*********************************************
በመንግሥት የፀጥታ መዋቅር ውጥ የተሰገሰጉ ፀረ ህዝብ እና የእኩይ ዓላማ አራማጆች ተልዕኮ ያላቸው የፖሊስ አባላት የፈጠሩት ችግር ነው!
የግርግሩ የሁከቱ መነሻ የአንድ ፌደራል ፖሊስ በሴቶች ላይ የአስለቃሽ ጪስ መልቀቅ መሆኑን የአይን እማኞች ነግረውናል:: እማኞቹ እንዳሉት አንድ የፌደራል ፖሊስ የአስለቃሽ ጪስ ከመሬት ጋር በማላተም እንደለቀቀ እና ቡሃላም በእግሩ ወደ ሴቶቹ እንደጠለዘ ገልጸዋል:: በዚሁ መሃል ግርግር ሲፈጠር ሌላ ጪስ በሌላ ፌዴራል ተለቀቀ:: ወንድ ወጣቶች ተሻግረው በመምጣት ተኳሹን ይዘውት የነበረ ሲሆን በሌሎች ፌዴራል ፖሊሶች ሽፋን ተደርጎለት እንዲወጣ ተደርጓል:: በዚህ መሃል ግርግር ተፈጥሯል:: ሴትችና ህፃንናት ለይ ጉዳት ደርሷል:: በርካታ ህፃናትም ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተጠፋፍቷል:: በዚህ ሆነ ተብሎ በተደረገ ሸፍጥ ላይ የተሳተፉ በመንግስት መዋቅር ውስጥ የተሰገሰጉ የፀጥታ አካላት እኩይ ሴራ መሆኑ ታውቆ አፋጣኝ ምላሽ በመንግስት እንዲሰጥ እንጠይቃለን::
ህዝበ ሙስሊሙ ይቅርታ ሊጠየቅ ይገባል!!!
Please wait, video is loading...