ኣደ ሉሲ ማለትም ከግዜ ብዛት ተቆልምሞ አዱሊስ ቢባልም፡ ትርጉሙ ‘የሉሲ ኣናት ማለት የብርሃን እናት’ እንደማለት መሆኑን ከቁምነገር አዘሉ ቀልድ አጢነናል። የብርሃን እናት ላይ ከደረስን ሌላዉን ፈላስፎች ተፈላሰፉበት። መቸም ጉደኛዋ ሃገራችን ኤርትራ፡ እዛው ከአዱሊስ ብዙም ሳይርቅ “እም ኩሉ” የሚባል ታሪካዊ ቀዬም ኣላት፡ “የሁሉ እናት” እንደማለት ነው በግዕዙና በትግርኛው ጥምረት ሲተረተርና ሲተነተን። ታዲያ “የሁሉ እናት” እንዲሁም “የብርሃን እናት” እያሉ ነበር ስም የሚያወጡት የኛ ቀደምቶች። እዛው አዱሊስ አካባቢ ቀደምቶቻችን “ገደም” ብለውም ስም ያወጡለት ተራራም ኣለ ፡ ገዲም ማለት ራሱ ቃሉ ቀደምት ማለት ነው ትርጉሙ፤ ጥንት ያኔ ተራራው ገዳም ሆኖ አገልግሎም ሊሆን ይችላል። መቼም የታሪካዊዋን የእምበረሚን ታሪክ እዚህ ላይ ገልጠንላችሁ ነበር። https://mereja.com/forum/viewtopic.php? ... A#p1096664
“ያለ ባለቤቱ አይነድም እሳቱ” እንዲሉ፡ እኛ ኤርትራዉያን የመሃልና የመስመር ዳኞች፡ የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ አዱሊስን፣ ዙላን፣ አብዱርን፣ ቦያን፣ እምኵሉን ገደምንና እምበረሚን አስጎበኘናችሁ አይደል፤