Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

"መንግስት፤ የህወሃት እና የኤርትራ ግጭት ወደ ኢትዮ- ኤርትራ ግጭት እንደማያመራ ገለጸ" ... አያመራምን ምን አመጣው?? ፋኖ የሚሸለም እንጂ የሚመታ አይደለም ካሉን ..

Post by sarcasm » 31 May 2022, 11:26

"መንግስት፤ የህወሃት እና የኤርትራ ግጭት ወደ ኢትዮ- ኤርትራ ግጭት እንደማያመራ ገለጸ" ... አያመራምን ምን አመጣው?? ፋኖ የሚሸለም እንጂ የሚመታ አይደለም ካሉን .. ከወር በኃላ ነበር እርምጃ የወሰዱበት!



የኛ ልጅ በርታ በርታ .. የወዲ አፎም ሟሟሟቂያ ...

By
Finfinne Press


ወደ ኢትዮ-ኤርትራ ግጭት አያመራም 😂 .. አያመራምን ምን አመጣው። ለማንኛውም ፋኖ የሚሸለም እንጂ የሚመታ አይደለም ካሉን .. ከወር በኃላ ነበር እርምጃ የወሰዱበት 🙃 !

ህወሓት አሸባሪ ብለው በህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፀደቁ። ይህ ስም በህጋዊ መንገድ እስካልተነሳ ድረስ ሁሌም ሊነገር ይችላል። እንደ ፕሮፖጋንዳው ታዲያ ስያሜው ተመሳሳይ ነው ተብሎ መታሰብ የለበትም።

ይቺ የወዳጅ ወዳጅ ጠላት ታፔላ ብዙዎችን አዘናግታ ገደል ከታለች። ለማንኛውም ቃለ አቀባይ ፣ ፕሮፖጋንዳ ሆነ የመንግስት ሹማምንቶች ከዲፕሎማሲ ከፖለቲካ ብሎም ህዝቡ ምን ይፈልጋል ከሚለው አንፃር በተሰላ መንገድ ነው የሚናገሩት 😃 !

እነሱን ማመን የሚገባው መንግስት ያመናቸው ቀውሶችና የተፃፉ ስምምነቶች ላይ በሚወጡት መግለጫዎች ነው። አለበለዚያ ግን የሚያወሩት የፖለቲካ ቃላትን ነው።
ወዲ አፎም .."የኛ ልጅ በርታ በርታ በTDF እንዳትረታ" .. የሚለውን የመንግስት ቃል ሆነ ፕሮፖጋንዳ ይረዱታል።

የፌደራሉ መንግስት TDF እርምጃ እየወሰደ እንደሆነ ካወቀ ለምን አያግዘንም ? TDF ስትራቴጂካዊ ቦታዎችን ሳይቆጣጠር ለምን አይዋጋም ?

የሚለውን ጥያቄ የሚመልሱት .. በመዘናጋት ውስጥ ወይስ በቃል ውስጥ ነው ? ሁለቱም ሪስክ የዘሉ ውሎች ናቸው። ኤርትራ ታማኝ ሀያል ሀገር የማስተማመኛ ካርድ ስለሌላት የምታምነው አንድም ስምምነት አይኖራትም።

የሚሻለው .."የኛ ልጅ በርታ በርታ በTDF እንዳትረታ" .. የሚለውን ነጥብ በወጥመድነት ለክቶ የፌደራሉ መንግስትን በዳግማዊ ስጋትነት ፈርጆ ነው። በዚህ ሰአት አይደለም የቃል ተጨባጭ የፅሁፍ ስምምነቶች እራሱ ድንገት ይቆርጣሉ። እንደ ፋኖ 😂

Finfinne Press

Please wait, video is loading...



መንግስት፤ የህወሃት እና የኤርትራ ግጭት ወደ ኢትዮ- ኤርትራ ግጭት እንደማያመራ ገለጸ
ህወሃት ኢትዮጵያ እና ኤርትራን ለማጋጨት ትንኮሳ እያደረገ መሆኑን መንግስት ገልጿል


ህወሓት የኤርትራ ጦር ጥቃት “እየከፈተብኝ” ነው ሲል ከሷል

በአሸባሪነት የተፈረጀው ህወሃት ኤርትራን እየተነኮስ መሆኑን የኢትዮጵያ መንግስት ገልጿል፡፡

የህወሓት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ ቅዳሜ እና ዕሁድ ዕለት የኤርትራ ሠራዊት በሽራሮ በኩል ጥቃት ከፍቶ እንደነበር ቢገልጹም የኢትዮጵያ መንግስት ግን ቀድሞ ትንኮሳ ያደረገው ህወሃት እንደሆነና በዚህም ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል ብሏል፡፡

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ለአል ዐይን አማርኛ እንደተናገሩት ህወሃት የኤርትራ ጦር ጥቃት ከፈተ በሚል የሚያሰራጨው መረጃ ትክክል አይደለም፡፡

https://am.al-ain.com/article/ethiopia- ... a-conflict