድ ትልቅ ሁቴል ቢከፍት እንኩዋን ትንሽ ገንዘቡ ለነሱም ይዳረስ ነበር ፣ እኔ የምለው ክአፋር ከተማ ውጭ ያሉትን የእሳቱ ጎመራ መቃረቢያ ያሉትን ቦታዎችን ነው የምለው ኢንቨስትመት ይፈልጋሉ።

ሌላው ደግሞ የቱሪዝም ሚኒስተርን ከመጠበቅ ፣ በአዲስ አበባ ያሉት ሁቴል ባለቤቶች በአንድነት ገንዘብ በማዋጣት በአንድነት ኢትዬዽያን ማስተዋወቅ አለባቸው ። በየነጠላው ከማስተዋወቅ በአንድነት ከሆኑ ገንዘቡም ይቀንስላቸዋል። ለምሳሌ አንተ ያልከውን ዩቱበር አስር ሺህ ዶላር ቢስጡት ፣ አስር ሁቴሎች ከሆኑ አንድ ሺህ ዶላር ይመጣባቸዋል ደግሞ አምሳ ሁቴሎች ከሆኑ ሁለት መቶ ዶላር ይመጣባቸዋል ማለት ነው።




i AM IN LOVE wit her vioce

Post Reply