Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Horus
Senior Member+
Posts: 42983
Joined: 19 Oct 2013, 19:34

የጎሳ ፖለቲካ ሰንዳ

Post by Horus » 08 Jun 2022, 12:50

የዘር ፖለቲካ ሁለት ስለት ያለው ሳንጃ ነው። ሰንዳ ማለት ያ ነው ። የጎሳ ፖለቲካን እንደ ማህበራዊ ሰርዓት ወስደው ተግባራዊ ለማድረግና የኢትዮጵያን አንድ አገርነት፣ አንድ ሕዝብነት ለማፍረስ ድፍን አምሳ አመት የባከኑት የዘር ነጋዴዎች ዛሬ በራሳቸው ሰንዳ እየተቆራረጡ ነው ። ይህ እንደ ሚሆን ሺ ግዜ ነግረናቸው ነበር።

ሰንዳ ለማንም አያዳላም ። ሰንዳ ሌላውን ቆርጦ ሲመለስ ባለቤቱን ይቆርጣል! ሰንዳ ትግሬ፣ ኦሮሞ፣ አማራ አይልም። በጎሳ ሰርዓት ውስጥ ሰዎች በሃይማኖት ተከፋፍለው ይዋጋሉ። በብሄር ተከፋፍለው ይዋጋሉ ። በዘውግ ተከፋፍለው ይዋጋሉ። በክላን፣ በዞን፣ በወረዳ፣ ባውራጃ ተከፋፍለው ይዋጋሉ ።

የኦሮሞች የባንዲራ ንትርክ ሌላ ጥልቅ የሆነ የክርስቲያንና እስላም ኦሮሞ፣ ያሩሲና ወለጋ ኦሮሞ፣ የሸዋና የእንትን ኦሮሞ ማንነት ልዩነት ውጤት ነው ። ኦሮሞ ወደ ስልጣን በወጣና ትግሉ ሁሉ ስለ ሃብትና ሃይል እየሆነ ሲሄድ ክፍፍሉ እየከረረ መሄዱ ሳይንስ ነው ። ይህ ገና መጀመሪያው ነው ።

በነገራችን ላይ አቢይ አህመድም ከዚህ የባንዲራ ትግል ትምህር መውሰድ አለበት ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ወያኔን ያስወገደው በኢትዮጵያ ታሪካዊ ሰንደቅ ስር ተሰልፎ ነው! ከዚህ የሕዝብ ሰንደቅ አላማና ማንነታችን ምልክት እጅህን አንሳ እንለዋለን። ለሱ ለራሱ ጥቅም ስንል! የባንዲራው መዘዝ ብዙ ነው! አይሞትም! አይረሳም!