Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
Abere
Senior Member
Posts: 15522
Joined: 18 Jul 2019, 20:52

የወያኔ ፀሐይ ስትጠልቅ፤ የኦሮሙማ ኦነግ ጀምበር ደግሞ እያቆለቆለች ነው። እግዜር በወለጋ፤አሩሲ፤ባሌ፤ሀረር፤ወዘተ የፈሰሰውን እንባ ሲያደርቅ የሌላውን እንባ አፍስሶ ነው - እንባን በእንባ

Post by Abere » 07 Jun 2022, 09:52

የወያኔ ፀሐይ ስትጠልቅ፤ የኦሮሙማ ኦነግ ጀምበር ደግሞ እያቆለቆለች ነው። እግዜር በወለጋ፤አሩሲ፤ባሌ፤ሀረር፤ወዘተ የፈሰሰውን እንባ ሲያደርቅ የሌላውን እንባ አፍስሶ ነው - እንባን በእንባ ነው የሚያደርቀው። ጸሎቴ ግን ይቺ የምጥ ቀን አጭር ትሁን ብቻ ነው።አንዳንዶች በውድቀት ቀን ይጨፍራሉ - ዐብያችን ነቢይችን እያሉ። ማስተዋላቸውን ሆዳቸው ነስቷቸዋል። የኦሮሙማው ጌታቸው የህዝብ ድጋፍ ሙቀት እስትንፋሱ ቀዝቅዞ እየከሰመ ያለን አለመረዳታቸው የሚደንቅ ነው። ጥቂቶች የማይባሉ ቅኔ መወድስ በኢንተርኔት የዘርፋሉ። አዎን፤ ባህል ነው ጥንትም የንጉስ እራት በልቶ እና ወይን ጠጅ ጠጥቶ ዝም አይባልም - ለንጉሱ ቅኔ ይዘርፋሉ፤የደገድጋሉ፤ ያሸበስባሉ ይወርባሉ። ግን ከንቱ ውዳሴ ስለሆነ በእግዜር ፊት በግፍ የፈሰሰውን የህዝብ ደም ንጉሱን አያጥብለትም - ይበልጥ እንደ አለላ ያቀላዋል። የእራት ግብዣ የበሉትም እንደ እሪያ (ዓሣማ ) እንጅ እንደ የዋህ በግ አይታዩትም።