Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42911
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

በጉራጌ ክልልነት አቋም ላይ የሕዝባችን ቁጣና የብልጽግናው መሃመድ ጀማል ብልጣብልጥ ምላሽ! ጉራጌን መክዳት ያስከፍላል!! የጉራጌ የበላይ የጉራጌ ሽማግሎች ናቸው!

Post by Horus » 25 Jul 2022, 14:00

ይህን መልስ ልብ ብላችሁ ስሙት ። እሱ የጉራጌ ምክር ቤት ወስኖ የላከው እንደ ማስፈጸም ለራሱ ስልጣን ሲል ጉራጌን ከሸጠ በኋላ አሁን ስሙት ። የከለስተር ሃሳብ የብልጽግና ፓርቲ ያመጣው ጉራጌ በክለስተር ይደራጅ የሚሉት ወገኖች ማለትም ጥቂት ስልጣንና ገነዘብ የተሰጣቸውና ጉራጌ መሆን አንፈልግም የሚሉት ጥቂት የማረቆና ቀቤና ኢሊቶች እንዲደራጁ እድል ለመስጠት ነው ይላል መሃመድ ጀማል በደምብ ስሙት ። ላይ ላዩን በህዝቡ ቁጣ የደነገጠ አስመስሎ ግን ጸረ ጉራጌ ቡድን ተደራጅቶ ጉራጌን በክላስተር እንዲጨፈልቅ ግዜ ለመግዛት ነው።

ይህ መሃመድ ጀማል የሚባል ሰው ለጉራጌ ሕዝብ ድምጽ፣ ፍላጎትና ውሳኔ ሳይሆን ጉራጌ በካልስተር ምናምን ተበትኖ ጠፍቶ ማየት የሚፈልግ የሌቦች መታጎሪያ የሆነው የሙሰኛው ብልጽግና ስራ አስፈጻሚ ነው ። ስለ ጉራጌ ብሄርና ሕዝብ ከራሳቸው በላይ የብልጽግና ፓርቲ ሌቦችና ሙሰኞች ይበልጥ ያውቁለታል የሚለው የመሃመድ ጀማል ተጨፈኑ ላሞኛቹ ከማሳዘኑም በላይ ያስቃል!

የጉራጌ ሕዝብ የጉራጌን ክልልነት ጥያቄ አስፈጽም ብሎ ነው የላከህ! ያ ነው ያንተ ስራ! ከዚያ አልፈህ ጉራጌን ብትከዳ ካልስተሩ አይፈጠርም፣ አንተም በጉራጌ ሴራ ከማህበረሰቡ እንድትወገድ ትደረጋለህ! ክላስተርነት ለጉራጌ የሚቀርብ አማራጭ አይደለም !! ሰብኛ ማለቅ ዬውሁን! ኬር ለኢትዮጵያ!


Last edited by Horus on 25 Jul 2022, 14:33, edited 1 time in total.


Post Reply