Ethiopian News, Current Affairs and Opinion Forum
sarcasm
Senior Member
Posts: 11594
Joined: 23 Feb 2013, 20:08

የአገው ብሔራዊ ክልል መንግስት ጥያቄ በፅሁፍ መልስ እንዲሰጥ ለፌዴሪሽን ም/ቤት አፈ-ጉባኤ የቀረበ አቤቱታ

Post by sarcasm » 26 Apr 2022, 19:03

#አገው
፨፨፨፨፨፨

የአገው ብሔራዊ ክልል መንግስት ጥያቄ ከ2 ዓመት በፊት ለአዊ ብሔረሰብ ዞን ም/ቤት ያቀረብነው ምላሽ አልተሰጠንም በማለት ምላሽ እንዲሰጠን መጋቢት 21/0772014 ዓ/ም ለፌዴሪሽን ም/ቤት አፈ-ጉባኤ ማስገባታችን ይታወቃል።

በመሆኑም የፌዴሪሽን ም/ቤት አፈ-ጉባኤ ጥያቄው ለምን እንደ ዘገየ አጣርቶ መልስ እንዲሰጥ በተደጋጋሚ በአካል በመሄድ የጠየቅን ቢሆንም እስከ አሁን መልስ ማግኘት ስላልቻልን በድጋሜ ከአገው ህዝብ ለቀረበው አቤቱታ በ2 ሳምንት ውስጥ በፅሁፍ መልስ እንዲሰጠን በዛሬው ዕለት ማለትም ሚያዚያ 12/08/2014 ዓ/ም አቤቱታውን ለፌዴሪሽን ም/ቤት አፈ-ጉባኤ አቀርበናል።

የፌዴሪሽን ም/ቤት አፈ-ጉባኤ በ2 ሳምንት ውስጥ ለህዝብ ጥያቄ በፅሁፍ መልስ የማይሰጥ ከሆነ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት የምንስድ መሆናችንን እናሳውቃለን።
የአገው ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በልጆቹ ትግል እውን ይሆናል!!!



Please wait, video is loading...