ኢዜማ በኦነግ-ብልፅግና ተወረሰ ወይስ ፈረሰ? 3ኛው ዓለም ውስጥ የተወለደ ሕፃን ልጅ እና የፓለቲካ ፓርቲ ዕድሜው አጭር ነው።ሁለቱም የተዛማች የኢንፌክሽን በሽታዎች ሰለባዎች ናቸው።
ኢዜማ በኦነግ-ብልፅግና ተወረሰ ወይስ ፈረሰ? 3ኛው ዓለም ውስጥ የተወለደ ሕፃን ልጅ እና የፓለቲካ ፓርቲ ዕድሜው አጭር ነው።ሁለቱም የተዛማች የኢንፌክሽን በሽታዎች ሰለባዎች ናቸው። እኔ እንኳን ስለ ኢዜማ የማውቀው ነገር የለኝም፤ ግን ሰሞኑን የተለጣጠፉት ቪድዮዎች የሚያስተላልፉት መልዕክት ይህ ፓርቲ ወይ በኦነግ ብልጽግና ተስቦ በሽታ ተይዟል ወይም በአባላቱ መካከል የመርህ እና የርዕዮተ-አለም ልዩነቶች ተፈጥረዋል። ሁለቱም ለፓርቲው መሞት አስተዋጽኦ ሊያበረክቱ ይችላሉ። ትልቁ ችግር ምንድ ነው? እርባና ያለው የፓለቲካ ፓርቲ ዘርቶ ለማብቀል የሚያስችል ዝግጁ የፓለቲካ ማሳ(environment) በኢትዮጵያ የለም - በስልጣን ላይ ያለው ሚሊታሪ ጁንታ ብልጽግና ኦነግ (Military Junta PP-OLF) አገራዊ ፋይዳ ሊኖራቸው የሚችሉ ፖርቲዎች በፍጹም እንድ በቅሉ አይፈቅድም። የፓለቲካ ማሳው ፀረ-መልካም ፓርቲ መርዝ ይረጫል። እንደ አረም እንጅ እንደ ጠቃሚ ጉዳይ አይቆጠሩም። ለዚህም ስኬት ፓርቲዎች ሲጸነሱ ጀምሮ ጸር የሆኑት የብልጽግና ኦነግ አረሞች እንደ ሓረግ አብረው ይሰባጠራሉ። እኔ እንኳን በኢትዮጵያ እስከ አሁን አንድም ፋይዳ ያለው የፓለቲካ ፓርቲ አይቸ አላውቅም - የምሰማውም ሁሉ ፋይዳ እንደማይኖረው አውቃለሁ። ለማንኛው ስለ ኢዜማ ስለሚባለው ፓርቲ ተልዕኮ እና የፓሊሲ ራዕይ የምታውቁ የኢንተርኔት መስፈንጥሩን (link) ብትለጥፉልኝ አመሰግናለሁ። ታሪካውን ሳላውቀ እንዳያልፍ ነው።
Re: ኢዜማ በኦነግ-ብልፅግና ተወረሰ ወይስ ፈረሰ? 3ኛው ዓለም ውስጥ የተወለደ ሕፃን ልጅ እና የፓለቲካ ፓርቲ ዕድሜው አጭር ነው።ሁለቱም የተዛማች የኢንፌክሽን በሽታዎች ሰለባዎች ናቸው።
Dr. Berhanu Nega should do the right thing.
Resign from EZEMA and apply to join PP.
The application may be rejected but it may save the party
.
Resign from EZEMA and apply to join PP.
The application may be rejected but it may save the party
.