Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42915
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

መንግስትና ብልጽግና የሚባሉ 2 የሌቦችና ወንጀለኞች ድርጅቶች

Post by Horus » 14 Jul 2022, 14:39

የጎሳው የቢሮ ከበርቴ የሌቦችና ወንጀለኞች ድርጅት ነው ።
ሌብነት ሁሉ አንድ ነው ።
የኢኮኖሚ ሌብነት፣
የፖለቲካ ሌብነት፣
የመብት ሌብነት፣
የስልጣን ሊብነት፣
የዝና ሌብነት፣
የማንነት ሌብነት፣
የታሪክ ሌብነት!

የተፈናቀሉ ሰዎች መነገጃ ስለሆኑ ሆን ብለው ህዝብ የሚያፈናቅሉ በሞት መቀጣት አለባቸው ።

ለተፈናቀሉ ሰዎች የተመደበን ምግብና ልብስ ሰርቀው የሚሸጡ፣ የሌሉ ተፈናቃዮችን ፈብርከው የህዝብ ሃብት የሚዘርፉ በሞት የቀጡ።

ማዘጋጃ ቤትን እንደ ማፊያ የሌብነት ድርጅት በመጠቀም በቁጠባ ቤት ፈላጊ ላይ 200ሺ ጉቦ የሚሰበስቡና ህጋዊ ቤት ገዥዎች ፋይል የሚያጠፉ በሞት ይቀጡ።

የህግ ጠበቃ ተብለው፣ ዳኛ ተብለው የፍርድ ድርጅቱን እንደ ማፊያ የወንጀል ድርጅት በመጠቀም የዉሸት ዶክመንት ሰርተው፣ የዉሸት ካርታ ሰርተው ያገሪቱን መሬት የሚሰርቁ የሚሸጡ የሚለውጡ በሞት ይቀጡ ።

አባዱላ ገመዳ ለምንድን ነው ለፍርድ የማይቀርበው?

የብልጽግና ፓርቲ በሚባል የወንጀል ድርጅት ውስጥ ተደራጅተው አንድ ህዝብ እራሱ የሚፈልገውን እራሱን የመግዛት መብት ይከበርልኝ ብሎ ሲጠይቅ የዚያን ህዝብ ፈቃድና ውሳኔ ሰርቀው በማጥፋት እራሳቸው በፈበረኩት ውሳኔ የሚተኩ የህዝብ መብት ሌቦች ልክ እንደ ማንኛውም የስንዴ፣ የልብስ፣ የብርና የመሬት ሌቦች ለፍርድ መቅረብ አለባቸው ።

ሌብነት ሁሉ አንድ ነው ። የአንድን ህዝብ ቤትና ንብረት መስረቅና መንብትና ነጻነቱን መስረቅ አንድ ነገር ናቸው ።

በኢትዮጵያ ሁለት የሌቦችና ወንጀለኞች ድርጅት አሉ፤ አንዱ ብልጽግና የሚባል የማፊያ የማፈኛ ድርጅት ነው። ሌላው ባለብዙ እጆቹ መንግስት የሚባል የሌቦችና ውንጀለኞች ድርጅት ነው ።
Last edited by Horus on 14 Jul 2022, 15:11, edited 2 times in total.

Abere
Senior Member
Posts: 15496
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

Re: መንግስትና ብልጽግና የሚባሉ 2 የሌቦችና ወንጀለኞች ድርጅቶች

Post by Abere » 14 Jul 2022, 14:52

:lol: :lol: በመጀመሪያ ያልከውን ቅጣት ለመፈጸም አገሪቱ ህግ አላት እንደ? እኔ እኮ ህግ እና መንግስት የለም ባይ ነኝ። የምትለው በባህል ህግ ይቀጡ ከሆነ ይገባኛል።


Post Reply