አንድ ሺህ 204 ኢትዮጵያውያን ከሳኡዲ አረቢያ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ
*******************
(ኢ ፕ ድ)
በሶስት ዙር በተከናወነ ዜጎችን ከሳኡዲ አረቢያ የመመለስ ስራ አንድ ሺህ 204 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው ተመልሰዋል።
ከተመላሾቹም 728 ወንዶች፣ 169 ህጻናትና 307 ሴቶች ናቸው ተብሏል።
ለተመላሽ ዜጎችም ተገቢውን ድጋፍና እንክብካቤ በማድረግ ወደ ተዘጋጀላቸው የማቆያ ማእከላት እንዲሄዱ ተደርጓል፡፡
እስካሁን ድርስ በተከናወነው ዜጎችን ወደ ሀገር የመመለስ ስራ ቁጥራቸው 48 ሺህ 612 ኢትዮጵያውያንን መመለስ
መቻሉን የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቋል።



